UMMA TOKEN INVESTOR

zeyniya Jemal shared a

🥀ነጋ አልሃምዱላህ ፈጅር ሰላት 🥀

ከሳሊሆች አንዱ ነውና ሁሌ ከአዛን በፊት ወደ መስጅድ ለምን ትሄዳለክ ተብሎ ተጠየቀና እንዲህ ብሎ መለሰ

«አዛን'ኮ ዝንጉዎችን ለማስታወስ ነው ከእነርሱ እንዳልሆን እፈልጋለሁ

🥀አሏህ ሆይ! ከሰጋጆች አድርገን 🥀

ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል

አንድ ባሪያ ወደ ሶላት መቆምን ባሰበ ግዜ

ወንጀሉ ሁሉ ትመጣና ጫንቃው ላይ ትደረጋለች

ባጎነበሰ(ሩኩእ) እና ወይን በተደፋ(ሱጁድ) ግዜ ከአርሱ (ወንጀሉ)ትረግፋለች።

📚አልባኒ ሶሂህ ብለውታል

⁉️ትተኛላችሁ ወይስ ትሰግዳላችሁ ከየትኛው ናቹ 🥀ከሰጋጆች ወይስ እንቅልፍ ካሸነፋቸው እራሳችንን እንፈትሽ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እድሜህን በጭንቀት፣ በሀዘንና በትካዜ አትጨርስ። በረባ ባረባው በትንሽ በትልቁ እየተብሰለሰልክ ውስጥህን አትጉዳ። ከዛም አልፎ ለስኳር፣ ለደም ግፊትና ለሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች እራስህን አታጋልጥ። የሚያስከፋ የሚያሳዝንና ደስ የማይል ነገር ቢገጥምህ ቀልብህ ላይ ቋጥረህ ይዘህ ነፍስህን አታጨስጨንቅ። ዱንያ አጭር ናት ቢደላህም ቢከፋህ ታልፋለች። ዘውታሪነት ለአላህ እንጂ ለማንም የለም። ስታገኝ አመስጋኝ ስታጣ ታጋሽ ውድ የአላህ ባሪያ ሁን። ከዛ በዘለለ ለዱንያ ብዙም ቦታ አትስጥ። እንደሚታወቀው  ከሀዘን በኋላ ደስታ ከማጣት በኋላ ማግኘት እንዳለ ሆኖ የዱንያ መከራና ስቃይ የፈለገ ቢገዝፍና ቢበረታ በሶብርና በፅናት ትሻገረዋለህ። እጅግ ከከፋም በሞት ትገላገለዋለህ። ነገራቶች ሲስተካከሉልህ፣ ያሰብከው ሲሳካና ህልምህን እውን ሲሆን እንደምትደሰተው ሁሉ ነገራቶች በተቃራኒ ሲሆኑብህ የአላህ ውሳኔ ነውና ወደህ ተቀበል። ሲሳካለትና ሲያገኝ የሚደሰት ሲያጣና ሲቸገር የሚማረር ጥቅሙን ብቻ የሚያሳድድ ራስ ወዳድ አትሁን። ነገራቶችን ቀለል አድርገህ ኑር። የሁል ጊዜ ሀሳብና ጭንቅህ ከሞት በኋላ ስላለው ለዘልአለማዊ ህይወትህ ይሁን። ከዱንያው ይልቅ ለአሄራው ቤትህ አብዝተህ ልፋ። በትነሽ ትልቁ አትማረር። በዱንያ ላይ ስትኖር የበታችህን እንጂ የበላይህን አትመልከት። የሌሎችን እያየህ እራስህን በቅናት አትግደል። በአላህ ካመንክና በሱ ላይ ትክክለኛ መመካትን ከተመካህ በማጣት ውስጥ ሆነህ ማግኘትን ታያለህ። በችግር ውስጥ ሆነህ ደስታን ታጣጥማለህ።

🛑👉ዱንያ በባህሪዋ አጭርና ጠባብ ናት የባሰ ደግሞ አንተ አታጥባት። ሲጀመር ዱንያ የተፈጠረው ላንተ እንጂ አንተ ለሷ አይደለም። ነግደህ ስላላተረፍክ አትበሳጭ። ከትምህርት ስለወደቅክ የህይወትህ መጨረሻ አድርገህ አትመልከት። ህይወትህ ሊለውጡ የሚችሉ ከዛ ውጪ ሌሎች ብዙ አማራጮች አሉህ። አንዱ ካልተሳካልህ የግብህ መጨረሻ ያ አታድርግ። በጌታህ ታግዘህ ነገራቶችን ቀያይረህ ሞክር። እንደ ጋሪ ወደ አንድ አቅጣጫ ወደፊት ብቻ አትመልከት። በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ። ተስፋ መቁረጥ የስኬት ግርዶሽ ነው። ማወቅ ያለብህ ያንተ ጥረትና ልፋት ሰበብ እንጂ ሌላ አይደለም። ሰጭውና ከልካዩ የበላይና የበታች አድራጊው አላህ ነው። ስለዚህ ሁሌም አመስጋኝ፣ ታጋሽ፣ ታታሪ፣ ጠንካራና ማራል ያለው ጀግና ሁን። ባጣኸው ነገር ውስጥ ሊደርስብህ የነበረ መጥፎ ነገር ስለማታውቅ ለምን አጣሁት ብለህ ችክ አትበል።

🛑👉ሁሌም ደስተኛ ሁን። ለሀዘን ለትካዜ በር አትክፈት። ደስታን ለማግኘት እሩቅ አትሂድ እጅግ በጣም ቀላል ነው። በአላህ ማመን እሱን በብቸኝነት መገዛትና መልካም መስራት ብቻ ነው የሚጠበቅብህ። ይህ ካደረግክ አላህ በዱንያም በአሄራ ደስተኛ ህይወት ሊያኖርህ ቃል ገብቷልና።

مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
zeyniya Jemal Changed her profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
zeyniya Jemal Changed her profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
zeyniya Jemal shared a
Translation is not possible.

አላህ ሆይ! የፈለስጢን ሙስሊሞችን እርዳቸው፤ በጠላቶቻቸው ላይ ዲልን አቀዳጃቸው። ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቃቸው።

#islam #gaza #quran #islamedia #إسلاميواليت

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group