Translation is not possible.

"እኔን ለኔ ተውኝ"

ምገባው በቀብሬ:

ከስራዬ አብሬ:

አይደል ተጨምሬ:

ከሰዎች አብሬ:

 

ደግሞም ስቀሰቀስ:

ወደ መህሸር ስፈልስ:

ከጌታም ስከሰስ:

ለክሱም ስመልስ:

ከዚያም ስመነዳ:

ሲደርስም አጨዳ:

ወይ ከጀነት ጓዳ:

ወይ የጀሂም እዳ:

ይሄ እየጠበቀኝ:

በሰው ምን ጠመደኝ:

ለሰዎቹ ይብላኝ:

ቢዚ ለሆኑልኝ:

Plese ሰዎች ስሙኝ:

እኔን ለኔ ተውኝ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group