UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.
ምን ቢበዛብህም የችግር መከራ:
ባንተ ላይ ቢዘንብም ባንተም ቢያባራ:
በትግስት ጠብቅ የፀሀዩዋን ጮራ:
ምንም ብትዘገይ አትቀር ተቀርቅራ።
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
የተውበት ኡኡታ
እኔስ ዋይ ጥፋቴ:
አቤት ሞኝነቴ:
ላጠፋ ደረስኩኝ የ²ሀገር ቤቴ:
አስቤ አልሜ የአፍታ ስሜቴ:
አላህን ረስቼ እንዲው መዋተቴ:
በሀራሙ ደስታ እራሴን መሳቴ:
ኧረ ምን ይዋጠኝ እንደው ምን ውስጥ ልግባ:
እተዋለሁ ብዬ ቃል እንኳን ብገባ:
ነገ እረሳዋለሁ በስሜት ስገባ:
ለነፍሴ ፈራሁኝ እሳት እንዳልገባ:
ብሄድ በዚ ሁኔታ  ምን ይለኛል ጌታ:
እኔስ አፍሪያለሁ መቅረብ እዛ ቦታ:
ምን ማረግ ቢያቅተኝ ሀሳቤም ቢምታታ:
አንድ ሀሳብ አለኝ ማይነፈግ ቦታ:
መመለስ ወደሱ ወደ አንዱ ጌታ:
አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው በአንድምታ:
ጌታዬዋ ስማኝ የተውበት ኡኡታ:
አማራጭ የላቸው ተሳሳቾች ሁላ:
ወንጀላቸው በዝቶ ምን ባህር ቢሞላ:
ከተውበቱ ውጪ አንድም የለው መላ:
ላይመለስበት ቃል ገብቶ መሀላ።
✍ሰዑድ ጀማል
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
እኔ እሆን ምክንያቱ⁉️
ለቤትህ መደፈር ክብር መነካቱ:
ንግግርህ ወድቆ መሬት መታየቱ:
ሰጋጁ ከሱጁድ ቀብር መሸኘቱ:
ለሰላቱ ወጥቶ ተቀጥፎ መቅረቱ:
የኔ ወንጀል ይሆን ለሁሉ ምክንያቱ?
ስንቱን መዳፈሬ በሌት በጠዋቱ:
ማታየኝ ይመስል ዘንግቼ ተውበቱ:
ከሆነ ታረቀኝ አታድርገኝ ከንቱ:
አጥራኝ ጌታዬዋ ሳይደርስብኝ ሞቱ:
ጠግነው ጀባሩ ቀልቤን ስብራቱ።
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
"እኔን ለኔ ተውኝ"
ምገባው በቀብሬ:
ከስራዬ አብሬ:
አይደል ተጨምሬ:
ከሰዎች አብሬ:
 
ደግሞም ስቀሰቀስ:
ወደ መህሸር ስፈልስ:
ከጌታም ስከሰስ:
ለክሱም ስመልስ:
ከዚያም ስመነዳ:
ሲደርስም አጨዳ:
ወይ ከጀነት ጓዳ:
ወይ የጀሂም እዳ:
ይሄ እየጠበቀኝ:
በሰው ምን ጠመደኝ:
ለሰዎቹ ይብላኝ:
ቢዚ ለሆኑልኝ:
Plese ሰዎች ስሙኝ:
እኔን ለኔ ተውኝ።
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
የጋዛ እናት ከመንደሯ አቅራቢያ የአየር ድብደባ ሲጀመር ሁሉንም ነገር ትታ ወጣች ........ ቁርአኗን ሲቀር
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group