UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

" የአላህ መልእክተኛ ነብያችንን ስታገኟቸው ህዝቦችህ ከዱን ኡመቶችህ የጋዛን ህዝቦች ከዷቸው በሏቸው ። የልጅ ልጆቼ ሆይ ለአላህ መልእክተኛ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ንገሯቸው ! የልጅ ልጆቼ ሆይ የሆነብንን ሰሙቱላቸው ! የአላህ መልእክተኛ ሆይ ኡመቶችህኮ የጋዛ ህዝብ እንዲጠፋ ፈቀዱ በሏቸው ! የአላህ መልእክተኛ ሆይ ጠላቶቻችን እንዲያወድሙን ኡመቶችህ ፈቀዱላቸው በሏቸው ! የኢስላም ጠላቶች ሲበጣጥሱን ህዝቦችህ ፀጥ ብለው ተመለከቱን በሏቸው ! "

ይህ እኝህ የፍልስጤም አባት በእስራኤል የሚሳኤል ናዳ የተቀጠፉ ልጆቻቼውንና የልጅ ልጆቻቼውን ሲሸኙ ያስተላለፉት ልብ ሰባሪ መልእክት ነው ።

አላህና መልእክተኛው ፊት መልሳችን ምን ይሆን ???

ፍልስጤማዊያን አላህ እና መልእክተኛው ፊት ሲከሱን መልሳችን ምን ይሆን ?

አሁን እኛ በውዱ ነብይ መናፈቅ የሚገባን ህዝቦች ነን ወይ 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

5 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#በድል_ምእራፍ_ላይ_የሚገኘው_ሀማስ !

ጦርነቱ ተፋፍሞ እንደቀጠለ ቢሆንም ከእስራኤል በኩል መተንፈስ ይታያል ። ያበጠው ትእቢቷ እየሞሸሸ ይመስላል ። በቀናት አሳካዋለሁ ያለቺው በወራት ቢረዝምባትም እያሳካቺው ያለው ግን ድልን ሳይሆን ውርደትን ሽንፈትን ነው ።

ከአንድ ወር በላይ በተሻገረው የሀማስና የእስራኤል ትንቅንቅ እስካሁን ሀማስ ከ 136 በላይ ታንክና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎቿን እምሽክ አድርጎላታል ። ከ 500 በላይ ወታደሮቿንም ወደዚያ ወደሚጠብቃቸው አለም አሰናብቷቸዋል ። ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል ወታደሮች ደግሞ ቁስለኛ ሆነው የእስራኤል ሆስፒታሎችን አጠናንቀዋል ። የእስራኤል ወታደሮች አስክሬን በሰአታት ልዩነት ውስጥ እየገማ ለገናዥ ለቀባሪም አስቸግሯል ። ሄሊኮፕተሮች አስክሬን እና ቁስለኛ በማመላለስ ተጠምደዋል ።

ይህ ሁሉ ከባድ ምት ይህ ሁሉ ድቆሳ የደረሰባት አንድም የአየር ሀይል አንድ ሜካናይዝድ ሀይል አንድም የተራቀቀ የሚሳኤልና የሮኬት ሀይል በሌለው ጀግንነት ኢማንን ፅናትን ስንቅና ትጥቁ ባደሰረገው ሀማስ ነው ። እስራኤል ከተመሰረተች ጀምሮ እንደዚህ አይነት ውርደትም ሽንፈትም ውድመትም ደርሶባት አይታወቅም !

ልብ በሉ !

እስራኤል ከመካከለኛው ምስራቅ ተወዳዳሪ የሌላት የጦር ሀይል እንድትሆን ከ 600 በላይ የጦር ጄቶችን ከአሜሪካና አጋሮቿ የታጠቀች ፤ ሮኬት ተወንጭፎ እንዳይመታት Iron dome ን የመሳሰለ ቴክኖሎጂ ከአሜሪካ የተሰጣት ፤ የኑክሌር ቦንብን እንድትታጠቅ በምእራባውያን የተደገፈች ፤ ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎ በየአመቱ ረብጣ ቢሊዮን ዶላሮች ለጦሯ ማጠናከሪያ ወደ ካዝናዋ የሚንቆረቆርላት ሀገር ነች ። ይሄም ሁሉ አልበቃ ብሎ አሜሪካ የጦር ሀይሏን ጭምር ወደ መካከለኛው ምስራቅ ልካ " ምናልባትም ኢራን ብትመታትስ " በሚል የምትጠብቃት ሀገር ናት ። ታዲያ እስራኤል በዚህ ሁሉ መሀል ከ 400,000 በላይ ጠንካራ ሰራዊትን ገንብታለች ።

ግና ይሄ ሁሉ ነገር ሀማስን እንድታሸንፍ አለማስቻሉ ነው እንቆቅልሹ ። እናንተየ እንደት ከአለም ሁሉ ተነጥሎ አንድት ትንሽየ ግዛት ውስጥ የራሱን ርኬቶች በራሱ እጅ እየሰራ የሚታገል ድርጅት ይህን ሁሉ የሆነች ሀገርን ማርበድበድ ተቻለው ? ግሩም ድንቅ ነው ! የነርሱስ ይለያል !!

አሁን እስራኤል ወደ ጋዛ ከተማ ለመግባት የምታደርገው መንገድ የጀሀነም መንገድ ሆኖባታል ። የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ቃል በቃል የተናገረውን ልንገራችሁ " ከጋኔሎች (ጅኖች ) ጋር ነው እየተዋጋን ያለነው " አለ ። ለምን ተብሎ ሲጠየቅ " ከጋኔል ጋር ስትዋጋ ከየት መጥቶ ፊትህን እንደሚደረግመው አታውቀውም በጎዳናው እየሄድክ ድንገት ሊያነድብህ ይችላል እንድህ አይነት ጦርነት ነው እያደረግን ያለነው " አለ ። ወዳጅ ቢመስክር ምን ይደንቃል ? እንደዚህ ጠላት ሲመሰክር ግን አቤት ልእልና !! አቤት ጀብደኝነት !!

ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ደግሞ እንደዚህ ሲል ሀማስን ወቀሰ " ሀማሶች በደፈጣ አጥቅተው እየሸሹ እየተዋጉ ነው ያሉት " አለ ። እና ለአየር ሀይሉ እዚህ ነን እያሉ መጣራት ነበረባቸው 🤔

አንድ ነገር ግን ልንገራችሁ !

አሁን ሀማስ ሀይሉን ቆጥቦ ነው እየተዋጋ ያለው ። ወታደራዊ እንቅቃሴዎቿን ወታደርና ተሽከርካሪዎቿን እያጠመደ መደምሰስ ላይ ብቻ ነው የተወሰነው ። ምክንያቱም ጦርነቱ እስከሚን ሊቀጥል እንደሚችል ሶለማይታወቅ እስራኤልንም በረጅም ጊዜ ፍልሚያ የማዳከም አላማ ስላለው አሪፍ አድርጎ እየገባላት ነው ።

እና አሁን እስራኤል ነገሮች እንዳሰበቺው እየሄዱላት አይደለም ። ለዚያም ዛሬ በየቀኑ የተወሰነ ሰአታት ተኩስ አቁም አሳውቃለች ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እንግሊዝ በተቃውሞ እየተናጠች ነው !

የእንግሊዝ ፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ ስብሰባ ጠርቷል !

በእንግሊዝ የሚደረገው የፍልስጤማውያን የድጋፍ ሰልፍ የእንግሊዝ መንግስትን ወንበር እየነቀነቀው ። ትውልደ ህንዳዊው ሪሺ ሱናክ የሚመራው የእንግሊዝ መንግስት ለእስራኤል የማያወላውል ድጋፍ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክም እስራኤል ድረስ በመሄድ " ብቻሽን አይደለሽም እንግሊዝ ከጎንሽ አለች " ብሎ የመሰረተቻት ሀገር አሁንም እንደማትተዋት ገልፆ ወደ እንግሊዝ ሲመለስ ግን የገጠመው የእንግሊዝ ህዝብ ቁጣን ነው ።

ለንደን የፍልስጤም ከተማ እየመሰለች ነው ። እናም ነገ እጅግ ከባድ የሆነ የፍልስጤማውያን የድጋፍ ስልፍ በመጠራቱ መንግስት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቋል ።

በመሆኑም የእንግሊዝ መንግስት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስቸኳይ የፓርላማ ስብሰባ የጠራ ሲሆን በፍልስጤም እና በእስራኤል ላይ ያለውን አቋም እንደሚያሳውቅም ገልጿል ። እናም መንግስት ለእንግሊዝ ህዝብ ባስተላለፈው ጥሪ የነገን ብቻ እንዲጠብቁ እስከ ውሳኔው ድረስ በትእግስት እንዲጠብቁ ተማፅኗል ።

እንግሊዝ እየተነሳባት ባለው የህዝብ ቁጣ ከአቋማ እየተንሸራተተች ሲሆን የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ድምፀ ተአቅቦ ማድረጓ ይታወቃል ።

ፍልስጤሞች የምእራቡን አለም ህዝብ እያሸነፉ ሙምጣታቸውና ምእራባውያን ህዝቦች ለእስራኤሎች ያላቸው ጥላቻ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ እስራኤልን እና አሜሪካን በከፍተኛ ሁኔታ ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል ።

ሰላማዊ ትግል ለውጥ ያመጣ ለማይመስላቸው የአረቡ አለምና የሀገራችን ፊርቀኞች ይህ ትልቅ ትምህርት ይሁናቸው !

image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
6 month Translate
Translation is not possible.

ameeen

የአላህ ያረብ

8 views
1 view
Send as a message
Share on my page
Share in the group