Translation is not possible.

📖 ከቁርኣን ተኣምራት…………

የሙእሚን ነፍስ ስትወጣ ለምን:

{ወደ ጌታሽ ተመለሺ} እንጂ ወደ "ጌታሽ ሂጂ" አትባልም?

የመሄድ እና የመመለስ ልዩነታቸው ምንድን ነው?

መሄድ ማለት………

መዘውተሪያ ከሆነው ቦታ ጊዜያዊ ወደሆነው ቦታ የሚደረግ ጉዞ ሲሆን

መመለስ ማለት………

ጊዜያዊ ከሆነው ቦታ መዘውተሪያ ወደሆነው ቦታ የሚደረግ ጉዞ ነው።

ለምሳሌ፦

"ወደ ሱቅ ሄጃለሁ", "ወደ ቤት ተመልሻለሁ" ትላለህ።

ግን

"ወደ ሱቅ ተመልሻለሁ", "ወደ ቤት ሄጃለሁ" አትልም።

ለዚህም ነው ነብዩላህ ሱለይማንﷺ መልእክተኛውን በላከ ጊዜ እንዲህ ያለው፦

📖{اذْهَب بِّكِتَابِي هَذَا فَأَلْقِهْ إِلَيْهِمْ}

{ይህንን ደብዳቤዬ ይዘህ ሂድ: ወደ እነርሱም ጣለው።}

[አል_ነምል:28]

ከንግስቷ ወደ ሱለይማን ተልኮ ለነበረው መልእክተኛ ሲመልስ ግን እንዲህ አለው፦

📖{ارْجِعْ إِلَيْهِمْ}

{ወደ እነርሱ ተመለስ።}

[አል_ነምል:37]

ስለሆነም አንድ ሙእሚን በሚሞት ጊዜ አላህ ለነፍሱ

📖{ارْجِعِي إِلَى رَبِّكِ رَاضِيَةً مَّرْضِيَّةً}

{ወዳጅም ተወዳጅም ሆነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ።} ይላታል

[አል_ፈጅር:28]

{ወደ ጌታሽ ተመለሺ} እንጅ "ወደ ጌታሽ ሂጂ" አይላትም።

ምክንያቱም፦ ዱንያ ለአንድ ሙእሚን ጊዜያዊ መቆያው እንጅ ዘላለም መዘውተሪያው አይደለችም።

ዘላለም መዘውተሪያ አላህ ዘንድ ያለው አኼራ ላይ ብቻ ነው። አላህ በሌላ ቦታ እንደገለፀው፦

📖{وَاتَّقُوا يَوْمًا تُرْجَعُونَ فِيهِ إِلَى اللَّهِ}

{በእሱ ውስጥ ወደ አላህ የምትመለሱበተን ቀን ተጠንቀቁ።}

[አል_በቀራ:281]

እዚህ ቦታም ላይ {ወደ አላህ የምትመለሱበት} እንጅ "የምትሄዱበት" አላለም።

ምክንያቱም፦

መዘውተሪያችን አኼራ ሲሆን: እቺ ዱንያ ግን ጊዜያዊ መቆያ ብቻ ናት።

📖ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇

https://t.me/hamdquante

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group