ሱብሐነክ ያረብ‼
===========
«ጉዳዩ እኔንም ፈገግ አሰኝቶኛል።»
✍ ሐዲሡን ያስተላለፉት፤ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ታላቁ ሶሐባ 《ዐብዲልላህ ኢብኑ መስዑድ》 ናቸው።
★
ረሱል ሶለልሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል ይሉናል።
*
ከጀሀነም ባለቤቶች ውስጥ መጨረሻ ላይ ከእሳት የሚወጣውንና ከሁሉም መጨረሻ ላይ ወደ ጀነት የሚገባውን ሰው፤ አላህ "اذهب، فدخل الجنّة!"
«ሂድ! ጀነት ግባ‼» ይለዋል።
ሰውየውም ወደ ጀነት ሲሄድ የሞላች ትመስለዋለች።
ከዚያም ይመለስና፦ "يا ربّ ، وجدتها ملأى"
«ጌታዬ ሆይ! "ሞልታ አገኘዃት‼"» ይለዋል።
አሁንም እንደዚሁ ወደ ጀነት ይሄድና የሞላች ትመስለዋለች። በድጋሜ መልሶ "ሞላችብኝ!" ብሎ ያሰሙትና አሁንም "ሂድ ግባ!" ይባላል።
★
መጨረሻ ላይ ግን "ሞላችብኝ!" ብሎ ወደ አላህ በድጋሜ መጥቶ ሲያሰሙት፤ አላህ እንዲህ ይለዋል፦
"اذهب فدخل الجنّة، فإنّ لك مثل الدّنيا وعشرة أمثالها!"
«ሂድ! ጀነት ግባ!፤ ላንተ ዱንያን አምሳያና 10 አምሳያዎቿን ያክል አለህ‼»
*
ሰውየውም እንዲህ ይላል፦
"أتسخر بي، أو أتضحك بي– وأنت الملك؟"
«"ትቀልድብኛለህን?!"፣ ወይም "ትስቅብኛለህን?!" ፤ አንተ (የአለማት) ንጉስ ሁነህ ሳለህ?!»
♣
የሐዲሡ አስተላላፊ ዐብዲልላህ ኢብን መስዑድ እንዲህ ይላል፦
«የአላህ መልዕክተኛን ሶለልሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በርግጥ ቀንጣጢያቸው እስኪታይ ድረስ ሲስቁ ተመልክቻለሁ‼»
አክለውም እንዲህ ይሉ ነበር ብሏል፦
"ይህ (ለዚህ ሰውዬ የተሰጠው ዱንያና 10 አምሳያዎቿ)፤
የጀነት ባለቤቶች አነስተኛው ደረጃ ነው።"
||
ሱብሐነልሏህ‼ ይህ አነስተኛው ከሆነ፣ ይሄውም የተሰጠው ለጀሀነም ተዳርጎ ለነበረ ሰው ከሆነ፤
ከናካቴው ጀሀነም ላልነካቻቸው የሚሰጠው ምን ሊሆን ነው?!
♠
የገረመኝ ሰውዬው አላህን "ትቀልድብኛለህ፣ ትስቅብኛለህ?" ያለው ነው።
በዘመናችን ቋንቋ፤
ከጀሀነም ወጥቼ ሳለ ይህን ሁሉ አለህ በማለት «ሙድ ትይዝብኛለህ?!» ማለቱ ነው።
ያ ሰላላም‼
አላህ ከጀነት ሰዎች ያድርገን።
ሌላው ቢቀር ይህን የመጨረሻውን እንኳ እንዳያሳጣን።
||
ሐዲሡን ያገኘሁት ሪያድ ላይ ነው።
ግን [ቡኻሪ: 6571 ላይ እና [ሙስሊም: 186]] ላይ ታገኙታላችሁ።
||
ወንድማችሁ: ሙራድ ታደሰ
=======
ከጉዞ ላይ!
ኦገስት 16, 2019 G.C.