Areb Jemal Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Areb Jemal shared a
Translation is not possible.

መህዲ ማነው?

▬▭▬▭▬▭▬

✅:‹‹መህዲ›› በመጨረሻው ዘመን ከደጃልና ዒሳ መምጣት አስቀድሞ የሚነሳ ታላቅ ‹‹ኸሊፋ›› ነው። ‹‹መህዲ›› የማዕረግ ስሙ ሲሆን ‹‹ሁዳ›› ከሚለው ቃል የተገኘና ‹‹የተመራ ቅን ኸሊፋ›› ማለት ነው። መጠሪያ ሙሉ ስሙ ደግሞ ‹‹ሙሐመድ

ኢብን አብዱላህ አል-መህዲ›› ነው።

🔰:ስለ መህዲ በቁርኣን የተነገረ ምንም ነገር አናገኝም። መረጃዎቹ በሙሉ ከሐዲስ የተገኙ ሲሆን #ከሃያ በላይ የተረጋገጡ ዘገባዎች ይገኛሉ። ብዙ የሱንና ዑለማዎች ስለ መህዲ የፃፉ ሲሆን ቲርሚዚና አቡ-ዳውድ ራሱን የቻለ ምዕራፍ ሰጥተውታል። ከሁሉም ታዋቂው ሐዲስ አቡ-ዳውድ የዘገቡት ሲሆን ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ትንሳኤ(የውመል ቂያማ) ሊቆም አንድ ቀን ቢቀረው እንኳን አላህ ከቤተሰቤ የሆነን፤ ስሙ ከእኔና ከአባቴ ጋር የሚመሳሰል መሪን ሳያስነሳና በበደል የተዋጠችውን ምድር በፍትህ ሳይሞላት አይተዋትም።››

📕|(አቡ-ዳውድ 4282)|📕

🔭:ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው መህዲ የነቢዩ (ﷺ) ቤተሰብ ነው። ስሙም የነቢዩን (ﷺ) እና አባታቸውን የያዘ ሲሆን ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ›› ወይም ‹‹አህመድ ኢብን አብዱላህ›› ነው። የሚመጣውም ዓለም በዙልም በተዋጠችበት በመጨረሻው ዘመን ሲሆን የአላህን ቃል ከፍ በማድረግ ፍትህን ያነግሳል።

📮:ኡሙ ሰለማ (ረዲየሏሁ አንሃ) እንደተናገረችው ነቢዩ (ﷺ) ‹‹መህዲ #በፋጡማ በኩል የሚገኝ ቤተሰቤ ነው።›› ብለዋል።

🔎:ኢብኑል ቀይም ይሄንን▽ሐዲስ ሲያብራሩ ࿐

‹‹መህዲ የሐሰን ዘር ሲሆን አል-ሐሰን ለሙስሊሙ አንድነት ሲሉ ኸሊፋነታቸውን አሳልፈው በመስጠታቸው ምክንያት አላህም በመጨረሻው ዘመን ከቤተሰባቸው ታላቅ ኸሊፋ በማስነሳት ክሷቸዋል።›› ሲሉ ፅፈዋል።

📕|(አቡ-ዳወድ 11/373)|📕

🔖:አቡ-ሰዓድ አልኩድሪ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ (ﷺ) ስለ መህዲ ገፅታ ሲናገሩ ༻

‹‹ቁመቱ ረጂም፣ ትከሻው ሰፊ፣ አፍንጫው አጠፍ ያለ ነው።›› ብለዋል።

📕|(አቡ-ዳውድ 4265)|📕

✅:መህዲ የሚነሳበትን ቦታ በተመለከተ የተለያዩ ዘገባዎች አሉ። ከፊሎቹ ከሻም ከፊሉ ከኹራሳን ሌላው ደግሞ ከመዲና እንደሆነ ይናገራሉ። ኢብን ከሲር የሁሉንም ሐዲሶች ጥቅል ሀሳብ ሲያስቀምጡ ‹‹የሚነሳው ከምስራቅ ነው። ከዚያም ወደ መካ ይሄዳል። ሰዎችም በከዓባ ዙሪያ ቃልኪዳን ይገቡለታል።›› ብለዋል። እንዲሁም በሌላ መጽሐፋቸው ‹‹በሐዲስ በተጠቀሰው መሰረት

ባንዲራው ጥቁር ነው።›› በማለት አብራርተዋል።

📒|(አልቢዳያህ ወልኒያህ 19/63፤ አልፊታን ወልመላሂም 1/49)|📒

🔰:ኢማም አህመድ እንደዘገቡት መህዲ መሪነት ሲመረጥ ፍላጎቱም ክህሎቱም አልነበረውም። እናም ‹‹አላህ በአንድ ሌሊት ይመራዋል።›› ብለዋል (ﷺ)።

ኢብን ከሲር ሐዲሱን ሲያብራሩ፡- ‹‹ይህ ማለት አላህ ይረዳዋል፣ ከዚህ በፊት ያልነበረውን ችሎታም ይሰጠዋል ማለት ነው።›› ብለዋል።

📓|(አህመድ 2/58/ አልፊታን ወልመላሂም 1/29)|📓

👑:መህዲ #ኸሊፋነትን ከተረከበ በኋላ ሙስሊም አገራትን በአንድ በማፅናት በቀደመው ኢስላማዊ አስተዳደር ስር ያስገባቸዋል። ከዚያም በቡኻሪ እና

ሙስሊም (2897) እንደተዘገበው ከሮማውያን ጋር የመጨረሻው ታላቁ ጦርነት ‹‹አል-መልሃማ አል-ኩብራ›› ይካሄዳል። ሙስሊሞችም ዳቢቅ ላይ ድል ደርጋሉ። ከዚህ በፊት ያልተከፈቱ አገራትንም ይከፍታሉ። ከዚያ በኋላ ሙስሊሞች በየትኛውም ኃይል አይሸነፉም። አላህ አማኞችን ከፍተኛ የሀብት መትረፍረፍ ይባርካቸዋል።

🌴:ሸይህ ዑመር ሱለይማን አል-አሽቀር ሐዲሱን መሰረት በማድረግ እንደተናገሩት ፦

‹‹ይህ ጦርነት ከባድ ውድመትን ስለሚያስከትል ዓለም አሁን ካለችው ስልጣኔ ወደኋላ በመመለስ እንደ ጥንቱ በጦር በጋሻ በፈረስ መጠቀም ይጀምራሉ።›› ብለዋል።

📘|(አል-ቂያማህ አስ-ሱግራ 275)|📘

📌:መህዲ ታላቅ ጦርነት አድርጎ ሙስሊሞችን የበላይ ቢያደርግም ጊዜው የቂያማህ ቀን መቃረቢያ በመሆኑ ከባባዶቹ ፊትናዎች ይከሰታሉ። ከእነዚህም መካከል ቀዳሚው #የደጃል መነሳት ነው። እሱን ተከትለው የዕጁጅና መዕጁጆች ከጉድጓዳቸው ይወጣሉ። በዚህ ጊዜ አላህ ዒሳን (ዓለይሂ ሰላም) ለእርዳታ ይልከዋል። በሐዲስ እንደተጠቀሰው ዒሳ (ዓለይሂ ሰላም) ወደ ምድር የሚወርደው በፈጅር ሰላት ወቅት ነው። ነቢዩ (ﷺ) ሲናገሩ ‹‹መህዲ ዒሳን አሰግደን ይለዋል። ዒሳም እናንተ መሪዎች መሆናችሁ ከቂያማህ ምልክቱ ነውና አንተ አሰግደን ይለዋል። ዒሳም ከመህዲ ኋላ ተከትሎ ይሰግዳል።›› ብለዋል።

📘|(ሙስሊም 225)|📘

🪩:ከዚያ በኋላ ዒሳ ከሙስሊሞች ጋር በመሆን የዕጁጆችንና ደጃልን በመጋደል በአላህ ዕርዳታ ያጠፋቸዋል። ነቢዩ (ﷺ) እንደተናገሩት ‹‹ሙስሊሞች ለሰባት ዓመታት ያህል የየዕጁጆችን አጥንት ቀስትና ጋሻ ለማገዶነት ይጠቀሙበታል። መህዲ በኸሊፋነት የሚቆይባቸው ዓመታት ‹‹ሰባት›› እንደሆኑ አብዛኛዎቹ የሐዲስ ምሁራን ይናገራሉ። ከእነሱ መካከል አንዱ የኢብኑ ማጃህ ሲሆኑ ነቢዩ (ﷺ)

‹‹መህዲ ሰባት አጭር ጊዜያትን ይቆያል።›› ማለታቸውን ዘግበዋል።

📙|(ኢብን ማጃህ 4039)|📙

🔖:አል-መህዲ እስኪመጣ ሙስሊሙ ጂሐድን በመተው መጠበቅ ይኖርበታል? ለሚለው ጥያቄ ሸይህ ሙሐመድ ሷሊህ አል-ሙነጂድ በፈትዋ ገፃቸው እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹ከጂሐድ መዘንጋት ከከባባድ ወንጀሎች አንዱ ነው። አላህ ያዘዘው ሁሉም የራሱን ግዴታ እንዲሞላ ነው። መህዲ የራሱ ጂሐድ አለው። ይሄም ህዝብ የራሱን ጂሐድ ማድረግ ግዴታው ነው። አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ብሏል፡-

‹‹ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚሆን ድረስ ተጋደሏቸው። ቢከለከሉም አላህ የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነው።››

[አንፋል፡ 39

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Areb Jemal shared a
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Areb Jemal shared a
Translation is not possible.

"አል-ካቡስ"

ይህ በእንቅልፍህ ጊዜ የሚያጠቃህ "አል-ካቡስ" የተባለ ልዩ ጂን ነው።

የጥቃቱ ምልክቶች አንድ ሰው በእንቅልፍ ላይ እያለ ደረቱ ላይ ከባድ ነገር

መጫን ፣እግርን ቆላልፎ አካሉን ጨምቆ በመያዝ እና ትንፋሹን በመገደብ

መናገር መጮኽ እና መንቀሳቀስ እንዳይቺል ያደርጋል

ይህ ጂን ከላይህ ላይ ከሄደ በኋላ ወዲያውኑ በድንጋጤ ትነቃለህ።

የምዕራባውያን ሳይንቲስቶች ይህንን ክስተት "የእንቅልፍ ሽባነት" ብለው

ይጠሩታል።

ነገር ግን እስልምና ሰዎችን በእንቅልፍ ወቅት የሚያጠቃ ጂን እንደሆነ

ይነግረናል .....

አንድ ሰው ሰይጣን ይተኛል ወይ በማለት ስለ ሰይጣን መተኛት በየትኛው

ኢስላማዊ ወጎች ውስጥ ተጠቅሷል ብሎ አንድ አሊምን ጠየቀ ? .......

አሊሙም ፈገግ አሉና “ያ የተረገመ ፍጡር ተኝቶ ቢሆን ኖሮ ትንሽ ፋታ አግኝቼ

ነበር!” በማለት መልስ ሰጡ።

ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-ወደ መኝታ ስትሄድ ሰይጣን

ጭልጥ ያለ እንቅልፍ እንድትተኛ ከራስህ ጀርባ ሶስት ቋጠሮዎችን ይቋጥራል

።በእያንዳንዱ ቋጠሮ ላይ የተለያዩ ቃላትን እያነበነበ ይተነፍሳል...

⇨1.ኛው ቋጠሮ ከእንቅልፍህ ስትነቃ ይበጠሳል

⇨2.ኛው ቋጠሮ ወዱእ ስታደርግ ይበጠሳል

⇨3.ኛው ቋጠሮ ስትሰግድ ይበጠሳል

በተለይ ለሱብሂ ሰላት ንቁ እንዳትሆን ወደተሻለ የእንቅልፍ ደረጃ ያሸጋግራል

፣ይህ ከሰይጣን መሆኑን እወቅ።

በእንቅልፍ ወቅት ሰይጣን በጆሮዎችህ ውስሕ ሽንቱን ይሸናል።

ሰይጣን በአፍንጫህ ያድራል ፣በእንቅልፍ ውስጥ ጥቁር ውሻ ካየህ ሰይጣን

መሆኑን እወቅ።

በቤትህ ወይም በክፍልህ ውስጥ መኖሩን አታውቀውም በተለይ በእንቅልፍ

ውስጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንትፈጽም ያደርግሀል!! ከዛ የሱብሂ ሰላትን

ይከለክልሀል

ሰይጣን አይተኛም አንተ በምትተኛበት ጊዜ የተረገመው ሰይጣን ሙሉ በሙሉ

ንቁ ሆኖ ይጠብቅሀል። በጭራሽ አይተኛም።እርሱ ሁል ጊዜ ሰዎችን ይጠብቃል

እነሱን ለመጉዳት እድሎችን ይፈልጋል።

ታዲያ እራሳችንን ከዚህ ጂን እንዴት እንከላከል? በሱና ተኛ

ከመኝታ በፊት ዉዱእ አድርግ ከዛም የወዱእ ሱና ስገድ፡-

ወደ አልጋህ ከመውጣትህ በፊት የምትተኛበትን ቦታ በጨርቅ ፣ወይም

በምትለብሰው ልብስ አልያም በእጅህ ሶስት ጊዜ ወደ ግራ አራግፍ ....

ይህ ጂኑ በምትተኛበት ቦታ ላይ ቀድሞህ ስለሚቀመጥ ከክፍልህ ወይም

ከቤትህ እንዲወጣ ያደርገዋል ።ከዚያም ወደምትተኛበት ቦታ በፍጥነት

ተቀመጥ። ከመተኛትህ በፊት......

✯ ሱራ ኢኽላስን

✯ ሱራ አል-ፈለቅ እና

✯ ሱራ አን-ናስን ማለትም

⇨ቁልያ አዩኽል ካፊሩን 3 × ጊዜ

⇨ቁልሁ ወላሁ አሀድ 3 ×ጊዜ

⇨ቁል አኡዙ ቢረቢናስ 3 × ጊዜ ቅራ

✪ከቻልክ አያተል ኩርሲይን አስከትል

ከቀራህ በኋላ በመዳፎችህ ላይ ሶስት፣ሶስት ጊዜ ትፍ፣ትፍ አድርገህ፣ ከአናትህ

በስተኋላ ጀምረህ እጅህ መድረስ እስከሚችለው ቦታ መላ ሰውነትህን ዳብስ

በመቀጠል.... ➽ ሱብሃነላህ 33 ጊዜ

➽ አልሀምዱሊላህ 33 ጊዜ

➽ አላሁ አክበርን 34 ጊዜ ዚክር አድርግ ።

ከዛ ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርገው

አላህ ሁላችንንም ከጂን ይጠብቀን። አሚን

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group