Translation is not possible.
ለውዴታቸው መመዘኛው ውልደታቸውን አስቦ መፈንጠዝ ቢሆን በመወለዳቸው ከአቡለሀብ በላይ ማን ፈነጠዘ እና?
መውደድ ትርጉም ሚሰጠው.... ተወዳጁ አካል እንድትወደው በሚፈልገው መንገድ ስትወደው ነው። ለራሱ ክፉ ደጉን ያለየ ነው ብለህ እስካልጠረጠርክ በቀር። አሽረፈል ኸልቅ ደሞ ከዚህ የጠሩ እንዴት ቢወደዱ እንደሚገባቸው ያወቁ፣ መለኮታዊው ትእዛዝም በዚህ ላይ ሚመራቸው ናቸው።
ለዚህም ስል እንድወዳቸው በፈለጉት መልክ ለመውደድ በማረገው ሙከራዬ ምክንያት መውሊዳቸውን አላከብርም🙌
አክባሪ እና ብቸኛ ወዳጃቸው ነኝ ባዩንም... እንቢተኛ ሁነህባቸዋል ብዬ በሳቸው ጠላትነት ልፈረጀው ሳልዳፈር እኔን በታዛዥነቴ ምክንያት ጠላት ለሚለኝ ቂል አልረበሽም😊
ምክንያቱም "መወለዳቸውን ጠልታ ነው" ባለኝ ጭፍን ሎጂኩ አምሳያ ሄጄ "በመሞታቸው ተደስተህ ነው" በዛሬ ቀን ምደልቀው ብሎ መበሻሸቅ አብሮ ቂል ከመሆን የዘለለ ምጥቀት ስለማይጠይቅ።
ብቻ ግን ልክ በእንደዛሬ በረቢዕ 12 በ 11 ኛወ አመተ ሂጅራ ሞቅ ባለው ንጋት ረሱላችን اللَّهُمَّ الرفيق الأعلى ብለው ወደ ምርጫዊ የተሻለ የህይወት ጉዟቸው ተሸጋግረዋል። ለእኛ ከየትኛውም ጉድለት በላይ ይህ ክስተት አጉድሎብናል።
ምድር የመደምደሚያ ነብይዋን በሞት ከመሸኘትዋ በላይ ምንም ፅልመት አይኖርባትም😥
ከረሱል ሞት ተያይዞ ምን ክስተት ይበልጥ ልባችሁን ይነካዋል?
Send as a message
Share on my page
Share in the group