UMMA TOKEN INVESTOR

Suleyman Dawud Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

" የአላህ መልእክተኛ ነብያችንን ስታገኟቸው ህዝቦችህ ከዱን ኡመቶችህ የጋዛን ህዝቦች ከዷቸው በሏቸው ። የልጅ ልጆቼ ሆይ ለአላህ መልእክተኛ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ንገሯቸው ! የልጅ ልጆቼ ሆይ የሆነብንን ሰሙቱላቸው ! የአላህ መልእክተኛ ሆይ ኡመቶችህኮ የጋዛ ህዝብ እንዲጠፋ ፈቀዱ በሏቸው ! የአላህ መልእክተኛ ሆይ ጠላቶቻችን እንዲያወድሙን ኡመቶችህ ፈቀዱላቸው በሏቸው ! የኢስላም ጠላቶች ሲበጣጥሱን ህዝቦችህ ፀጥ ብለው ተመለከቱን በሏቸው ! "

ይህ እኝህ የፍልስጤም አባት በእስራኤል የሚሳኤል ናዳ የተቀጠፉ ልጆቻቼውንና የልጅ ልጆቻቼውን ሲሸኙ ያስተላለፉት ልብ ሰባሪ መልእክት ነው ።

አላህና መልእክተኛው ፊት መልሳችን ምን ይሆን ???

ፍልስጤማዊያን አላህ እና መልእክተኛው ፊት ሲከሱን መልሳችን ምን ይሆን ?

አሁን እኛ በውዱ ነብይ መናፈቅ የሚገባን ህዝቦች ነን ወይ 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

5 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እንዳትሰላቹ እስከ መጨረሻው ይነበብ!!!

እ.ኤ.አ. በ 1258 የሞንጎላውያን ጦር ለማውራት የሚዘገንን እልቂት የበግዳድ ሙስሊሞች ላይ ከፈፀመ፣ የዐባሳውያን ኺላፋንም እስከ ወዲያኛው ካፈራረሰ በኋላ እርጥብ ደረቅ ሳይለይ ያገኘውን እየበላ ወደ ደማስቆ ሲገሰግስ የሆነውን አልኢማም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይተርኩታል።

“ከኢስላማዊ ሸሪዐህ ውጭ ያለው የተታር ጦር ደማስቆን ሲያጠቃ ጊዜ ላኢላሀ ኢለላህ” የሚሉት ሙስሊሞች ወደ ሁሉን ቻዩ አላህ ከመሸሽ ይልቅ ‘አደጋን ያስወግዳሉ፣ ጉዳትን ያነሳሉ’ ብለው ወደሚያምኑባቸው ሰዎች መቃብር ነበር የወጡት። ከነዚህም ሰዎች ገጣሚያቸው እንዲህ ሲል ገጥሟል፡-

‘እናንት ተታርን የምትፈሩ

በአቡ ዑመር ቀብር ተጠለሉ።’

ወይም ደግሞ እንዲህ ይል ነበር፡-

‘በአቡ ዑመር ቀብር ተጠበቁ

ያተርፋችኋል ከጭንቁ።’

ይህኔ እንዲህ አልኳቸው፡ ‘እነዚህ እርዳታን የምትጠይቋቸው ሰዎች ከናንተው ጋር ጦርነቱ ውስጥ ቢገቡ ልክ የኡሑድ ጦርነት ላይ ሙስሊሞች እንደተሸነፉት ይሸነፋሉ።’ … በዚህም ሳቢያ የዲኑ ምሁራን እና አስተዋዮች በዚህ ጦርነት ጊዜ አልተዋጉም። ምክንያቱም አላህና መልእክተኛው ያዘዙበት የሆነው ሸሪዐዊ ጦርነት ስላልነበር፣ ክፋትና ጥፋት የሚከተለው በመሆኑ፣ በጦርነቱም የሚፈለገው ድል ባለመኖሩ ነው። እናም የዱንያም ይሁን የአኺራ ሽልማት አይገኝበትም።… ከዚህ በኋላ ሰዎችን ሃይማኖታቸውን አሸናፊና የላቀ ለሆነው አላህ እንዲያጠሩ፣ ከሱም ብቻ እንጂ እርዳታን እንዳይጠይቁ፣ ከዚህ ውጭ ቅርብ በሆነ መልአክም፣ በተላከ ነብይም እርዳታን እንዳይጠይቁ ማዘዝ ያዝን። ልክ የላቀው አላህ የበድር ጦርነት ጊዜ ከጌታችሁ እርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ መለሰላችሁ እንዳለው ማለት ነው። … ከዚያ በኋላ ሰዎች ሁኔታዎቻቸውን ሲያስተካክሉና በጌታቸው እርዳታ እውነት ብለው ሲያምኑ በጠላታቸው ላይ ረዳቸው። ተታሮች የዚህን ጊዜ የተሸነፉትን ያክል ቀድመው አልተሸነፉም። ምክንያቱም ቀድሞ ከነበረው በተለየ የላቀው አላህ ተውሒድ እና ለመልእክተኛው ታዛዥ መሆን በሚገባ ስለተረጋገጠ ነበር። የላቀው አላህ መልእክተኛውንና እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቷም ህይወት እንዲሁም ምስክሮች በሚቆምበት ቀን በርግጥም ይረዳል።” [አረድ ዐለል በክሪ፡ 2/732-738]

ዛሬም ችግሩ ከፍቶ ሙስሊሙ በዐቂዳህ ብክለት ከጫፍ እስከ ጫፍ ይናጣል። ፍትህን በነፈጉት አንባገነኖች ይረገጣል። በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ይታመሳል። ታዲያ ችግሩን የሚመለከቱ የተለያዩ አካላት እንደየአስተሳሰባቸው የተለያዩ የመፍተሔ አቅጣጫዎችን መርጠዋል። ከፊሉ ሙስሊሙን ካለበት ውርደት ለማውጣት ሁነኛው መፍተሄ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን ማፈርጠም ነው በሚል ጧት ማታ ለዚያ ይጥራል፣ ስለለዚያም ይደሰኩራል። ከፊሉ ሌሎች አጀንዳዎችን ከቁብም ሳይቆጥር ማህበራዊ ህይወትን ያቃና ዘንድ ሰርክ ደፋ ቀና ይላል። ሌላው የችግሩን ቀዳሚ ሰበብ ፖለቲካ አድርጎት ኖሮ የስልጣን ማማዎችን ለመቆናጠጥ ሳይቦዝን ይጭራል። ሌላው ደግሞ የችግሩ ምንጭ ከዘመናዊ ትምህርት መራቃችን ነው በሚል ያለ የሌለ ሃይሉን አስኮላ ላይ አድርጓል። እነዚህ “የመፍተሄ አቅጣጫዎች” ከፊሎቹ ቢሳኩም የሙስሊሙን ክብር የማያስመልሱ፣ ካለበት ምስቅልቅል ህይወት የማያወጡት ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ከፊል እውነታ ቢይዙም ነገር ግን ባፈፃፀማቸው ግድፈት ምክንያት ይበልጥ የሙስሊሙን ስቃይ ጨምረውታል። “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ።

በኢኮኖሚ መፈርጠም ከገባንበት ውጥንቅጥ ለመውጣት ዋስትና አይሆነንም። እንዳውም ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም {ድህነትን አይደለም የምፈራላችሁ! ይልቁንም ሀብትን ለማግበስበስ የምታደርጉትን መሽቀዳደም ነው የምፈራላችሁ!} ይላሉ። [አስሶሒሐህ፡ 2216] ዛሬ ዱንያ ፊቷን ስታዞርላቸው ከዲን ፊታቸውን የሚያዞሩት ስንቶች ናቸው? ዘመናዊ ትምህርትም ብቻውን ከችግራችን አይታደገንም። እንዳውም በቅጡ ካልተያዘ፣ በከሃዲዎች ታሪክና ስልጣኔ ተማርከን የአስተሳሰብ ቅኝ ግዛት ስር ከወደቅን መማራችን ይበልጥ ለውድቀታችን ሰበብ ሊሆን ይችላል። ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንደሚሉት “የፋርስና የሮማ ፈላስፎች ጥበብ ላይ የሚያተኩር ለኢስላማዊ ጥበብና ስርኣት ልቡ ውስጥ ቦታ አይኖርም።” [አልኢቅቲዳእ፡ 217] ዛሬ ሃያ ሰላሳ አመት እድሜያቸውን ትምህርት ላይ ፈጅተው ይሄ ነው የሚባል ትኩረት ባልሰጡት እምነት ላይ በተበከለ ህሊናቸው ሊፈርዱ የሚዳዳቸው ስንቶች ናቸው? የስልጣን ማማዎችን መቆናጠጥም በራሱ ሸሪዐዊ ፍትሕ በህዝብ ዘንድ እንዲሰፍን አያደርግም። ለምን ቢባል“ከተውሒድ በላይ ፍትህ፣ ከሺርክ በላይ በደል የለምና!!" [መዳሪጁስሳሊኪን፡ 3/336] ይልቅ ቀዳሚው የመፍተሄ አቅጣጫ የዐቂዳን ብክለት ማስወገድ ነው። እምነት ሲስተካከል ሌሎቹ ጉዳዮች መስመር ይይዛሉ። ተውሒድ በሌለበት የሙስሊሙ ልማትም፣ ብቃትም፣ ንቃትም ፍትሕም አይታሰብም።

ከ"ተውሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ" መጽሐፍ የተወሰደ

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የተባረከው የፍልስጤም ምድር  

              ክፍል 1

✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️

   የተባረከው የፍልስጤም ምድር መቼም ቢሆን የአይሁድ ይዞታ ሆኖ አያውቅም፡፡ ለዚህ አንዱ ማስረጃ ለአይሁድ የተለየ አገር (separate homeland) የመፍጠሩ ሀሳብ ሲንሸራሸር በነበረበት ወቅት ከፍልስጤም ውጭ ሌላም ቦታ ታስቦ የነበረ መሆኑ ነው፡፡

ዛሬ ዓለምን ለማደናገር እንደሚሞከረው የፍልስጤም ምድር ከድሮም የአይሁድ ይዞታ የነበረ ቢሆን ኖሮ፣ ለነሱ አገር ቤት በመፍጠሩ ሀሣብ ውስጥ አርጀንቲናና ዑጋንዳ ታሳቢ ባልተደረጉ ነበር፡፡

   ለአይሁድ የብቻ አገር ቤት የመፍጠሩ ሀሣብ የአውሮጳን ቡራኬ አግኝቶ በዋናነት ፍልስጤም ተመረጠች፡፡ ዓላማውን እውን የማድረጉ እንቅስቃሴም ተጀመረ፡፡ ጊዜው በ8ኛው መቶ ሂጅሪያ ማብቂያ ላይ ነበር፡፡ ይህ ወቅት ደሞ የምዕራብ የኩ#ፍ..ር ኃይላት የዑስማንያ ቱርክን ኢስላማዊ መንግሥት ለመጣል የተጠናከረ ርብርብ እያደረጉ የነበረበት ወቅት ነው፡፡

አይሁዶችም ይህንኑ ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀምና ገፀ-በረከት በማስያዝ አንድ ከማኅበረ-አይሁድ የተውጣጣ የልዑካን ቡድን በአውሮጳ ድጋፍ ሰጪነት ወደ ወቅቱ የዑስማኒያ ኸሊፋ ሡልጣን ዐብዱልሐሚድ ላኩ፡፡ ልዑኩም በሡልጣኑ ቤተ-መንግሥት ተገኝቶ አይሁዳዊያን በፍልስጥኤም መሬት ላይ መሥፈር እንዲችሉና የመግቢያ ፈቃድም እንዲሰጣቸው ተማጽኖ አቀረበ፡፡

   ሡልጣን ዐብዱልሐሚድ ግን በጊዜው መንግሥታቸው ላይ እየተደረገ በነበረው አሉታዊ ጫና ሳይበገሩ፣ በቀረበላቸው ገፀ-በረከትም ሳይደለሉ የአይሁዶችን ጥያቄ ውድቅ አደረጉ፡፡ አይሁዶች አንዴ እንደምንም ብለው ፍልስጤም መሬት ላይ እግር መትከል ከቻሉ አገሪቱን ከተቀረው ኢስላማዊ ግዛት በቀላሉ በመነጠል የግላቸው ሊያደርጓት ይችላሉ የሚል ስጋት ነበራቸው፡፡ ቀድሞ ከታያቸው ከዚህ ሥጋት በመነሳትም ይመስላል ሡልጣኑ በ1900 እና በ1901 መካከል በነበረው አጭር ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ ደንቦችን በማስረቀቅ ማንኛውም የአይሁድ መንገደኛ ከሶስት ወር ባለፈ ፍልስጥጤም መሬት ላይ ውሎ ማደር እንደሌለበት የደነገጉት፡፡ ከዚህም ሌላ ምንም ዐይነት የመሬት ሽያጭ ከአይሁድ ጋር እንዳይፈፀም ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ 

    የአይሁዶች ጥረት ግን በቀላሉ የሚቆም አልነበረም፡፡ ሰላሳ አምስት ሚሊዮን የወርቅ ዲናሮችን በከረጢት ቋጥረው እንደገና በ1920 ወደ ሡልጣኑ ቤተ-መንግሥት አመሩ፡፡ በጊዜው የዑስማኒያ ኢስላማዊ መንግሥት ካዝና በብዙ ወጪዎች ተራቁቶ ባዶ እንደነበረም ያውቃሉ፡፡ እንደዛም ሁኖ ግን የኢስላማዊውን መንግሥት ይሁንታ በወርቅ ሳንቲሞች ለመግዛት ያደረጉት ጥረት በሡልጣኑ ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም፡፡ ሡልጣኑ የጉዳዩ ዋና አስተባባሪ ለነበረው ለቴዎዶር ሄርዞል በላኩት ማስታወሻ ግልጽ አደረጉ

“… የግል ንብረቴ አይደለምና ከፍልስጤም መሬት ስንዝር ቆርሼ መስጠት አልችልም፡፡ ባለመብቱ ህዝቡ ነው፡፡ ህዝቦቼ ለዚህ መሬት ሲሉ የህይወት መሥዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ ደማቸውን አፍሰውበታል፡፡ ስለዚህ አይሁዶች የወርቅ ዲናሮቻቸውን ለራሳቸው ያድርጉት፡፡ ምናልባት መንግሥቴ ቢፈርስ ያን ጊዜ ፍልስጤምን በቀላሉ ነጥሎ መያዝ ይቻላቸው ይሆናል፡፡ እኔ በአፀደ ሥጋ እያለሁ ግን ከሰውነቴ ላይ በስለት ተቆርጦ ቢወሰድ ይቀለኛል - ፍልስጤም ከኢስላማዊው መንግሥት ተነጥላ ስትሄድ ከማይ፡፡ ይህ ደሞ ከቶም ሊሆን የማይችል ነው” በማለት ያላቸውን ቁርጠኛ አቋም ግልጽ አደረጉላቸው፡፡ 

                     ይቀጥላል…

መረጃው ሌሎች ጋር እንድደርስ ሸር ማድረጋችሁን አትርሱ።

💯ተጨማሪ መረጃ እንድደርስዎ ቻናላችንን Join በማድረግ ይቀላቀሉ

👇👇👇

ቴሌግራም:–

https://t.me/Brathersmedia

👇👇👇

ኡማ ላይፍ:–

https://ummalife.com/Brathersmedia

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሁለቱም አንድ አይነት ጥምጣም ነው የለበሱት፣ ግና አንደኛው ወጣትነቱን ለአላህ ዲን መስዋት አድርጎ እስከ አፊንጫቸው ከታጠቁ ሸያጢኖች ጋ ሊ'ፋ'ለም ግንባር የተሰለፈ ሰሆን ሌላኛው ደግሞ ሪያድ ላይ ለተዘጋጀ ዳንኪራ መድረክ ሊመራ የተሰየመ ነው.....

{ قُلۡ كُلࣱّ یَعۡمَلُ عَلَىٰ شَاكِلَتِهِۦ فَرَبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِمَنۡ هُوَ أَهۡدَىٰ سَبِیلࣰا }

አብዱሰመድ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group