UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1

የልደታ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የክፍለ ከተማውን የሙስሊም ወጣቶች ሊግ ይፋዊ የምስረታ እና የትውውቅ መርሀግብር ተካሄደ!

...

(ሀሩን ሚዲያ ፦ታህሳስ 06/2016)

...

የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ካደረጋቸው የመዋቅር ዝርጋታ መካከል የሙስሊም ወጣቶች ሊግ አንዱ ነው።በዚህ መሰረት የተለያዩ ክፍለ ከተሞች የሙስሊም ወጣቶች ሊግ ምስረታ ያደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለት ታህሳስ 06/2016 በኡማ ሆቴል የልደታ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች የሙስሊም ወጣቶች ሊግ ይፋዊ የምስረታ እና የትውውቅ መርሀግብር ተካሂዷል።

...

በመርሃግብሩ ላይ የአዲስአበባ መጅሊስ ፕሬዚዳንት ሼኽ ሱልጣን አማን ም/ል ፕሬዚዳንቱ ሼኽ ፈቱድን ሀጅ ዘይኑ ሙቅና ዋና ፀሀፊው ሼኽ ሁሴን በሽር የአዲስአበባ መጅሊስ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሊድ ሙሀመድ የክፍለ ከተሞች ህብረት ዋና ሰብሳቢ ኡስታዝ ሀሺም ሽፋ የልደታ ክፍለ ከተማ መጅሊስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኡስታዝ ሚስማህ ወርቁ በመድረኩ ላይ በመገኘት የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

...

በልደታ ክፍለ ከተማ መጅሊስ ከእስሩም ወረዳዎች የተመረጡት የሙስሊም ወጣቶች ሊግ አባላት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በቅንነት እና በኢኽላስ ለማገልገል በአዲስአበባ መጅሊስ ዋና ፀሀፊ ሼኽ ሁሴን በሽር አማካኝነት ቃለመሃላ ፈፅመዋል።

...

ወጣቶች በኢስላም ያላቸውን ቦታ በተመለከተ በሼኽ አብዱሰላም ዝግጅት የቀረበ ሲሆን ኡስታዝ ነስሩ ኸድር ደግሞ "የመደራጀት ጥቅምን" አስመልክቶ በመድረኩ ዝግጅቱን አቅርቧል።

...

በመጨረሻም በልደታ ክፍለ ከተማ መጅሊስ ስር የሚገኙና ጥሩ አፈፃፀም ለነበራቸው መስጅዶች የወረዳ መጅሶች እና ተቋማት የዕውቀትና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

...

©ሀሩን ሚዲያ

image
image
image
image
image
image
+3
Send as a message
Share on my page
Share in the group

የሀጅ ሙሃመድ ሳኒ ሀቢብ የእውቀት ማእከል ዲዛይን

በትላንትናው እለት ይፋ የተደረገው በለሚ ኩራ ክፍለከተማ በአራት ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈው የሐጅ ሙሃመድ ሳኒ ሀቢብ የእውቀት ማእከል ዲዛይን ቪዲዮ ይኼን ይመስላል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በአራት ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈውን ማእከል በሃላፊነት እንዲያስገነቡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሱልጧን ሀጅ አማን ኤባ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ አስረክበዋል።

አላሁ አክበር!

ሀጅ ሙሃመድ ሳኒ ሀቢብ የመጅሊስ መስራችና የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማምና ኻጢብ ብቻ አልነበሩም። ሀጅ ሙሃመድ ሳኒ ሀቢብ በጨለማው ዘመን እኩልነት በማይታሰብበት ኢፍትሀዊነት እንደ ፍትሀዊነት በሚቆጠርበት በዛ ዘመን እንደ ሻማ እየቀለጡ ለዑማው ብርሐን ለመሆን የለፉ ጭምር ነበሩ ።

ሀጅ ሙሃመድ ሳኒ ሀቢብ ከትልቅ መራር እውነት ጋር እየታገሉ አላህ በሰጣቸው ሰብር ብዙ መከራዎችን ያለፉ የገዛ ወንድ ልጃቸውን ጭምር በሸሂድነት የተነጠቁ ጭምር ሲሆኑ ምንም የሞራል ስብራት ሳይገጥማቸው ለህልማቸው ኖሮው ያለፉ ትልቅ ሼይኽ ነበሩ ።

┉✽̶»̶̥ አላህ የጀነት ያድርጋቸው »̶̥✽̶┉

image
image
image
image
image
image
+1
Send as a message
Share on my page
Share in the group

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገኙበት ታላቅ

የሰላምና የምስጋና ኮንፈረስ በድምቀት ተጠናቀቀ!

ህዳር 25/2016

"ቀጣይ ምዕራፍ ለሁለንተናዊ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አዘጋጅነት ታላቅ የሰላምና የምስጋና ኮንፈረንስ በሚኒሊየም አዳራሽ ተካሄድዋል።

በሰላምና የምስጋና ኮንፈረንሱ ላይ የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንትን ጨምሮ፣የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣የክልል መጅሊስ አመራሮች፣ኡለማዎች፣ዱአቶች፣ኡስታዞች፣ የአ/አ መስተዳደር ከንቲባ አምባሰደሮች የዳስፖራ አባላት እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት ተካሄድዎል።

በሰላም በኮንፍረንሱ ላይ የምስጋና ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን ለኢ/እ/ጉ/ጠ/ቤት ፕሬዝዳንት ለሼህ ሀጂ ኢብራኢም ቱፋ፣ ለኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ለአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አበቤ የምስጋና ሽልማት ተበርክቷል።

በዚህ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ በለሚኩራ ክፍለከተማ የተሰጠው የአራት ሺህ ካሬ የመስጂድ ቦታ በሀጅ መሀመድ ሳኒ ሀቢብ እንደሚሰየምም ተገልፅዋል።

በዝግጅቱ ማጠቃለያ ላይ ቀጣይ የምስጋናና የሰላም ኮንፍረንስ እንደሚቀጥል የተገለፀ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በጅማ ከተማ ለማካሄድ የኦሮሞያ መጅሊስ አደራውን ተቀብሏል።

©ሀሩን ሚድያ

image
image
image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group

ሁሉን ቻይ የሆንከው ጌታችን ሆይ

ዝምታህ አለመቻልህ መስሏቸው ድንበር

እያለፏ ነው እና ችሎታህን አሳያቸው!

اللهم أرنا فيهم عجائب قدرتك

وعظيم عدلك وغضب انتقامك

وشدة عذابك فإنهم لا يعجزونك

#ياقادر

#يا الله

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group

የመን ይፋዊ በሆነ መልኩ እስራኤል ጋር ጦርነት ያወጀች የመጀመሪያዋ ሀገር ሁናለች

...

ሀሩን ሚዲያ፥ ጥቅምት 20/2016

...

የየመን ታጣቂ ሃይሎች ሚሳኤሎችን እና ዩኤቪዎችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፋቸውን ተናግረዋል።

...

“የእኛ የታጠቁ ሃይሎች በእስራኤል የተለያዩ ኢላማዎች ላይ እጅግ ከባድ የሚባሉ የባለስቲክ እና የክሩዝ ሚሳኤሎችን እንዲሁም በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አስወነጭፈናል" ሲል ገልጿል። ከነዚህ ውስጥ ረጅም ርቀት የሚጓዙ ሚሳኤሎች የእስራኤል የኒውክለር ማብላያን ኢላማ ያደረጉ ጭምር ነበሩ ተብሏል።

...

የየመን ጦር ሃይሎች ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ያህያ ሳሪ የእስራኤል ጥቃት እስኪቆም ድረስ ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም የተሻሉ ጥቃቶችን ማድረሳችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

...

© ሀሩን ሚዲያ

___________

በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia

በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group