Translation is not possible.

✍መሄጃችን ደርሷል ተቃርቧል ቀጠሮ

ከገመዱ ጫፍ ነን ይታያል ቋጠሮ።

ሁሉም ይጓዛታል ያቺ የሩቅ ጉዞ

የሌለው ባዶውን ያለው ስንቁን ይዞ።

ሁሉንም ይሄዳል የለም እዚህ ቀሪ

ተጓዥ ቢሆን እንጂ አታይም ዘውታሪ።

አናቀውም እንጅ የመሄጃችን ቀን

ጥርጥር የለውም ይመጣል 1ቀን።

ይመጣል 1ቀን እያልን ኖረናል

መኖሩ ጨርሰን ለመሄድ ቀርበናል።

ተዘጋጅተናል ወይ ወይስ ይቀረናል

መልካም ወይስ ክፉ የቱ አብዝተናል?

ሰው ይዞ ሲመጣ የሰራውን ስራ

መልካሙን ለማጨድ ከመልካሙ ዝራ።

ከመልካም የሰራ ውስጡን አሳምሮ

ነገ ለመደሰት ዛሬ ተቸግሮ፤

ያገኛል ምንዳውን በዝቶ ተባዝቶለት

ይሆናል ማረፍያው ዘላለም በጀነት!!

ከዚህ ሌላ ሆኖ ስራው ካላማረ

ነፍሲያው ሲታዘዝ በወንጀል የኖረ፤

ስራውን ያገኛል ማግኘት ባይፈልግም

ከዝያም ወደ እሳት መሄድ ባይፈልግም።

🖊ሐምዱ ቋንጤ

ከፉርቃን ሰማይ ስር!!

https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Send as a message
Share on my page
Share in the group