UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ያለህ ነገር ...ሀብት ...ዕውቀት ...ስልጣን ...ባንተ ብልሃት፣ባንተ ብልጠት ፣ባንተ አቅም ሳይሆን በአላህ ችሮታ መሆኑን አትዘንጋ !...ያላቸው ነገር የተሰጣቸው እነሱ ባለመብት በመሆናቸው እንደሆነ የተሰማቸው ሰዎች ሲጠፉ አይተናል ...ሂጃብ የለበሰች ሴት ሂጃቡን የለበሰችው እሷ ተገቢ ስለሆነች እንደሆነ አስባ ተኩራርታ ያለበሱትን ስትንቅ በተቃራኒው አድርጎ ያለበሱትን አልብሶ እሷ አውልቃ አይተናል ...መስጂድ በመመላለሱ ሶላት በመስገዱ ባልሰገዱት ላይ ሲኩራራ እሱ ከጀመዓም ከጁመዓም ቀርቶ በነሱ ላይ ሲኩራራባቸው የነበሩት በቦታው ተተክተው የመስጂድ ቤተሰብ የሆኑበትን አጋጣሚ አይተናል...መልካም ነገር ሲደረግልህ ያ ጉዳይ የተደረገልህ ተገቢ ስለሆንክ ያልተደረገላቸው ሰዎች ደግሞ ብልጠት ስለጎደላቸው እንዳይመስልህ አላህ ነው ሁሉን ያደረገው እንደኛ ቢሆንማ...

★ወንጀል ላይ በወደቀ ሰው አትሳለቅ ..በከሰረ ሰው አታሹፍ... በተፈተነ ሰው ላይ አትኩራራ... ምናልባት ያጋጠማቸው ነገር አንተን ቢያጋጥምህ ልትብስ ትችላለህ ...ሁሉም የአላህ ችሮታ ነው በብልጠትህ አይደለም !

አብሽር የኔ መልካም ❤

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሙዓዝ ኢብኑ አነስ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “ከእምነት በላጩ ለአላህ ብለህ መውደድ፣ ለአላህ ብለህ መጥላት፣ አንደበትህን በመልካም ስራ መስራት ነው። አላህን ማውሳት" ሙዓዝ “እንዴት ነው የአላህ መልእክተኛ ሆይ?” አለው። ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ለራስህ የምትወደውን ለሰዎች ውደድ፣ ለራስህም የምትጠላውን ለነሱ ጠልተህ መልካም ነገርን ተናግረህ ወይም ዝም ትላለህ።

ሙስነድ አህመድ 21627

عن معاذ بن أنس قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَفْضَلُ الْإِيمَانِ أَنْ تُحِبَّ لِلَّهِ وَتُبْغِضَ فِي اللَّهِ وَتُعْمِلَ لِسَانَكَ فِي ذِكْرِ اللَّهِ قَالَ وَمَاذَا يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ وَأَنْ تُحِبَّ لِلنَّاسِ مَا تُحِبُّ لِنَفْسِكَ وَتَكْرَهَ لَهُمْ مَا تَكْرَهُ لِنَفْسِكَ وَأَنْ تَقُولَ خَيْرًا أَوْ تَصْمُتَ

21267 مسند أحمد مسند الأنصار رضي الله عنه

Send as a message
Share on my page
Share in the group