UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እንዲህም ይታሰባል...

ሰውየው በፈረስ በሚሳበው ጋሪ አሸዋ በማመላለስ ላይ ሳለ ሃይለኛ ንፋስና ወጀብ የቀላቀለ ዝናብ መዝነብ ጀመረ በአካባቢው ያሉ ሰዎች ከዝናቡ ሽሽት ሩጫ ሆነ ባለመኪናዎችም መስኮታቸውን ዘጋግተው መሸጉ ባለጋሪው ግን ፍንክች አላለም ፈረሱን ጥብቅ አድርጎ በማቀፍ ዝናቡ እስከሚያባራ ለሰዓታት አብሮት ቆመ

ከዚያም ዝናቡ አባርቶ ከእቅፉ ቀና ሲል በዙሪያ የነበሩ ዝናቡን የተጠለሉና መኪናቸው ውስጥ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ዓይኖች በፍቅር በማዘንና በፈገግታም ጭምር ወደሱ እንዳተኮሩ ተመለከተ።

ከዛ እሱም ፈገግ በማለት "እሱ (ፈረሱ) በምፈልገው ጊዜ ጥሎኝኮ አልሔደም ታዲያ እኔስ በዚህ ወቅት እንዴት ብቻውን ጥዬው ልሔድ ይቻለኛል።!? በማለት በለሆሳስ ተናገረ።

በንፋሱ በወጀቡ ጊዜ አብረውህ የነበሩትን ፀሀይ ወጣ ብራ ሆነ ብለህ ጥለኻቸው አትሒድ !!

ሰናይ ቀን ይሁንላቹ ❤️❤️

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

💔😥❤✌️ አባት ለአንዲት ሴት ልጁ እንዲህ አላት፦

ልጄ ሆይ፦ እባክሽን ስራዬ የፅዳት ሰራተኛ መሆኑን ለማንም አትናገሪ ይዘባበቱብሻል፣" አላት። እሷም ከዛ በኋላ ከታች ያለውን ፎቶ በሶሻል ሚዲያ ላይ በመልቀቅ እንዲህ ብላ ፖስት አደረገችው።" አባቴ የፅዳት ሰራተኛ በመሆኑ እኮራበታለሁ፣ በጣምም እወደዋለሁ Ilove you dad" በማለት በይፋ አሳወቀች።✌️❤

Jemal Bireda Dawud Muzeyin

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ኢትዮጵያ ፣ ካናዳዊ አቀንቃኝ

አቤል ተስፋዬ ( ዘ ዊክንድ)

የመጀመሪያ ዘፋኝ እና ታዋቂ ሰው ለጋዛ ሰብአዊ እርዳታ የሚውል 2.5 ሚሊዮን ዶላር ሊለግስ ነው

ከ173,000 በላይ ቤተሰቦችን ለሁለት ሳምንታት ለመመገብ የሚያስችል አራት ሚሊዮን ምግቦች

ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ጥቅማቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ለጋዛ ለመናገር እየፈሩ ባለበት ሰአት አቤል ግን ከምን ይመጣብኛል ይልቅ ሰብአዊነትን ያስቀደመ መልካም ሰው መሆኑን አስመስክሯል

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#ያ_ኡመር...🥹🤎

ድርቅ እጅግ ህዝቡን በጎዳበት የራማዳ ወቅት ላይ፤ ሰሀቦች ቀን በቀን የሌሎች ሰሀቦች ጀናዛ ላይ በሚሰግዱበት ወቅት እና እንስሳቶች የሚበሉትን አጥተው ሰዎችን ማጥቃት የጀመሩበት ሰአት ኸሊፋው ኡመር በህዝቡ ጭንቀት ምክንያት መልካቸው ተቀየረ! ሰውነታቸው መነመነ። ለአላህ ባላቸው ፍራቻ ምክንያት እጅግ ተጎሳቆሉ! 💔

ኡስማን ኢብን አፋን: "ድርቁ እንዲቆም በጣም ዱዓ ማድረግ የጀመርነው በድርቁ ምክንያት ባጋጠመን መከራ ሳይሆን ኡመርን በዚህ ሁኔታው ልናጣው እንችላለን ብለን በመፍራት ነው።" በማለት ይናገራል! ሰይዲና ኡመር ምነኛ አስፈላጊ ሰው ቢሆኑ ነው ሰሐቦች ከራሳቸው ህመም ኸሊፋውን ማጣታቸው ያሰጋቸው? ሰላሙን አለይክ ያ አሚረል ሙዕሚኒን! 🥺🤎

በድርቁ ሰአት የሙዕሚኖች መሪ ድርቁ እስኪያልፍ እና ህብረተሰቡ የሚበላውን እስኪያገኝ ድረስ እርጎ፤ ወተት፤ ቅቤ እና ስጋ ላለመብላት ለራሳቸው ቃል ገቡ። አንድ ቀን ከረሐባቸው የተነሳ ሆዳቸው መጮህ ጀመረ፤ ከዛም አሚሩ ለሆዳቸው እንዲህ አሉት:

"قرقري أو لا تقرقري لن تذوقي طعم اللحم حتى يشبع أطفال المسلمين"

"ብታጉረመርም ባታጉረመርም ሙስሊም ልጆች መብላት እስካልቻሉ ድረስ አትሞላም።" አሉት የሚያጉረመርመውን ሆዳቸውን! ... ያ አላህ! ምን አይነት ስብዕና ነው? ...ጌታዬ ጉርብትናህን። 🥺

ሰዎች እንደ ሐዲያ ምግብ ሲሰጧቸው ለራሳቸው ሳይቀምሱ በህዝቦቻቸው ዘንድ ያከፋፍሉት ነበር። በዚሁ ድርቅ ወቅት አንድ ቀን ወደ ቤታቸው ሲገቡ ልጃቸው አብደላህ ሐባብ እየበላ ይመለከታሉ! ይህንን ሲመለከቱ ኡመር በድንጋጤ ልጃቸውን ሐባቡን ሊቀሙት ሲሉ ሚስታቸው: "ያ ኡመር! በራሱ ገንዘብ ነው የገዛው ይብላ።" አለች ... ኡመሩል ፋሩቅ ምን አሉ?: "የዚህ ኡማ ልጆች ይህንን መብላት እስካልጀመሩ ድረስ የኛ ልጅ መብላት የለበትም።" ብለው መለሱላት! ሱብሓነላህ ሰውነት'ን ኖረው አለፉበት ኡመር! ሰላሙን አለይክ ያ ኡመሩል ፋሩቅ! 🤎

አንድ ታዋቂ አባባል'ም አላቸው:

"كيف يعنيني شأن الرعية إذا لم يمسّني ما مسّهم”

"እንዴት እራሴን እንደ እረኛ(ጠባቂ) አስባለሁ የምጠብቃቸው አካሎች የተነኩበት ነገር ሳይነካኝ?" በማለት የህዝባቸውን መከራ አብረው ይጋሩ ነበር። ለህዝባቸው ያላቸውን ውዴታ፤ ፍቅር እንክብካቤ እና ሀላፊነት በብዙ አጋጣሚዎቻቸው ላይ እንመለከታለን! 🤎

ሰላመን ያ አሚረል ሙዕሚኒን! 🫶🏽

በዚህ unfair አለም ሰይዲና ኡመርን አለመናፈቅ አይቻልም!

Nadia Biya

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group