UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Hussen Gebi shared a
Translation is not possible.

🕌ሀዲስ

የዛሬው ሀዲስ

.....................................

አቡ ሁሬይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት አንድ ሰው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ቀረበና፡- ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሆይ! ይበልጥ ሎጎዳኘው የሚገባኝ ሰው ማንነው?›› አላቸው፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹እናትህ›› አሉት፤ በድጋሚ ‹‹ከዚያስ ቀጥሎ ማንነው?›› አላቸው፤ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹እናትህ›› አሉት፡፡ ሰውዬው ‹‹ከዚያስ ቀጥሎ?›› አላቸው፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹እናትህ›› አሉት፡፡ (ለአራተኛ ጊዜ) ‹‹ከዚያስ ቀጥሎ?›› አላቸው፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹አባትህ› አሉት፡፡

📚ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

በሌላ ዘገባ ደግሞ ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ይበልጥ ልጎዳኘው የሚገባኝ ሰው ማንነው?›› ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹እናትህ ከዚያም እናትህን ከዚያም እናትህን ከዚያም የቅርብ ዘመድህን ከዚያም የቅርብ ዘመድህን›› አሉት፡፡

1️⃣ እናት ከልጁ መወለድ እስከ ሞቱ ድረስ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለችና የምትከፍልም በመሆኗ ከፍተኛ አትኩሮት ለመስጠት ነው፡፡

2️⃣ የእናት ደረጃ ከአባት የበለጠ ከፍተኛ ስፍራ እንዳለው ማሳያ ነው፡፡

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Hussen Gebi shared a
Translation is not possible.

ሙዓዊያ እና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁማ በተጋጩ ጊዜ ሁለት ኢስላማዊ ስረወ መንግስት ተመሰረተ የሮሙ ንጉስ ይህን ሰምቶ እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈ ፦

" ከሮም ንጉሰ ነገስት ለሙስሊሞች መሪ ሙዐዊያ አቡ ሱፍያን!! 

ባንተ እና በዐሊይ መካከል የተከሰተውን ግጭትሰምተናል ስለዚህም ለሙስሊሞች መሪ አንተ መሆን እንዳለብህም ስለምናምን አንተ ፍቃድህ ከሆነ የዐሊይን ጭንቅላት 

ቀንጥሶ የሚያመጣልህን ወታደር ልላክልህ "

ይህ ደብዳቤ ሙዐዊያ ጋር እንደደረሰም ሙዓዊያም :-

" ከሙዓዊያ ለሮም መሪ!!! ሁለት ወንድማማቾች ስለተጣሉ አንተ ምን አገባህ? አፍህን የማትዘጋ ከሆነ ጅማሬው እኔ ጋ የሆነ 

እና ፍፃሜው አንተ ጋ የሆነ ሰራዊት ልኬ አንገትህን በማስቀንጠስ ለዐሊይ በስጦታ መልኩ አበረክትለታለሁ "

#ይህ_ትክክለኛ_ሙስሊሞች_ሳለን_ነው‼️

============================

ኻሊድ ኢብን ወሊድ ለፐርሺያው ንጉሰ ነገስት እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈለት፦

"ስለም ትድናለህ። እንቢ ያልክ እንደሆን ግን፤ እናንተ ህይወትን የምትወዱትን ያህል ሞትን የሚወዱ ሰራዊቶችን ይዤልህ 

እመጣለሁ።" 

ንጉሱ ይህን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የቻይናውን ንጉስ የጦር እርዳታ ሊለምነው ደብዳቤ ፃፈለት። የቻይናውም ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ መልሶ ላከለት። 

"ንጉስ ሆይ! ተራራን እንኳን ለመናድ ካሰቡ ምንም ከማያግዳቸው ወታደሮች ጋር ለመጋፈጥ አቅሙ ስለሌለኝ 

ጥያቄህን መፈፀም አልችልም።"

#ምን_ያህል_ሀያላን_እንደነበርን_ተመልከቱ ‼️

============================

በደውለቱል ዑስማኒያ የአገዛዝ ዘመን የሙስሊም ወታደሮች የጦር መርከቦቻቸውን ይዘው በአውሮፓ ደሴቶች ሲያልፉ በአከባቢው ያሉ አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ሙስሊሞች መጥተው ፈትህ እንዳያደርጉ በመፍራት ከበሮ ከመምታት እና ምንም አይነት ድምፅ ከማሰማት ይቆጠቡ ነበር። 

#ያኔ_ጀግና_ሳለን‼️

============================

በደውለቱል ኡስማኒያ የአገዛዝ ዘመን በያንዳንዱ ቤት ደጅ ላይ ሁለት የበር ማንኳኩያዎች ይኖራሉ። አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ትንሽ ነው። በትልቀኛው ከተንኳኳ አንኳኪው ወንድ ነውና በሩን ሊከፍት 

የሚመጣው ወንድ ይሆናል። ነገር ግን በትንሸኛዋ ከተንኳኳ አንኳኪዋ ሴት መሆኗ ስለሚታወቅ ሴት ትከፍትላታለች። 

በዚያ ምርጥ ዘመን አንድ ቤት ውስጥ ሰው ከታመመ ደጅ ላይ ቀይ አበባ ይንጠለጠል ነበር። ያን አበባ የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ 

እዚያ ቤት በሽተኛ መኖሩን ስለሚያውቁ በበሩ ሲያልፉ ድምፃቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር። 

#ሹፍ_ምን_እንመስል_እንደነበር ‼️

============================

ጊዜው ሰላሀዱን አል አዩቢ በይተል መቅዲስን ባስመለሰበት ግዜ ነበር። እና ጦርነቱ ነገውን ሊጀመር ማታ ላይ የጦር መሪው ሰላሀዲን የወታደሮቹን ድንኳን እየዞረ ሲያዳምጥ፤ ግማሹ ለይል ይሰግዳል፣ ሌላው ቁርአን ይቀራል፣ የተቀሩት ደግሞ ይዘክራሉ። 

ግን ድንገት በሆነ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ በድንኳኑ ውስጥ ያሉት ሁሉም ተኝተው ነበር። ይህን ጊዜ ፦"በዚህች ድንኳን አዳሪዎች 

ምክንያት ልንሸነፍ እንችላለን" ብሎ አለፈ። 

#ማንተኛበት_ዘመን‼️ 

___ 

ቀደምት ዑለማዎች በሶስት ነገራት አደራ ይባባሉ ነበር። 

1.ሰውዬው በሱ እና በአሏህ መካከል ያለውን ግንኙነት ካሳመረ፤በሱ እና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ያምርለታል። 

2.ሰውዬው ሚስጥራዊ ተግባሩን ካሳመረ አሏህ ይፋዊ ተግባሩን ያሳምርለታል። 

3፦ሰውዬው የአኺራው ጉዳይ ካስጨነቀው አሏህ የዱንያውንም የአኺራውንም ጉዳይ ያግራራለታል። 

============================

#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው‼️ 

ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።  አዎ ትልቁ ኪሳራ ይህ ነው!!

በእለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ ቁርአንን መቅራት ካልተካተተ ይህም ትልቅ ኪሳራ ነው። 

ይህን ፅሁፍ በማሰራጨት ጓደኛህን/ሽን እንድታነቃው ይከጀላል!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Hussen Gebi shared a
Translation is not possible.

Peace be upon you

Dear Umma Life family, may God's peace, mercy and blessings be upon you and our Palestinian people, may God remove the evil of the enemy and grant them victory

May Allah protect them and you should be strong in your dua and don't get distracted. Their pain, their suffering is our pain and suffering. A Muslim is one with his believing brother in everything.

The other thing is that you are all invited to this media, help each other and follow each other without paying each other. Pray for our fellow Palestinians!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!""""

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Hussen Gebi shared a
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Hussen Gebi Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group