UMMA TOKEN INVESTOR

Neima Hussen shared a
Translation is not possible.

#የኩዌቱ_ፀሐፊ ዐብደላህ አልጃረላህ ዛሬ እንደሞተ ተነግሯል - አላህ ይዘንለት፡፡ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፡፡

- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣

- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ

ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡

1- ልብሴን ያወልቃሉ፣

2- ያጥቡኛል፣

3- ይከፍኑኛል፣

4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣

5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣

6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣

7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡

ከነኚህ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡

8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል

- ቁልፎቼ

- መጽሐፎቼ

- ጫማዎቼ

- ልብሦቼ …..

በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣

- የዓለም እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣

- የኢኮኖሚው ቀውስም አልተፈጠረም፣

- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ ይወጣል፣

- ንብረቴ የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣

- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤

- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል

- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤

ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! …

በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ

1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ

2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣

3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣

የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ

ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!

1- መልክህ፣

2- ሀብትህ፣

4- ጤናህ፣

5- ልጅህ፣

6- ቪላህ፣

7- ዝናህ፣

8- ሚስትህ/ባልሽ

ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ

እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡

እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ

ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡

እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ

1- በግዴታዎች፣

2- በሱንና ነገሮች፣

3- በድብቅ መፅውት፣

4- መልካም ሥራ አብዛ፣

5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣

ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡

መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡

ምንጭ ፡ ጠሪቁ ተውበህ

abu kalid wa islam

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Neima Hussen Changed her profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group