UMMA TOKEN INVESTOR

Подписки
0
Нет подписок
Перевод невозможен
image
Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе
2 года перевести
Перевод невозможен
እዚያው ቁጭ ብለው የእናታቸዉን መታመምና የአባታቸዉን ሞት ተራ በተራ የሚሰሙ ስደተኞች ይገርሙኛል። ያሳዝኑኛልም። "ለምን አትመጡም?" ሲባሉ "አልሞላልኝም" ይላሉ ። እንዲሁ እያሉ አሥርና ሀያ ዓመት የሆናቸው "ቀልደኞች" አሉ።
ወዳጆቼ! ሁላችንም ባለችን ጥሪት ነው የምንንቀሳቀሰው እንጂ መቸ ሞላልን። ዱንያ ላይ የሞላለት አንድም ሰው የለም።
ከሥር ከሥር ካልከወንናቸው በስተቀር ዱንያ ላይ ቶሎ ቶሎ የሚበላሹብን ብዙ ነገሮች አሉ። ከሚበላሹ ነገሮች መካከል አንዱ ሰው ነው። ሰው ድንገተኛ ፈራሽ ነው። ቀስ ብለን፣ ሲሞላልን፣ ኋላ ላይ ... እንዘይረዋለን ያልነው ሰው ድንገት ሳይታሰብ ሊፈርስ ይችላል ። ያ ከመሆኑና ቁጭታችሁ ከመብዛቱ በፊት በተለይ እናት አባቶቻችሁን ቶሎ ቶሎ ዘይሩ።
 
ሶባሐል ኸይር
Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе
2 года перевести
Перевод невозможен
ሰደቃ ያለ ገንዘብ!
 
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
 
﴿وَتُمِيطُ  الْأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ صَدَقَةٌ﴾
 
“ከመንገድ ላይ አስቸጋሪ ነገር ማሰወገድ ሰደቃ ነው።”
 
📚 ቡኻሪ (2959) ሙስሊም (1009) ዘግበውታል
Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе
2 года перевести
Перевод невозможен
አተህያቱ
 
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
 
ነብያችን”ﷺ” በለይለቱል ኢስራ ወል ሚዕራጅ ጉዞዋቸዉ ወቅት አላህ ሲገናኙ እንዲህ ነበር ያሉት’’
አተህያቱ ሊላሂ ወሰለዋቱ ፤ ወጠይባ’’ التَّحِيَّاتُ لِلّٰهِ وَالصَّلَوَاتُ وَالطَّيِّبَاتُ،
ማለትም ’’ክብር ሁሉ ለአላህ ነዉ፤ ሶላቶች እና መልካም ተግባራቶችም ለአላህ ሲባል የሚደረጉ ናቸዉ" አሉ።
 
አላህም መለሰላቸዉ፦ ’’አሰላሙ አለይከ አዩሃ ነቢዩ ወራህመቱላሂ ወበረካቱ" اَلسَّلَامُ عَلَيْكَ أَيُّهَا النَّبِيُّ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ، ማለትም ’’አንተ ነብይ ሆይ! ሰላም በአንተ ላይ ይዉረድ፡፡ የአላህ እዝነትና ዉዴታም ይስፈንብህ"
 
ነብያችን”ﷺ” እንዲህ በማለት መለሱ፦ "’አሰላሙ አለይና
ወዐላ ዒባዲላሂ አሷሊሒይን’’´ اَلسَّلَامُ عَلَيْنَا وَ عَلٰى عِبَادِ اللهِ الصَّالِحِيْنَ، ማለትም "በእኛ እና በአላህ ቅን ባሪያዎችም
ላይ ሰላም ይስፈን"
 
ይህንን የሰላምታ ቃለ-ምልልስ እየሰሙ የነበሩ መላእክቶች እንዲህ አሉ፦
’’አሽሃዱ አን ላ ኢላሃ ኢለላህ ወአሽሃዱ አነ ሙሃመደን ዐብዱሁ ወረሱሉሁ’’ أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلٰهَ إِلَّا اللهُ، وَأَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَ رَسُوْلُهُ ማለትም "ከአላህ ዉጪ ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልእክተኛዉ እነደሆነ አመሰክራለሁ"፡፡
 
እንግዲህ ይህ ነዉ በጌታችንና በነብያችን”ﷺ” መካክል የተደረገዉ የሰላምታ ልዉዉጥ፡፡ጥበብ የተሞላበት የነብያችን”ﷺ” ኡመትን ሁሉ ያካለለ ቅዱስ ንግግር ነዉ፡፡ ልብ ብላችሁ ከሆነ አላህ ’’አንተ ነብይ ሆይ! ሰላም በአንተ ላይ ይዉረድ፡፡ የአላህ እዝነትና ዉዴታም ይስፈንብህ" ሲላቸዉ፤ እርሳቸው "በእኛ እና በአላህ ቅን ባሪያዎችም ላይ ሰላም ይስፈን" ነበር ያሉት፤ ነቢያችን በእኔ ላይ ሰላም ይስፈን አላሉም ይልቁንስ በእኛ የሚለዉን ቃል ነዉ የተጠቀሙት፡፡
 
ትርጉሙን የማታዉቁ ሰዎች ከአሁን በኃላ ኢንሻላህ እንዲህ አይነት ስሜት ይኖራችኋል ብዬ አስባለው።
 
✍️ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
 
የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
 
ወሰላሙ አለይኩም
image
Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе
2 года перевести
Перевод невозможен
ጀነት ሰርፕራይዝ ያለበት አገር ነው። ግምታችን ትክክል ላይሆን ይችላል። ይገባሉ ያልናቸዉን ሰዎች የማናገኝበት፤ አይገቡም ብለን ያሰብናቸው ሰዎች የሚገኙበት ሊሆን ይችላል።
 
ፍፁም ትክክል ነን የጀነት ነን አትበሉ። ኢማን አለን አትበሉ። አላህን እንፈራለን አትበሉ። ማን ኢማን እንዳለው ፤ ማን እሱን እንደሚፈራ የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው። ማንን ለጀነቱ እንዳጨና እንደመረጠ የሚያውቀው እሱ አላህ ሱ.ወ. ብቻ ነው።
Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе