🔔「 በደንብ የሰሙት 」📈
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬
✅¹:የሰሙትማ ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል፡፡ ሱንናዎችን ጠራርገው ሰርተዋል፡፡ አላህ ሱብሃነሁ ወተዐላ በሚወዳቸው ነገሮች ላይ ፈጥነው ተገኝተዋል፡፡ ለዚህ ዲን የቻሉትን ያህል አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ በደንብ የሰሙት እነ ቢላል ፣ እነ ሱመያ፣ እነ ያሲር ፣ እነ ኸባብ ናቸው፡፡ በብርቱ ቅጣት በአላህ መንገድ ተፈትነውዝንፍ አላለም ከአቋማቸው፡፡በደንብ የሰሙት ለዚህ ዲን ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ታስረዋል፣ ተርበዋል ፣ ተሠደዋል ፣ ተንገላተዋል ፣ ደህይተዋል ፣ ታመዋል ፣ ቆስለዋል ፣ ደምተዋል ፣ ሙሉ ንብረታቸውን ለአላህ መንገድ ሠጥተዋል፡፡ የሚወዷትን ነፍስ ሰውተዋል፡፡
✅²:በደንብ የሰሙት ምድርን ሳይለቁ እዚሁ እያሉ የጀነት እንደሆኑ ተበስረዋል፡፡ ሥራቸው አላህ ሱብሃነሁ ወተዐላ ተቀባይነት እንዳገኘ ተነግሮአቸዋል፡፡ አላህ ወዷቸዋል፡፡ እነርሱም ባገኙት ምንዳ ተደስተዋል፡፡ በደንብ የሰሙት እነ አቡበክር፣ እነ ዑመር፣ እነ ዑስማን፣ እነ ዐሊ፣ እነ ዐብዱረህማን፣ እነ ዙበይር፣ እነ ሠዕድ፣ እነ ሰዒድ፣ እነ ዙበይር፣ እነ ጦለሃ ናቸው፡፡
✅³:በደንብ የሰሙት ሶሃቦች ወደ ፍልሚያ ሜዳ ሲሮጡ በእጃቸው የያዙትን የተምር ፍሬ እንኳ ለመጨረስ አልታገሱም፡፡ ‹ቆስለናል፣ ደምተናልና እረፍት ያስፈልገናል፡፡ አላሉም፡፡ ‹ወቅቱ ሀሩር ነውና ዘመቻው ለሌላ ጊዜ ይተላለፍልን፡፡› ብለው አልተከራከሩም፡፡ የሰሙ ሰዎች ትእዛዙ እስኪደገምላቸው አልጠበቁም፡፡ ቁሙ ሲባሉ ቆሙ ተነሱ ሲባሉ ተነሱ፡፡ ሥሩ ሲባሉ ሰሩ፡፡ ተው ሲባሉ ተው፡፡
✅⁴:በደንብ የሰሙት ሶሃቦች ኢስላምን ለመከላከል ከፊት ነበሩ፡፡ በድር ላይ የሐምዛ ተጋድሎ ይነገራል፡፡ ኡሑድ ላይ የጦለሃ ተወርዋሪነት ይተረካል፡፡ አል አሕዛብ ላይ የዐሊ ደጀንነት ይወሣል፡፡ ሙእታ ላይ የጀዕፈር ትንግርት ይዘከራል፡፡ የርሙክ ላይ የአል ኸንሣእ ልጆች ውሎ ይተረካል፡፡
🚨እነርሱ በርግጥም በደንብ ሰምተዋል። አድርጉ የተባሉትን አድርገዋል። ተከልከሉ የተባሉትን ተከልክለዋል።
📏📏📏📏✨📏📏📏📏
➡️ሙስሊም በሰማው እና በታዘዘው ልክ ነው ስኬቱ፡፡ በደንብ የሰሙት ሁሌም ስኬት አላቸው፡፡ በሁለቱም ዓለም የበላይ ናቸው።ሰምተው የታዘዙት ጀነት ናቸው፡፡ ሰምተናል አንበል አልሠማንም፡፡ እስቲ ለአፍታም ቢሆን ቁርኣን የሚለውን በደንብ እንስማ፡፡ መልእክተኛ ﷺ የሚሉትን በደንብ እናደምጥ፡፡ ስንጠራ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ስንባል ጆሮ እንስጥ፡፡ እናዳምጥ፡፡ እናትኩር፡፡ አላህ ሱብሃነሁ ወተዐላ ምን ይላል መሠላችሁ፡፡
🔘يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَا تَوَلَّوْا عَنْهُ وَأَنتُمْ تَسْمَعُونَ]وَلَا تَكُونُوا كَالَّذِينَ قَالُوا سَمِعْنَا وَهُمْ لَا يَسْمَعُونَ [٨:٢١]
🔴‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ፡፡ እናንተም የምትሰሙ ስትኾኑ ከርሱ አትሽሹ፡፡ እንደነዚያም እነሱ የማይሰሙ ሲኾኑ ሰማን እንዳሉት አትሁኑ፡፡› (አል አንፋል፡ 20-21)
🔘يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَجِيبُوا لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمْ لِمَا يُحْيِيكُمْ ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ يَحُولُ بَيْنَ الْمَرْءِ وَقَلْبِهِ وَأَنَّهُ إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ
🔴‹ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልክተኛው) ሕያው ወደሚያደርጋችሁ እምነት በጠራችሁ ጊዜ ለአላህና ለመልክተኛው ታዘዙ፡፡ አላህም በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መኾኑን ወደርሱም የምትሰበሰቡ መኾናችሁን እወቁ፡፡› (አል አንፋል፡ 24)
/ አላህ ቀልብ ይስጠን /
┊ ┊ ┊ ┊
┊ ┊ ┊ ✿
┊ ┊ ❀ 📚
┊ ✿ 📌
❀ሼር አድርጉት በጥሞና ይነበብ በቻልነዉ ያህል እንስራበት الله መልካም ስራዎች አብዝተዉ እንዲሰሩ ከተወፈቁ ባሮቹ ያድርገን
https://ummalife.com/umma1698085195