Translation is not possible.
🔴ከአረብ ሃገር የምትመጡ በተለይ አዲስ አበባ ላይ ተጠንቀቁ ኤርፖርት ላይ ተጠንቀቁ!!
ለራሳችሁ ስትሉ ልብ ግዙ…🙏🙏🙏
⚠️የዛሬውን የሿሿ መረጃ ተመልከቱ🙊🙊
           
⭕️ከአረብ ሀገር የመጣችን ኢትዮጵያዊ ዘርፈዋት ያመለጡ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል !
⭕️ተሽከርካሪ ተጠቅመው የሿሿ የተባለ የታክሲ ላይ የዘረፋ ወንጀል የፈፀሙ አራት ተጠርጣሪዎችን ከነ-ኤግዚብቱ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገለፀ
⭕️ተሽከርካሪ ተጠቅመው የሿሿ የተባለ የታክሲ ላይ የዘረፋ ወንጀል የፈፀሙ አራት ተጠርጣሪዎችን ከነ-ኤግዚብቱ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገለጿል።
⭕️ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ሊውሉ የቻሉት በቤይሩት ሀገር ስትሠራ ቆይታ ወደ ሀገራችን በመመለስ ላይ ያለች የግል ተበዳይ ወ/ሪት በላይነሽ በዶሬ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የራይድ ታክሲ አገልግሎት ሰጭ በመምሰል ኮድ 2- አ.አ ታርጋ ቁጥር B 96905 በሆነ ኮሮላ መኪና አሳፍረው ከቦሌ ወጡ።
⭕️ከዚያም ትንሽ አንደሄዱ ትራፊክ መጣብን እንዳንያዝ እዚህ ጋ ውረጂና ማዶ ተሻግረሽ ትሳፈሪያለሽ እንጠብቅሻለን በማለት ተበዳይ ስትወርድ ሻንጣዎቿን ጭነው ''ሿሿ"" የታክሲ ላይ የዘረፋ ወንጀል ፈፅመው  ሲያመልጡ አንድ ጉዳዩን በአይነ ቁራኛ ሲከታተል የነበር እግረኛ የመኪናውን ሰሌዳ ፎቶግራፍ አንስቶ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ትራፊክ ቁጥጥርና አደጋ ምርመራ አመራርና አባላት ፖሊስ ይሰጣል።
⭕️የትራፊክ ፖሊሶችም የደረሳቸውን መረጃ መሠረት በማድረግ ተጠርጣሪዎቹን በጂፒኤስ በመከታተል አራቱንም ተጠርጣሪዎች ልደታ አካበቢ በቁጥጥር ሥር አውለዋል።
⭕️በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹና በተሽከርካሪ ላይ በተደረገው ፍተሻ ከተለያዩ ግለሰቦች የሰረቋቸው ሰባት ተች እስክሪን የሞባይል ስልኮችን፣ ሁለት በተን ስልክ እና ከተለያዩ ግለሰቦች የተሰረቁ  84,485 ብር፣ አምስት ባለ አምስት መቶ ሪያል  ፣አንድ የባለ ሁለት መቶ ሪያል፣ ሦስት ባለ አስር ሪያል ኖት፣ ሁለት ባለ አምስት ሪያል መያዙን ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
⭕️የግል ተበዳይ ወ/ሪት በላይነሽ በዶሬ ንብረታቸውን ተረክበው በሰላም ወደ ቤተሰቦቿ እንዲሄዱ አድርጓል ፖሊስ።
⭕️ፖሊስና ኅብረተሰቡ በዚህ መልኩ ተባብረው ከሠሩ በየትኛውም የሀገራችን አካባቢ ሊፈጠር የሚችል የወንጀል ተግባር አስቀድሞ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እንደሚቻል ይህ ጥሩ ማሳያ ነው ብሏል ፖሊስ።
⭕️የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ትራፊክ ፖሊሶችም  በኤግዚብትነት የተያዙ ንብረቶች እና ተጠርጣሪዎችን ለቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለሀርቡ ፖሊስ ጣቢያ አስረክበዋል።
📣መረጃውን ለሌሎች ሸር አድርጉላቸው!!
የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉ: https://t.me/IbnuibrahimOfficial
image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group