UMMA TOKEN INVESTOR

7 month Translate
Translation is not possible.

.

.

ለእውነት ለመቆም ሀይማኖቱ ያላገደው የእምነት አባት

.

ሂላሪዮን ካፑቺ የተወለደው ሶሪያ በፈረንሳይ ኮሎኒ ስር ባለችበት የአሌፖ ከተማ በMarch 2, 1922 የካቶሊክ አምነት ተከታይ በሆነ ቤተሰብ ነው።

ካፑቺ ትምህርቱን በተገቢ ሁኔታ ከተከታተለ ቦሀላ መንፈሱ ወደ እምነቱ ስለ መራችው በግሪክ የካቶሊክ ኮሌጅ ትምህርቱን ተምሮ ወገኖቹን በእምነቱ በማገልገል 1947 ላይ የካቶሊክ ጳጳስ በመሆን ከፍተኛውን የእምነት ማእረግ ተቀብቷል።

በ1965 ወጣቱ ጳጳስ 4,500 የካቶሊክ እምነት ምእመናን ወዳሉባት እና እየሩሳሌም፣ዌስት ባንክ እና ማእከላዊ እስራኤልን የሚያካልል የእምነቱ አባት ተደርገው ወደ እየሩሳሌም ተዛወሩ።

ካፑቺ በአጭር ግዜ አገልግሎታቸው እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ እየፈጸመች ያለችው ዘግናኝ ግፎች አቻ የለሽ ሆነው ነው የጠበቋቸው። ቀን ከሌት ፍልስጤማውያን በገዛ ቤታቸው ሲገደሉ፣ቤታቸው ውስጥ ባሉበት ቤታቸው ፣የእርሻ ተክሎቻቸው በእስራኤል ወታደራዊ ሀይል ቤቱ በዶዘር የእርሻ ማሳው እሳት እየተለቀቀበት እንዲሰደዱ ሲያደርጓቸው እኚህ ጳጳስ ዝምታን ከመምረጥ ይልቅ በእያንዳንዱ የእስራኤል ባለስልጣን ቢሮ በመዞር ስለ እምነት ሳይሆን ሰው ልጅ እንባቸውን እየዘሩ ባለስልጣኖች በፍልስጤማውያን ላይ የሚፈጽሙትን ግፍ እንዲያቆሙ ቢማጸኑም አንዳች የሚፈይድ ተስፋ ማግኘት ሳይችሉ የፍልስጤም ሰቆቃ ቀጣይነት ያለው ሆነባቸው።

ከመሬታቸው ተፈናቅለው መውደቂያ ላጡት የፍልስጤም ተወላጆች ሀይማኖታቸው ሳያግዳቸው ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን እየለመኑ የድንኳን ቤት ቢያቆሙላቸውም ከጥቂት አዳሮች ቦሀላ የእስራኤል መንግሰት ወታደሮች አዛውንት አያቶች፣ እመጫት እናቶች የተጠለሉባቸውን ድንኳኖች ጳጳሱ በቆሙበት በእሳት እያጋዩ ሲመለከቱ እኚህ የእምነት አባት ልባቸው አመጸ።

ስለ ህልውናቸው መሳሪያ ያነገቱትን የፍልስጤም ነጻነት ተዋጊዎች(PLO) ማገዝ የመጨረሻው አማራጭ እንደሆነ አመኑ።

ወጣቱ ጳጳስ Aug. 8, 1974 ከሊባኖስ ድንበር ወደ እስራኤል በሚያስገባው የፍተሻ ኬላ ላይ ወደ ናዝሬት እያመሩ በእስራኤል ወታደሮች መኪናቸውን እንዲያቆሙ ተደረጉ። በአለም አቀፉ ህግ የዲፕሎማት መብታቸው እንዳይፈተሹ ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም ወታደሮቹ መኪናውን መፈተሽ እንዳለባቸው አስገድደዋቸው ሲፈተሽ ክላሽንኮፍ፣ሽጉጦች እና ተቀጣጣይ ፈንጂዎች ተገኙባቸው።

የካቶሊኩ ጳጳስ ከፍልስጤማውያን ጋር መሰለፋቸው እስራኤልን እጅግ ያስደነገጠ ሲሆን በእያንዳንዱ የፍልስጤም ህዝቦች ልብ ውስጥ ደግሞ "አባታችን" የሚል ስያሜን ተቸራቸው።

የእስራኤሉ የደህንነት ሀላፊ እስር ቤት ድረስ በመሄድ ከራሳቸው ቃል እስኪሰማ ፈጽሞ ማመን አልቻለም ነበር።

ጳጳሱ ያለ መከሰስ መብታቸው በፍርድ ቤት ተሰርዞ የ12 አመት እስር ተፈርዶባቸው ወደ ወህኒ ወርደዋል።

የእስር ግዜያቸውን አጠናቀው ሲለቀቁ መላው የፍልስጤም ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የጀግና አቀባበል አደረገላቸው።

ከዚያች የእስር ቀን ጀምሮ እምነታቸው ሳያግዳቸው የፍልስጤም ነጻ አውጪ ድርጅት አባል ሆነው እንደ አንድ ፍልስጤማዊ ሰላማዊ ሰልፎችን መርተዋል። አመጾችን አቀጣጥለዋል፣ ጥይት በሚተኩስባቸው የእስራኤል ወታደር ላይ ድንጋይ ፣ በጠርሙስ የተሰራ ቦንቦችን እየወረወሩ ፣ ከአንድ..ከሁለት ግዜ በላይ በጥይት ተመተው ደማቸውን ለተበዳዩ የፍልስጤም ህዝብ አፍስሰዋል፣ከሀያ ግዜ በላይ በእስራኤል እስር ቤቶች ታስረዋል።

እኚህ ድንቅ የያሲን አረፋት የልብ ጓደኛ 2017 በ94 አመታቸው ሙሉ እድሜያቸውን ስለ ሰው ልጅ ታግለው በሚመኟት ምድር አረፉ።ውለታቸውን ፈጽሞ ያልዘነጉት ፍልስጤማውያን ቴምብር ጭምር በማሰራት በልባቸው ማህተም ውስውስጥ ለዘላለም አንግሰዋቸው ይኖራሉ።

ክብር ለአባት ካፑቺ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Reshad Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group