Hanan Bedru Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Hanan Bedru shared a
Translation is not possible.

ያማል‼

ፈለስጢናዊቷ እህታችን ሃገር ሰላም ብላ ትዳር መሰረተች።

ግን የጽዮናዊቷ የቦምብ ጥቃት ሰለባ ሆነችና ሙሽረነቷን ሳትጨርስ ዱንያን ተሰናበተች።

አላህ በጀነት ይሞሽራት‼

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Hanan Bedru shared a
Translation is not possible.

የጽዮናዊዋ ድፍረት በዚህ ደረጃ ነው!

ባለፈ በራፋ መተላለፊያ መንገድ ላይ እርዳታ ሲገባ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በቦታው ተገኝቶ በእስራኤልና ፈለስጢን ጉዳይ አጭር ንግግር አድርጎ ነበር።

ከንግግሩ መሃል እንዲህ የሚል ይገኝበታል፦

«ሐማስ በእስራኤል ላይ ያደረሰው ጥቃት ያለምክንያት አይደለም። ፍልስጤማውያን ለ56 ተከታታይ አመታት የታፈነ ወረራ ገጥሟቸው ነው።»

ይህን ንግግሩን ተከትሎ  የእስራኤል መንግስት ፈጥኖ ባወጣው መግለጫ «ጉተሬዝ ስልጣናቸውን በአስቸኳይ ይልቀቁ፤ ፀብ-አጫሪ ንግግር ነው የተናገሩት!» ሲል ከሷል።

እርሷን የሚቃረን ከሆነ ለምን ወዳጇ አሜሪካ አትሆን መስማት አትፈልግም። እያጠፋችም ቢሆን በደፈናው የሚደግፋት እንጂ ታረሚ የሚላትን አትሰማም።

በርግጥ አንድ ቀን እርሷም ሆነች በውሸት ደጋፊዎች ታሪክ ሆነው ይቀራሉ። ኢንሻ አላህ!

ደጋፊዎቿ ጭምር ጥፋት ላይ መሆኗን አላጡትም።

#pakestine #gaza

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Hanan Bedru shared a
Translation is not possible.

"አል-አቅሷዐ በመስቀላዊያን እጅ ውስጥ ሆኖ ሳለ እኔ እንዴት ፈገግ ልል እችላለሁ? ምግብ እና ውሃ ከእኔ ጋር እንዴት ጣዕም ሊኖራቸው ይችላል?!" ይህ ቁድስን ከወራሪዎቹ የመስቀል ጦረኞች ነፃ ሳያወጣ በፊት አንድ ጊዜም ፈገግ ብሎ የማያውቀው የጀግኖቹ ጀግና የኩርዳዊው #ሰላሁዲን_አልአዩቢ ንግግር ነበር!

የቅርቡን የዚህችን እጅግ ጥንታዊት ከተማ ታሪክ እናንሳ እንኳ ቢባል ለ በርካታ መቶ አመታት በባይዛንታይን ሮሞች አረመኔያዊ አገዛዝ ስትማቅቅ የቆየችው ቁድስ በነ #ኻሊድ_ኢብን_ወሊድ እና #አቡኡበይዳ_ኢብን_አልጀራህ የሚመራው ጦር ባይዛንታይኖችን አንበርክኮ ቁድስ ዳግም በሙስሊሞች እጅ ለመግባት ችላ ነበር። የቁድስን ቁልፍ ቦታው ድረስ ሂደው የተቀበሉት #ኡመር_ኢብኑል_ኸጧብ የቁድስን ነዋሪዎች ነፃነት አውጀው ነበር የተመለሱት። ቁድስ ከዚያ በሗላ በፍትህና በኢስላማዊው ስልጣን ተንቆጠቆጠች። በኡመር ጊዜ ሙስሊሞች ከተቆጣጠሯት በሗላ ቁድስ እስከ መጨረሻው በሙስሊሞች እጅ አልቆየችም። የሙስሊሞችን መከፋፈልና እርስበርስ መባላት ተጠቅመው ባይዛንታይኖች ዳግም ቁድስን ተቆጣጠሩ። ቁድስ ዳግም የጨለማ ዘመን ውስጥ ገባች። ከተማዋን በደል ግፍና ጭካኔ ሞላት! በከተማዋ የሚስኪኖች ዋይታና የገዥዎች ከልክ ያለፈ አረመኔነት እንጅ አይሰማም አይታይም ነበር! ቁድስ በባይዛንታይኖች እንደዚህ በበደል ተውጣ ቆዝማ አዝና ብዙ አመታትን አሳለፈች! አሏህ #ሰልጁቅ የተሰኙ ቱርኮችን ከወደ ምስራቅ ኤዥያ አስነሳ። የሰልጁቅ የልጅ ልጅ የሆኑት እነ #ቱግሪል#ቻግሪ#አልፕ_አርስላን#መሊክ_ሻህ የመሳሰሉ ተወዳዳሪ አልባ ጀግና የጦር መሪዎች የአለም ልእለሀያል የነበረውን የባይዛንታይን ሮም ስርወመንግስት ስብርብር አድርገው የቱርኮች የኢስላም ገባሪ አደረጉት። ከሰልጁቆች ጎሳ #ከኪኒክ የሚመዘዘው የሰልጁቆቹ ጦር መሪ #አቲሲዝ_ቤይ ባይዛንታይኖችን አንኮታኩቶ ዳግም ቁድስ ነፃ አወጣት። አላህ ዲኑን በማን እንደሚረዳው ይአጅባል። ገና ከሰለሙ ጥቂት አመታትን ያስቆጠሩት ሰልጁቅ ቱርኮች የኢስላም ቅዱስ ከተሞችን በሙሉ አስመልሰው ከቻይና እስከ ሮም ያሉ የኢስላም ጠላቶችን በጉልበቶቻቸው አንበረከኳቸው። በሃያሎቹ ወራሪዎች የሰልጁቆች የአባሲድና የኸዋርዚም ሙስሊም መንግስታቶች ሲደመሰሱ አሁንም ዳግም አውሮፓዊያን ተባብረው "የመስቀል ጦርነት" በሙስሊሞች ላይ አወጁ። ሁሉንም የአውሮፓ መንግስታት ባካተተውና በጳጳስ ክሊመንት በተባረከው በዚህ ጦርነት ሙስሊሞች እንደ ቅጠል ረገፉ! ኢየሩሳሌምን ( ቁድስ ) የሰው ደም ሀይቅ ሆኖ ተንጣለለባት። ህፃናት አዛውንት ሳይሉ ፣ ሴት ደካማ ሳይሉ መስቀላዊያኑ ሁሉንም በሰይፋቸው አረዷቸው። ቁድስም ዳግም በጭራቆች እጅ ገባች። ቁድስን ዳግም ማስመለስ የአንድ በአሁኗ የኢራቋ ቲክሪት ከተማ የተወለደ ኩርዳዊ ሙጃሂድ ተራ ሆነ። ያ ሙጃሂድ የሙጃሂድ ልጅ ሰላሁዲን አልአዩቢ ይባላል። ሰላሁዲን በሰልጁቅ የጦር መሪ በነበረው በኢማዱዲን ዘንኪ ልጅ በኑረዲን ዘንኪ አመራር ስር ሆኖ በወታደራዊ ክህሎት ተኮትኩቶ በኡለሞች ተርቢ ታንፆ አደገ። አባቱ ሰላሁዲንን ከልጆች ጋር ሲጫወት ባገኘው ጊዜ ብድግ አደረገና ፍርጥ አደረገው። እና ተቆጣው ሰደበው "እኔ አድገህ ቁድስን ታስመልሳለህ እያልኩ አንተ እዚህ አቧራ ታቦናለህ?" አለው። ሰላሁዲን አላለቀሰም። ለምን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃልና።

ሰላሁዲን ቁድስን ነፃ ሳያወጣ በፊት ስቆ አያውቅም ተደስቶ አያውቅም። ያ የአሏህ ወልይ በቱርኮች ጥምረት መላው የአውሮፓ መስቀላዊ ጦርን ደምስሶ ኢየሩሳሌም ( ቁድስን ) ዳግም ነፃ አወጣ።

ከዚያ በሗላ በግብፅ የነገሱት ቱርኮቹ ማምሉኮች ተረክበው ኢየሩሳሌምን ጠብቀው አ hiቆዩ።

ከነርሱ በሗላ የአለማችን የምንጊዜውም ሀያሉ ኢምፓየር የሚሰኘው የኦቶማን ኺላፋ ( ደውለቱል ኡስማኒያ ) ቦታውን ተክቶ በየትኛውም የአለም ጫፍ ያለን የኢስላም ሉአላዊነት ሳያስደፍር ለ 500 አመታት ቀጥ አድርጎ ገዛ። ያኔ እንኳንስ ቁድስንና ትሪፖሊን እንኳ ማጥቃት የኦቶማኖችን ጀሃነም ያስከትላል። አውሮፓን በእንብርክኳ ያስኬዳት ፣ ሩሲያን ወገቧን የሰበራት ያ የኦቶማን ኺላፋ እስከ ውድቀቱ መጨረሻ ድረስ ቁድስን መካንና መድናን ለጠላት አሳልፎ አልሰጠም ነበር!

#አሁን_ቁድስ ከአንደኛው የአለም ጦርነት በሗላ #በክርስቲያን_አይሁዳዊያን ጥምረት ስር ነች። እነሆ ቁድስ ማንባት ከጀመረች ድፍን አንድ ክፍለዘመን ሊሞላት ነው።

እና ከዚያ ሁሉ ጨለማ የወጣች ቁድስ አላህ አሁን ሌላ ሰላሁዲን ፣ ሌላ አቲሲዝ ቤይ ፣ ሌላ አልፕ አርስላንን አይልክላትም ብላችሁ ታስባላችሁ??? በፍፁም አታስቡ !

ወድቆ መነሳት ፤ ጨለሞ መብራት የቁድስ ተፈጥሮዎች ናቸው !

ቁድስን አንድ ጊዜ አረቦች ፣ 3 ጊዜ ቱርኮች አንድ ጊዜ ኩርዶች ነፃ አውጥተዋታል ! አሁንስ እነማን የነፃነት ሰንደቁን ይዘው ቁድስን ነፃ ያወጡ ይሆን? ሁሉንም ጊዜ ያሳየናል! ግና አትጠራጠሩ ቁድስ ነፃ ትወጣለች።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Hanan Bedru shared a
Translation is not possible.

#ታማ አይደለም ግን በገንዘብ ማጣት ልትሞት ነው "እህታችን የወገኖቿ እርዳታ ትሻለች እንታደጋት !!!

የተከበራችሁና የተወደዳችሁ የገፄ ቤተሰቦች እንዲሁም ከሀገር ውጭ እና ሀገር ውስጥ የምትገኙ ኢትዮጲያውያን በሙሉ "ስለ አንዲት ህታችን ቤተሰቦቿን ለመርዳትና እራሷን ለመለወጥ ስትል እንደማንኛውም ኢትዮጲያዊ ውጪ ሳዑዲ አረቢያ በህጋዊ መንገድ ተሰዳ በነበችበት ቆይታዋ አንድ ያልጠበቀቺው ክስተት እና አሳዛኝ ታሪክ ልነግራችሁ ነው "የእናንተ ወገኖቿ እርዳታ የምትሻበት ምክኒያትም አሳውቂያችሁ ሁሉም የበኩሉን እና የሚችለውን አስተዋፆ እንድናደርግላት ብዬ ነው

"የተፈጠረው ክስተትና ታሪኩ ረዥም ቢሆንም አንባቢዎቼ እንዳይሰለቹ ስል በቻልኩት አቅም ለማሳጠር ሞክሪያለሁ፣ ነገሩ እንዲህ ነው እህታችን "ለይላ ኑርሰቦ ትባላለች ተወልዳ ያደገቺው ቡታጅራ ከተማ 02 ቀበሌ ዶቦ ጥጦ በሚባል መንደር ሲሆን በ2005 ዓ.ም ከአገሯ ወደ ሳዑዲ ንሮን ለማሸንፍ ስደት ትሄዳለች፣ ከዚያም በአንድ ሰዑዲ አረቢያዊያን የግል መኖሪያ ቤትም ተቀጥራ መስራት ብትጀምርም ነገር ግን "በተደጋጋሚ በቤቱ አባወራ ፆታዊ ትንኮሳዎች ይደርስባት እንደነበር ነበር ትነገረናለች

ታዲያ ከቆይታዋ 5 ወራት ቡኋላም ከዕለታት አንድ ቀን በተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት አባወራ ወይንም አሰሪዋ ከሌላው ቀን በተለየና ከፆታዊ ትንኮሳው ባለፈ ያለ ፍላጎቷ ሊያስገድዳት በነበረ ሁኔታ እራሷን ለመከላከል በምታደርገው ትግል ሳታውቅ የአሰሪዋ ጨቅላ/ህፃን ልጅ ትጎዳባታለች "እህታችንም ክስተቱ ወዲያውኑ ለፖሊስ በማሳውቅ እራሷን ለህግ አሳልፋ ትሰጣለች "የሳዑዲ ፖሊሶችም እህታችን ወደ እስር ቤት ወስዶ ያስራታል ከታሰረች ከ6 ወር ቡኋላ ህፃኗ ሞታለች ተብሎ ይነገራታል ከዚያም ጉዳዩ ፍርድ ቤት ይይዘውና ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ያለ ፍርድ ለ10 ዓመታት በተለያዩ ስቃዮች ከታሰረች ቡኋላ እህታችን በቅርብ "የሞት ፍርድ ይፈረድባታል። 😢😢😢

የተለያዩ ኢትዮጲያዊ የሚዲያ አካላቶች እና ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ እዛው የሚኖሩ ወገኖቿ ባደረጉት ያለለሰለሰ ጥረት "በመጨረሻ የይግባኝ ጥያቄው በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት ያገኛል ፍርዱ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ 2.000.000 የሳዑዲ ሪያል ገንዘብ በአንድ አመት ውስጥ እንድትከፍል እና ይህም ካልሆነ የተወሰነባታ የሞት ፍርድ እንደሚፀናባት ለረዥም አመታት የናፈቋት ቤተሰቦቿ በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ሆነው ያስረዱናል

ቤተሰቦቿም እነሱን ለመርዳት የተሰደደቺው ልጃቸው ከዚህ ፍርድ ለማዳን ከሚችሉት በላይ ተንቀሳቅሰው የተጠየቀውን ገንዘብ 10% ቱን ያህል መድረስ አልቻሉም ይህንንም ገንዘብ በተለያዩ መንገዶች ለማሰባሰብ ሲሞክሩ የልጃቸው ፍርድ ሊፀና የተሰጣት 1 ዓመት ጊዜ ከግማሽ በላይ ይባክንባቸዋል ሆኖም ተስፋ ባለመቁረጥ በተለያየ መንገዶች ከፈጣሪ ጋር በመሆን የልጃቸውን ሂወት ለማዳን አሁንም የቻሉትን በመጣር ላይ ይገኛሉ ታዲያ "እናንተም ደጋግ ኢትዮጲያዊ ወገኖቿም "ልጃችን ከሞት ፍርድ ለማዳን አቅማቹ የፈቀደውን እንድትረዱን በማለት በጥልቅ ሀዘንላይ የሚገኙት ቤተሰቧቿ በፈጣሪ ስም ይማፀናሉ

ከኢንባሲ የተሰጠ ደብዳቤዎች እና ጉዳዩን የሚያስረዳ ህጋዊ መረጃዎች እንዲሁም የህታችን ምስልና አንዳንድ ህጋዊ ማስረጃዎች ከታች ተቀምጧል

በእናቷ በአባቷ እና በወንድሟ የተከፈተ የኢ.ን. ባንክ አካውንት...👇

1000571065065 ወ/ሮ ነፊሳ እናት

አቶ ኑርሰቦ ረዲ አባት

ከድር ኑርሰቦ ወንድም

ለበለጠ መረጃ

0939397765 ከድር ኑረሰቦ "ወንድሟ✍️

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Hanan Bedru shared a
Translation is not possible.

የሱብሂ ሶላት ልክ እንድ ጦርነት ነው ጀግኖች እንጂ ፈሪዋች አይሳተፉበትም

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group