የልደታ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የክፍለ ከተማውን የሙስሊም ወጣቶች ሊግ ይፋዊ የምስረታ እና የትውውቅ መርሀግብር ተካሄደ!

...

(ሀሩን ሚዲያ ፦ታህሳስ 06/2016)

...

የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ካደረጋቸው የመዋቅር ዝርጋታ መካከል የሙስሊም ወጣቶች ሊግ አንዱ ነው።በዚህ መሰረት የተለያዩ ክፍለ ከተሞች የሙስሊም ወጣቶች ሊግ ምስረታ ያደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለት ታህሳስ 06/2016 በኡማ ሆቴል የልደታ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች የሙስሊም ወጣቶች ሊግ ይፋዊ የምስረታ እና የትውውቅ መርሀግብር ተካሂዷል።

...

በመርሃግብሩ ላይ የአዲስአበባ መጅሊስ ፕሬዚዳንት ሼኽ ሱልጣን አማን ም/ል ፕሬዚዳንቱ ሼኽ ፈቱድን ሀጅ ዘይኑ ሙቅና ዋና ፀሀፊው ሼኽ ሁሴን በሽር የአዲስአበባ መጅሊስ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሊድ ሙሀመድ የክፍለ ከተሞች ህብረት ዋና ሰብሳቢ ኡስታዝ ሀሺም ሽፋ የልደታ ክፍለ ከተማ መጅሊስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኡስታዝ ሚስማህ ወርቁ በመድረኩ ላይ በመገኘት የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

...

በልደታ ክፍለ ከተማ መጅሊስ ከእስሩም ወረዳዎች የተመረጡት የሙስሊም ወጣቶች ሊግ አባላት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በቅንነት እና በኢኽላስ ለማገልገል በአዲስአበባ መጅሊስ ዋና ፀሀፊ ሼኽ ሁሴን በሽር አማካኝነት ቃለመሃላ ፈፅመዋል።

...

ወጣቶች በኢስላም ያላቸውን ቦታ በተመለከተ በሼኽ አብዱሰላም ዝግጅት የቀረበ ሲሆን ኡስታዝ ነስሩ ኸድር ደግሞ "የመደራጀት ጥቅምን" አስመልክቶ በመድረኩ ዝግጅቱን አቅርቧል።

...

በመጨረሻም በልደታ ክፍለ ከተማ መጅሊስ ስር የሚገኙና ጥሩ አፈፃፀም ለነበራቸው መስጅዶች የወረዳ መጅሶች እና ተቋማት የዕውቀትና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

...

©ሀሩን ሚዲያ

image
image
image
image
image
image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group