በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገኙበት ታላቅ

የሰላምና የምስጋና ኮንፈረስ በድምቀት ተጠናቀቀ!

ህዳር 25/2016

"ቀጣይ ምዕራፍ ለሁለንተናዊ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አዘጋጅነት ታላቅ የሰላምና የምስጋና ኮንፈረንስ በሚኒሊየም አዳራሽ ተካሄድዋል።

በሰላምና የምስጋና ኮንፈረንሱ ላይ የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንትን ጨምሮ፣የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣የክልል መጅሊስ አመራሮች፣ኡለማዎች፣ዱአቶች፣ኡስታዞች፣ የአ/አ መስተዳደር ከንቲባ አምባሰደሮች የዳስፖራ አባላት እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት ተካሄድዎል።

በሰላም በኮንፍረንሱ ላይ የምስጋና ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን ለኢ/እ/ጉ/ጠ/ቤት ፕሬዝዳንት ለሼህ ሀጂ ኢብራኢም ቱፋ፣ ለኢትዮጲያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ለአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አበቤ የምስጋና ሽልማት ተበርክቷል።

በዚህ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ በለሚኩራ ክፍለከተማ የተሰጠው የአራት ሺህ ካሬ የመስጂድ ቦታ በሀጅ መሀመድ ሳኒ ሀቢብ እንደሚሰየምም ተገልፅዋል።

በዝግጅቱ ማጠቃለያ ላይ ቀጣይ የምስጋናና የሰላም ኮንፍረንስ እንደሚቀጥል የተገለፀ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በጅማ ከተማ ለማካሄድ የኦሮሞያ መጅሊስ አደራውን ተቀብሏል።

©ሀሩን ሚድያ

image
image
image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group