ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ቢያያት ኖሮ መነሻው እርሱ ዘንድ መድረሻው ፍልስጤም የሆነን ሠራዊት አሰልፎ ጽዮናውያንን ከምድረ-ገጽ ባጠፋቸው ነበር።
ሠይፉላሂል መስሉል ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ በህይወት ቢኖር ሰማንያ ሰይፍ እጁ ላይ በተሰበረ ልቡም ሳይቀዘቅዝ ጠላትን አንቀጥቅጦ ምሽጋቸውን ባፈራረሰ።
ጀግናው ሰላሐዲን ቢያያት ኖሮ ከጦርነቱ በፊት መቀበርያ ጉድጓዳቸውን በገዛ እጃቸው ባስቆፈራቸው።
የዘመኔ ባለስልጣናትና ነገስታት አይተዋታል። አሊሙም ሊቃውንቱም ተመልክተዋታል። ከውግዘት ፈትዋ በቀር ግን ምንም አላየንም።
እንደው አላህን እንዴት ትገናኙት ይሆን?!
መልሳችሁስ ምን ይሆን?!
ሰጊረቲን ቅበሯት... በእኔው ዑማ ላይም ሰላተል ጀናዛ ስገዱበት