የጋዛ እልቂት!
-----
እስራኤል ለአንድ ሳምንት አቁማው የነበረውን የቦምብ ውርጅብኝ ዛሬ (December 1/2023) ቀጥላበት 175 ንጹሐንን ገድላለች። ብዙዎች ያቀረቡላትን የተኩስ አቁም ጥሪ እምቢ ብላለች።
የእስራኤል መሪዎች ደም የጠማቸው ተኩላዎች ሆነዋል። 15,000 ንጹሐንን ጨፍጭፈው የጥፋት ዘመቻቸውን አላቆም ብለዋል። እናቶችንና ህጻናትን እያስለቀሱ መሳቅን የእርካታ ምንጭ አድርገውታል።
-------
በእስራኤል ታሪክ የአሁኑ ዓይነት ዘረኛ እና በአረመኔዎች የተሞላ ካቢኔ ታይቶ አይታወቅም። ይሁን እንጂ ይህ መንግሥት የጠገበው በራሱ ብቻ አይደለም። አሜሪካ የምትባል በዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ስም የምትቀልድ የማጅራት መቺዎች መሪዎች ሀገርን ተገን አድርጎ ነው በክቡሩ የሰው ልጅ ህይወት የሚቀልደው።
ሐማስ የሚባለው ድርጅት በOctober 7/2023 በእስራኤል ላይ ጥቃት ፈጸመ። እስራኤልም እርሱን ሰበብ አድርጋ ዘመቻ ጀመረች። በሚዲያ "ሀማስን አጠፋለሁ" ብላ ፎከረች። ይሁንና በዘመቻዋ ሐማስን አልደቆሰችም። የተዘመተው 2.3 ሚሊዮን በሚሆነው ሰፊው የፍልስጥኤም ሕዝብ ላይ ነው። ጋዛን ሙሉ በሙሉ ዘግታ፣ ኤሌክትሪክ፣ ውሃ፣ ምግብ፣ ነዳጅ እና ሌሎች አቅርቦቶችን ቆርጣ ከላይ F-35 አውሮፕላኖችን እያዘመተች ባካሄደችው ድብደባ ካለቁት መካከል የሐማስ ተዋጊዎች ከ560 አይበልጡም። በዘመቻው በጋዛ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ነው የተካሄደው። ዛሬም ዘመቻው ቀጥሏል።
------
ምዕራባዊያን "ሐማስ አሸባሪ ነው" ይላሉ። ነገር ግን አሸባሪው ማን እንደሆነ የዓለም ሕዝብ መስክሮአል።
እስራኤል ደግሞ "በጉልበት የሚችለኝ የለም" ትላለች። ኃይል እና ችሎታ ሁሉ የፈጣሪ ነው። አላህ ጉልበተኞችንና ጨፍጫፊዎችን ድራሻቸውን ያጥፋው አቦ!! ሰላቢ ሁላ!