🌐ካነበብኩት ላካፍላችሁ!
✍️ባል ወደ ቤት ሲገባ ሚስቱ የአልጋውን ጫፍ ተደግፋ ተንሰቅስቃ እያነባች አገኛት። ደነገጠ ስታለቅስ ሲያያት ሆዱ ተላወሰ። ያፈቅራት ነበርና ሐዘኗ አሳዘነው። አቅፎ ደግፎ ግንባሯን እየሳመ ለምን እንደምታለቅስ ጠየቀ።
"ከቤታችን ፊት ለፊት የሚገኘው ዛፍ ላይ ያሉት ወፎች ዘወትር ልብሴን ስቀይር ፀጉሬን ያዩብኛል። ይህም አላህን ማመፅ እንዳይሆንብኝ ብዬ እፈራለሁ ለዚህ ነው የማለቅሰው" ብላ መለሰችለት
ባል በንጽሕናዋና አላህን በመፍራቷ ተደንቆ በዓይኖቿ መካከል ሳማትና መጥረቢያውን አውጥቶ ከቤታቸው ደጃፍ ላይ የበቀለውን ዛፍ ቆረጠ።
ከሳምንቱ መጨረሻ በአንደኛው ቀን ስራ አድክሞት ያለ ወትሮው ወደቤቱ አቀና። ሌላ ጊዜ ከሚገባበት ሰዓት ቀደም ብሎ ወደ ቤት ተመለሰ። በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ሲዘልቅ ሚስቱ በሌላ ወንድ እቅፍ ውስጥ ተኝታ አገኛት። አልጋው ላይ እሱ የገዛውን አንሶላ ከሌላ ወንድ ጋር ለብሳ መርፌና ክር ሆና ተመለከታት።
የሚያስፈልገውን እቃ ሻንጣው ውስጥ ሸክፎ ምንም ሳይናገር የትውልድ ቀየውን ለቆ ወጣ።
ራቅ ወዳለ ሥፍራ ተጓዘ። መንገድ በማቋረጥ ላይ ሳለ ከአንድ ቤተ መንግስት አቅራቢያ ሰዎች ተሰብስበው ተመለከተ። ለምን እንደተሰበሰቡ ሲጠይቃቸው የንጉሱ ግምጃ ቤት ተዘርፎ ሌባው አለመገኘቱን ነገሩት።
በዚህ መሐል በእግሮቹ ጣት ጫፍ በቀስታ የሚራመድ ሰው ተመለከተ። ስለማንነቱም ጠየቀ "የከተማው ሸይኽ ነው ጉንዳን ረግጦ አላህ ዘንድ እንዳይጠየቅ በዝግታ ይጓዛል ከአላህ ፍራቻ ብዛት የጉንዳኖችን ህይወት ላለመቅጠፍ በመስጋት በቀስታ ይራመዳል" ብለው መለሱለት።
ወደ ንጉሡ ውሰዱኝ አለ። ወሰዱት። ለንጉሱም የአንተን ግምጃ ቤት የዘረፈው በጣቶቹ የሚራመደው ሸይኽ ነው። እሱ ሆኖ ካልተገኘ ፍርዴ ሞት ይሁን አለ። ንጉሱ ተገረመ በተቅዋው የሚታወቀው ሸይኽ እንዴት ሊዘርፈኝ ይችላል ሲል ራሱን ጠየቀ።
ወታደሮቹ ሸይኹን አምጥተው ከንጉሱ ፊት አቀረቡት። ምርመራው ተጀመረ ሸይኹ መስረቁን አምኖ ተቀበለ። መዝረፉም ተረጋገጠ።
ንጉሱም ወደ ሰውየው ዞሮ ሌባው እሱ መሆኑን እንዴት አወቅክ ሲል ጠየቀው
ሰውየውም፡-
"አላህን እንፈራለን ብለው ራሳቸውን የሚያጋንኑ ሰዎችን ከተመለከትክ ወንጀላቸውን ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት መሆኑን እወቁ" ሲል መለሰለትና በሩን ከፍቶ ከቤተ መንግስቱ ግቢ ወጣ።
የአመለካከት ሊቅ ነን የሚሉ የተቅዋቸውን ጥግ ለማሳየት የሚሮጡ ሼኾችን ማክበር ብቻም ሳይሆን መጠንቀቁ አይከፋም በጠላት ተጠልፈው ኢስላምን ለማጥፋት የሚኳትኑ መኖራቸውንም እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ።
👌ዲነኛነን አላህን ፈሪ ነን ካሉት ለብሰዉ ካየናቸዉ ይልቅ እነሱን መመዘን በልብሳቸዉ ሳይሆን በአመለካከታቸዉ በቤት ባህሪያቸዉ ሳይሆን በትምህርት ቤት ባህሪያቸዉ ቢታዩ ባይ ነኝ፡፡