💫💫💫" የሕይወት ወርቃማ መርሆዎች"💫💫💫
1. ከሰዎች ጋር ሮጠህ ያልደረስክበት ነገር ካለ ወደ ተነሳህበት
ተመልሰህ ከፈጣሪህ ጋር መሮጥ ጀምር፣ ያኔ ካሰብክበት
ሳይሆን ካሰበልህ ቦታ ትደርሳለህ፡፡
2. በአብዛኛው ጊዜ ሴቶች የፍቅርን ትርጉም የሚጠፋባቸው
በውበታቸው ማምለክ ሲጀምሩ ሲሆን ወንዶች ደግሞ
በገንዘባቸው ማምለክ ሲጀምሩ ነው፡፡
3. መጀመሪያ ለራስህ ራስህ መሆን ስትጀምር ለማን ምን
መሆን እንዳለብህ ትገነዘባለህ፡፡
4. የሰው ልጅ የማሰብ ችሎታው ሲጨምር የጓደኞቹን ብዛት
ይቀንሳል፡፡
5. ዝቅተኛ እውቀት ባለህ ቁጥር የምትተኛው እንቅልፍ ከፍተኛ
ይሆናል፡፡
6. ጓደኛን አለማመን ከመካድ የከፋ ነው፡፡
7. የራስህን ትኩስ እንጀራ ለመጋገር ስትል የሌላውን ቂጣ
አትርገጥ፡፡
8. አንዳንድ ሰዎች የሚወድቁት ሌሎችን በሁለት እግሮቻቸው
ለመርገጥ ሲጣጣሩ ነው፡፡
9. ሰው ከጊዜ እና ከማጣት ብዙ ይማራል፡፡
10. አንዳንዴ ሽንፈትም ከድል የበለጠ ዋጋ አለው/ ከማሸነፍ
ይልቅ በመሸነፍ ውስጥ ብዙ እውቀት አለ፡፡
11. ሠው የበለጠ እያገኘ በሄደ ቁጥር የበለጠ ስግብግብ
እየሆነ ይሄዳል፡፡
12. ሠዎች ትርጉም ያለው ሥራ መስራት ካልቻሉ የመኖር
ትርጉምም ይጠፋባቸዋል፡፡
13. የሰው ልጅ ከደስታው ይልቅ የሀዘኑን ጊዜያት መቁጠር
ይወዳል፡፡
14. አዋቂ ሆኖ ለመታየት የምናደርገው ጥረትና ከንቱ ድካም
አላዋቂ አድርጎ ያስቀረናል።
@yasin_nuru
💫💫💫" የሕይወት ወርቃማ መርሆዎች"💫💫💫
1. ከሰዎች ጋር ሮጠህ ያልደረስክበት ነገር ካለ ወደ ተነሳህበት
ተመልሰህ ከፈጣሪህ ጋር መሮጥ ጀምር፣ ያኔ ካሰብክበት
ሳይሆን ካሰበልህ ቦታ ትደርሳለህ፡፡
2. በአብዛኛው ጊዜ ሴቶች የፍቅርን ትርጉም የሚጠፋባቸው
በውበታቸው ማምለክ ሲጀምሩ ሲሆን ወንዶች ደግሞ
በገንዘባቸው ማምለክ ሲጀምሩ ነው፡፡
3. መጀመሪያ ለራስህ ራስህ መሆን ስትጀምር ለማን ምን
መሆን እንዳለብህ ትገነዘባለህ፡፡
4. የሰው ልጅ የማሰብ ችሎታው ሲጨምር የጓደኞቹን ብዛት
ይቀንሳል፡፡
5. ዝቅተኛ እውቀት ባለህ ቁጥር የምትተኛው እንቅልፍ ከፍተኛ
ይሆናል፡፡
6. ጓደኛን አለማመን ከመካድ የከፋ ነው፡፡
7. የራስህን ትኩስ እንጀራ ለመጋገር ስትል የሌላውን ቂጣ
አትርገጥ፡፡
8. አንዳንድ ሰዎች የሚወድቁት ሌሎችን በሁለት እግሮቻቸው
ለመርገጥ ሲጣጣሩ ነው፡፡
9. ሰው ከጊዜ እና ከማጣት ብዙ ይማራል፡፡
10. አንዳንዴ ሽንፈትም ከድል የበለጠ ዋጋ አለው/ ከማሸነፍ
ይልቅ በመሸነፍ ውስጥ ብዙ እውቀት አለ፡፡
11. ሠው የበለጠ እያገኘ በሄደ ቁጥር የበለጠ ስግብግብ
እየሆነ ይሄዳል፡፡
12. ሠዎች ትርጉም ያለው ሥራ መስራት ካልቻሉ የመኖር
ትርጉምም ይጠፋባቸዋል፡፡
13. የሰው ልጅ ከደስታው ይልቅ የሀዘኑን ጊዜያት መቁጠር
ይወዳል፡፡
14. አዋቂ ሆኖ ለመታየት የምናደርገው ጥረትና ከንቱ ድካም
አላዋቂ አድርጎ ያስቀረናል።
@yasin_nuru