Translation is not possible.

ያለህ ነገር ...ሀብት ...ዕውቀት ...ስልጣን ...ባንተ ብልሃት፣ባንተ ብልጠት ፣ባንተ አቅም ሳይሆን በአላህ ችሮታ መሆኑን አትዘንጋ !...ያላቸው ነገር የተሰጣቸው እነሱ ባለመብት በመሆናቸው እንደሆነ የተሰማቸው ሰዎች ሲጠፉ አይተናል ...ሂጃብ የለበሰች ሴት ሂጃቡን የለበሰችው እሷ ተገቢ ስለሆነች እንደሆነ አስባ ተኩራርታ ያለበሱትን ስትንቅ በተቃራኒው አድርጎ ያለበሱትን አልብሶ እሷ አውልቃ አይተናል ...መስጂድ በመመላለሱ ሶላት በመስገዱ ባልሰገዱት ላይ ሲኩራራ እሱ ከጀመዓም ከጁመዓም ቀርቶ በነሱ ላይ ሲኩራራባቸው የነበሩት በቦታው ተተክተው የመስጂድ ቤተሰብ የሆኑበትን አጋጣሚ አይተናል...መልካም ነገር ሲደረግልህ ያ ጉዳይ የተደረገልህ ተገቢ ስለሆንክ ያልተደረገላቸው ሰዎች ደግሞ ብልጠት ስለጎደላቸው እንዳይመስልህ አላህ ነው ሁሉን ያደረገው እንደኛ ቢሆንማ...

★ወንጀል ላይ በወደቀ ሰው አትሳለቅ ..በከሰረ ሰው አታሹፍ... በተፈተነ ሰው ላይ አትኩራራ... ምናልባት ያጋጠማቸው ነገር አንተን ቢያጋጥምህ ልትብስ ትችላለህ ...ሁሉም የአላህ ችሮታ ነው በብልጠትህ አይደለም !

አብሽር የኔ መልካም ❤

Send as a message
Share on my page
Share in the group