UMMA TOKEN INVESTOR

About me

ይህ አካውንት ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼

Translation is not possible.

✍መገንዘብ ለሚችል…………

"አኼራ እንዳለብህ እያመንክ የማትዘጋጅላት ከሆንክ: ይህ ትልቅ የሆነ ቂልነትህ ነው ሚያሳየው።

አንተ እኮ "ሁለት በአንድ ሽጥ" ብትባል እሺ ብለህ አትስማማም።

ታዲያ…………

ማብቂያ የሌለው አኼራ እንዴት በጥቂት የዱንያ ቀናቶች ትሸጠዋለህ??"

/إمام ابن تيمية

في شرح العقيدة الأصفهانية ص١٦٧/

https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

✍በሕይወትህ ላይ የምትፈልገውን ለውጥ ለማምጣት ከውሳኔ በኋላ የምትወስደው የመጀመሪያው እርምጃ;

ነባሮቹን ትተህ ለለውጥህ አጋዥ የሚሆኑ ባልደረባዎች መምረጥ ወይም መያዝ ነው።

አልሰማህም እንዴ?………

ያ ከዘጠና ዘጠኝ በኋላ አንድ ጨምሮ መቶ ነፍስ የረሸነው ገዳይ; ተፀፅቶ ወደ አላህ ለመመለስ ሲወስን የተመከረው ትልቁ ምክር:

"የሀገርህ ህዝቦች ክፉ ስለሆኑ ሀገር ቀይር" ነበር።

ሂጅራ የተደነገገውም ለዚሁ አላማ ነው………

ሀገሪቷ ክፉ ስለሆነች ሳይሆን በሀገሪቷ የሚኖሩ ህዝቦች ብልሹ ሲሆኑ ሰዎቹን ለመራቅ ሀገሪቷን ትተህ ትሰደዳለህ።

👆ይህንን ማድረግ ካልቻልክ መለወጥ አትችልም

https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

✍️ ሁለት የቢድዐ ከባድ አደጋዎች

⚫️አንደኛው;

🔥የአላህ ንግግር ማስዋሸት ነው‼️

አላህ በተከበረው ቃሉ

{الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ}

{በዛሬው ዕለት ዲናችሁን ሞላሁላችሁ}

ብሎ ይህ እስልምና ምንም ዐይነት ጉድለት የሌለበት ሀይማኖት እንደሆነ ይነግረናል።

ዛሬ አንድ ሰው ተነስቶ………

“ይህ ነገር እስልምና ውስጥ ቢጨመር ጠቀሜታ ይኖረዋል።”

ብሎ አዲስ ነገር ከፈጠረ ይህ ሰው በምላሱ ባይናገረውም በተግባሩ;

“አላህ ሙሉ ነው ያለን ዲን ሙሉ ሳይሆን ነው።”

የሚል መልእክት ይሰጠናል።

⚫️ሁለተኛው;

🔥የአላህ መልእክተኛ ﷺን መተቸት ነው‼️

አንድ ሰው እስልምና ውስጥ የአላህ መልእክተኛﷺ ያልሰሩት የሆነ ነገር………

“ይህ ነገር ለእስልምና ይጠቅማል።”

ብሎ ቢሰራ በንግግሩ ባይናገረውም በተግባሩ;

“የአላህ መልእክተኛﷺ ዲኑን ጨርሰው አላስተላለፉም።” የሚል ክፉ ግንዛቤ ይሰጣል።

እነዚህ ሁለት ነጥቦች አንድ ሰው አንድ ቢድዐ በመስራቱ የሚወድቅባቸው የከፉ አደጋዎች ናቸው። ቢድዐ ላይ የወደቀ ሰው እነዚህ ነጥቦች ተብራርተውለት "አዎን!" ብሎ ካረጋገጠ ቁርኣን በማስተባበሉና ነብዩﷺን በጉድለት በመተቸቱ ከእስልምና ይወጣል።

ስለሆነም;

የሸዋል ዒድም በለው ቲንሹ ዒድ ከሚለው ጀምሮ አጠቃላይ የቢድዐ ባንዲራ ተሸካሚ ይህንን ቆም ብሎ ሊያይ ይገባዋል!!

👇 👇 👇 👇

ወደ ኸይር ያመላከተ የሰሪው ምንዳ ያገኛል

👆 👆 👆 👆

https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

✍አላህ ደንግጎታል ሸሪዐችን ሞልቶ

ለሸዋል ጾም እንጂ ዒድ የለውም ከቶ!!

ፈርድና ሱናውን ጾመህ ስታበቃ

ቢድዐ ማስከተሉ ጥፋት ነው ዐለቃ!!

ያዘዘህ ሰርተሃል እሱ ይበቃሃል

ቢድዐ ብታስከትል ሁሉም ያከስርሃል!!

:

:

ትርፉ ኪሳራ ነው አዳዲስ ፈጠራ

በሱና ተብቃቅተህ የታዘዝከው ስራ!!

https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

📖{وَمِنْهُم مَّن يَقُولُ رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ}

በሚለው {فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً} ማለት "ሷሊሕ የሆነች ሚስት ናት" ብለው የፈሰሩት ለምን በዚህ እንደ ፈሰሩት የሚገባህ;

እንደዛ ዐይነት ሕይወት አላህ ሲወፍቅህ ነው።

የዛኔ………

{رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَاجِنَا وَذُرِّيَّاتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ وَاجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَامًا}

ወደ ሚለው ዱዐ ትሸጋገራለህ።

🤲አላህ ለሁላችን ይወፍቀን🤲