Translation is not possible.
⭕️ፖለቲከኞች የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የማይገቡት የውሸት ቃል የለም! ምኞት በየአይነቱ ይደረድራሉ፡ ከፈለጉም ወንዝ በሌለበት ቦታ ድልድይ እንሰራለን ይላሉ።
 
⭕️ልክ እንደዚሁ በሀራም አንዲትን ሴት ማጥመድ የፈለገ ተልካሻና ወሮበላ ወንድ ለልጅቷ የተስፋ ቃል ይደረድርላታል፡ መላኢካ መስሎ ልነጠፍልሽ ይላታል።
 
⭕️ጉዳዩን ከጨረሰ በኋላ ግን ወደ ጭራቅነት ተቀይሮ፡ በሀራሙ አጥቦና ጨምቆ ያነጥፋታል።
 
⛔️ከዛማ ተረኛዋን የማጥመድ ስራ ይጀምራል!
 
⭕️ውዷ እህቴ! ከአጅነብይ ወንድ ጋር መጨባበጥ፡ ካፌ ለካፌ መዟዟር በስልክ መጀናጀን፡... የጀመርሽ ቀን ያንቺ ጉዳይ ጠልሽቷል፡ የጌታሽና የመልዕክተኛውን ትዕዛዝ ጥሰሻል።
 
⛔️ጅማሬው አበላሽተሽ ጥሩ ፍፃሜን አትጠብቂ!
 
⭕️አንተስ ሰው መሳይ በሸንጎ፡ እንደው አሏህን ካልፈራህ፡ እህት እንኳ የለህም? በሴትስ አልተወለድክም?
 
⭕️አንተ የምታደርገው ነገር በእህትህ፡ በሴት ልጅህ ቢሆን ትወዳለህን?
 
⭕️አስተውሉ! ጌታችን አሏህ ዝሙትን አትፈፅሙ አይደለም ያለው፡ ይልቁንስ አትቅረቡ ነው ያለውና ርቀታችንን እንጠብቅ!
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group