Mensur Redwan Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Mensur Redwan shared a
Translation is not possible.

🇵🇸ሩቅ አይደለም!!

💫ነብዩ ኢብራሂምﷺ እጅ እና እግራቸው ጠፍረው እሳት ውስጥ የወረወሯቸው ሰዎች በዝያች ቅፅበት አላህ አላጠፋቸውም።

💫ፊርዓውን "እኔ ጌታችሁ ነኝ" እያለ ያልተቀበሉት ሰዎች ሰውነታቸው ቆራርጦ ሰቅሎ እየገደለ ሲያሰቃያቸው በዝያች ቅፅበት አላህ አላጠፋውም።

💫አላህ ከሰማይ መልእክት እያወረደላቸው "ጌታችሁ አላህ ነው, ተገዙት" ያሉ ነብያቶች የገደሉ ሙጅሪሞች አላህ በዝያች ቅፅበት አላጠፋቸውም።

💫"ጌታችን አላህ ነው, በእሱም አምነናል።" በማለታቸው ብቻ ጎድጓድ ቆፍረው እሳት አንድደው ያቃጠሏቸው “አስሀብ አል_ኡኽዱድ” አላህ በዝያች ቅፅበት አላጠፋቸውም።

💫ለዓለማት እዝነት ተደርገው የተላኩት ውዱ ነብይﷺ ጀርባ ላይ ፈርስ እየጣሉ፣ በተደጋጋሚም የግድያ ሙከራ ያደረጉ ሙጅሪሞች አላህ በዝያች ቅፅበት አላጠፋቸውም።

💫አላህ ከፈጠረው ሁሉ በላጭና ክቡር የሆኑት ነብዩﷺን ጦር ሜዳ ላይ ገጥመው ጭንቅላታቸው እስኪደማ የተዋጉዋቸው ሙጅሪሞች አላህ በዝያች ቅፅበት አላጠፋቸውም።

💫ቀራሚጣዎች ጀናዛ የያዙ አስመስለው ሰይፋቸው በከፈን ሸፍነው ወደ ኻረም ካስገቡ በኋላ በአንድ ጀምበር ብቻ ከሶስት ሺህ (3000) በላይ ሑጃጆች ገድለው፣ የዘምዘም ውሃ በሑጃጆች ጀናዛ ደፍነው፣ የተከበረው የካዕባ ሽፋን በጣጥሰው፣ መሪያቸው ከፍታ ላይ ቆሞ “የዛሬው ንግስና ለማን ነው?” እያለ ሲፎክር፣ “ጠይረል አባቢል የት አሉ? ሂጃራ ሚን ሲጂል የት አለች?” እያለ ሲፎክር፣ ሱረቱል ቁረይሽ እየቀራ “ከፍራቻ ሰላም ሰጣቸው ይላል ከእኛ ፍራቻ ግን ሰላም አልሰጣቸውም” እያለ ሲያላግጥ፣  ሀጀረል አስወድን ቀምተው ወደ ሀገራቸው ወስደው ሲጫወቱበት አላህ በዝያች ቅፅበት አላጠፋቸውም።

              لا إله إلا الله

በዚች ምድር ላይ ምን ግፍ አልተፈፀመም??

  ታድያ እነዝያ ሁሉ በዳዮች አሁን የት ነው ያሉት⁉️

   ወዴት ነው የሄዱት⁉️

ወላሂ ሁላቸውም ወደ ሰሩት ነገር ሄደዋል!!

ምክንያቱም፦

   ከጌታህ ሊያመልጥ የሚችል የለም!!

እናም ወዳጄ……

   የቁድስን ክብር አዋርደው፣ የሙስሊሞች ሀገር ቀምተው፣ ሴቶችና ህፃናት ጨፍጭፈው; እንዲሁ የሚተዉ ይመስልሀል!?

  ወላሂ አይተዋቸውም‼️

=> ቅጣታቸው የበለጠ አሳማሚ እንዲሆን አመፃቸው እንዲበዛ፣

=> አላህ የያዘላቸው ቀጠሮ እስከ ሚደርስ

     እና

=> አላህ የፈለገው ጥበብ እስኪሟላ ያቆያቸዋል እንጂ

   ሁሉም የጀሀነም ሙኩቶች ናቸው ወደዝያው በቅርብ ይነዳሉ።

  ቅርብ ነው, ሩቅ እንዳይመስልህ!!

  https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Send as a message
Share on my page
Share in the group