nebil nur Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

nebil nur shared a
Translation is not possible.

6 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
nebil nur shared a
Translation is not possible.

💡የተሻለ ማንነት እንዲኖረን የሚረዱን ምክሮች 💡

❖•◐ 1.ምንጊዜም ካለህበት የ ትምህርትና የእውቀት ደረጃ ከፍ ለማለት ሞክር ።

❖•◐ 2.ሚስጥርህን ለ ራስህ ብቻ ደብቀህ ያዝ ።ከ ልፍለፋና ከ ክርክር ራስህን አርቅ ።

❖•◐ 3.ጥፋት በምታጠፋበት ጊዜ ብቻ እንጂ ተደጋጋሚ የሆነ ይቅርታ አትጠይቅ ።

❖•◐ 4. በተፈጥሮህ ሁን ። ሰዎች ላይ ተፅዕኖ መፍጠር ከሚወዱ ሰዎች ጋር አትመደብ ።

❖•◐ 5. ራስህንና የፈፀምካቸውን መልካም ተግባራት አትናቅ ። ለሌላም ሰው አሳንሶ እንዲመለከትህ አትፍቀድ ።

❖•◐ 6. ማንንም ሰው አትለምን ። የሰው ልጅ ክብር በገንዘብ ና በቁሳቁስ የማይለካ ትልቀ ሀብት ነውና።

❖•◐ 7. አብዛኛውን የሕይወት ውሳኔዎችህን ራስህ ምረጣቸው ። ከ አንተው ውጭ ስለራስህ ሊያስብልህ የሚችል ሰው የለምና።

❖•◐ 8. ሕይወትን ተጨባጭ ላይ ባለው ሁኔታና በፈገግታ ተመልከታት ። በራስህ የተለየህ ሁን እንጂ ሰዎችን አትከተል።

❖•◐ 9.ጥንካሬና ሃይለኝነት ፍትሐዊ በመሆን እንጂ አምባ ገነን በመሆን የማይገኝ መሆኑን አስታወስ።

❖•◐ 10. የጊዜህን አሳሳቢነት አትዘንጋ ። በማይሆን ዛዛታና የውሸታሞችን ቅዠት በመስማት አታጥፋው።

❖•◐ 11. ብዙ ከማውራት ይልቅ ብዙ አዳምጥ ። ስለ ግል ሕይወትህም ብዙ ጊዜ ከማውራት ተቆጠብ ።

❖•◐ 12. ያገኘኸውን ሁሉ መውሰድና መጠቀም አይኖርብህም ። ላንተ የሚጠቅምህንና መልካምን ነገር ለመስራት የሚረዳህን ብቻ ውሰድ ።

❖•◐ 13.የተሻለ ህይወት መኖርና የምትፈልገውን ነገር ማሳካት ትችላለህ ይገባሃልም ። ነገር ግን ይህ በአንዴ የሚሆን ነገር ሳይሆን በራስህ ጥረት የምታሳካው ነገር ነው።

❖•◐ 14.ከሌሎች ሊያጋጥሙህ የሚችሉ እንቅፋቶችን ጠብቅ ። ሊያበሳጩህና ሊረብሹህ ለሚችሉ ነገሮች ትኩረት ሳትሰጥ ለማለፍ ሞክር

Send as a message
Share on my page
Share in the group