እናትና ልጅ በጠባቧ ክፍላቸው ውስጥ ተቀምጠዋል።
"እማ ርቦኛል" አለ ዩሱፍ ሆዱን እያሻሸ።
"ሀቢቢ ትንሽ ጠብቀኝ ቲማቲም ስልስ እሰራልሃለሁ" አለች እናት ፀጉሩን እያሻሸች።
ቤት ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ ባለመኖሩ የዩሱፍን ርሐብ ለማስታገስ ሁለት የቲማቲም ዘለላዎችን ፍለጋ ከቤት ወጣሁ። በበር በኩል አጮለቅኩና እስክመለስ በሩን እንዲዘጋ ነገርኩትና ወደ ጎረቤታችን ቤት አቀናሁ። ደጋግሜ አንኳኳሁ። መልስ የሚሰጠኝ አላገኘሁም። ከመንገዱ ማዶ ወደሚገኘው ወደ ኡሙ ሚቅዳድ ቤት አመራሁ።
አንኳኩቼ ገባሁ። እንዴት ነሽ ልጆችሽስ ብዬ ሰላምታን አቀረብኩላት።
"አልሀምዱሊላህ ደህና ነን አላህ ይጠብቀን" ብላ መለሰችልኝ።
እያንዳንዱ ሰከንድ የመጨረሻ ሊሆን ይችላልና እኛ ፍልስጤማዊያን ጦርነት ውስጥ ስንሆን እንዲህ ነን ብዙ አንናገርም።
"ባለቤቴ ውሎ አዳሩ ሆስፒታል ሆኗል። ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወደ ቤት አልተመለሰም። አልሐምዱሊላህ" አልኩና ቲማቲም ካላት እንድትሰጠኝ ጠየቅኳት። በፌስታል ቋጥራ ያቀበለችኝን ቲማቲም ይዤ ልወጣ ስል "ሁኔታዎች ከባድ ሆነዋል በዱዓ እንተዋወስ" አለችኝ።
"በአላህ እርዳታ ይህ ሁሉ ያልፋል ኢንሻ አላህ..." እያልኳት ገና ንግግሬን ሳልጨርስ ከባድ ፍንዳታ ተሰማ። በጥቁር ደመና አየሩን ተሸፈነ። አካባቢው በአቧራ ተሞላ። አእምሮዬ የዩሱፍን ስም አቃጨለ። ከራሴ ጋር እየታገልኩ ወደ ጎዳናው ሮጥኩ። ሁሉም ይጮኻል።
ዩሱፍን አይታችዋል..? እዚህ አካባቢ አንድ ትንሽ ፍሪዝ የሆነ ልጅ አጊኝታችኋል? እያልኩ ጮኽኩ። መልስ የሰጠኝ ማንም አልነበረም። በአንቡላንስ ተጭኜ ሄድኩ። የመኪናው በር ሲዘጋ በዩሱፍ ላይ የዘጋሁት በር ታወሰኝ።
እየተብሰለሰልኩ አሽ-ሺፋእ ሆስፒታል ደረስኩ። ዩሱፍ....የሱፍ.... ብዬ ተጣራሁ። ለአላፊ አግዳሚው የ7 አመት ቆንጅዬ ልጄን አይታቹታልን? እያልኩ ጠየቅኩ።
የዓይኔ ማረፍያ ባለጥቅልል ፀጉሩ ጥቃቱ ፊቱን ከማበላሸቱ በፊት ቆንጆ ምስሉን በአእምሮዬ ሳልኩ። ፍርስራሽ አቧራ ከሰውነቱ ጋር ተጣብቆ በደም ተጨማልቆ አልጋ ላይ ተንጋሎ አገኘሁት። ዩሱፍ በባዶ ሆዱ ጌታውን ተገናኘ።
Mahi mahisho
https://ummalife.com/mahimahisho