UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ያ ኢላሂ አንተው ሁናቸው🤲

‌‎« أَمَّن يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ السُّوءَ»

«ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ…»

[አ-ን'ነምል: 62]

قيل: المُضطر هو الذي انقطعت فيه كل السبل ولم يبقَ له ناصر أو مغيث........سوى الله.

«ችግረኛ/የተጨናነቀ» ማለት መንገዱ ሁሉ የተዘጋበት/የተቋረጠበት፣ ለርሱ ከአላህ ውጭ ረዳትም ሆነ የሚጠጋበት አንድም ያላገኘ ማለት ነው።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
7 month Translate
Translation is not possible.

amiiin yaa rabbiii

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የዓለም ህዝብ ግን አይገርምም⁉️

=======================

(ዓለም በዚህ ዘመን አይታው የማታውቀው የጦር ወንጀልና የዘር ጭፍጨፋ በጘዝ'ዛ)

||

✍ 365 km² ስፋት ባላት አነስተኛ ከተማ ውስጥ 2.3+ ሚሊዮን ዜጎች ተጠጋግተው ይኖሩባታል። በዚህች densely populated በሆነች ከተማ ላይ ለተከታታይ 3 ሳምንታት ያላባራ ከ12 ሺህ ቶን በላይ ቦምብ ሲዘንብ፤ በዚህም ሳቢያ፦

1) በትንሹ 7,028 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙስሊሞች ሲገደሉ፣

2) ከ70% በላይ የሚሆኑት ህፃናትና ሴቶች ሲሆኑ (2,913 ህፃናትና 1,709 ሴቶች)፣

3) 18,482 የሚሆኑት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ሲዳረጉ፣

4) ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 481 የሚሆኑት ሲገደሉ (ከመካከላቸው 209 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው።)፣

5) ከ1,650 በላይ የሚሆኑት ጀናዛቸው እንኳ ሳይገኝ እስካሁን ድረስ በቦምብ በፈራረሱት ህንፃዎች ስር ሲሆኑ (ከመካከላቸው 940 ህፃናት አሉበት።)፣

6) 731 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙሉ ቤተሰቦች ሲገደሉ፣

⑦) 101 የጤና ባለሙያዎች ሲገደሉና 100 የሚሆኑት ሲቆስሉ፣

⑧) 12 ሆስፒታሎችና 32 የጤና ማዕከላት በነዳጅ እጥረትና በቦምብ ጥቃት ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ፣

9) በኢንኩቤተር ውስጥ የሚገኙ ከ130 በላይ የሚሆኑ ህፃናት ያሉበት ሆስፒታል ባጋጠመው በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ነፍሳቸው በእንጥልጥል ላይ ሲገኝ፣

⑩) ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ንጹሐን ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች፣ በት/ቤቶች፣ በሆስፒታል ግቢዎች፣ በመስጂዶችና ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ሳለ በዛው ባሉበት ጥቃቱ ሲያገኛቸው…

(ከሰው ነፍስ አይበልጥምና ወደ አመድነት ስለተቀየሩት ውብ ህንፃዎችና መሠረተ ልማቶችማ አውርተን አንዘልቀውም።)

የሰለጠነ ተብዬው ዓለም አሁንም «ጦርነቱ ይቁም!» ከማለት ይልቅ «እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት፣ ሐማስ መጥፋቱን ማረጋገጥ አለባት፣ ከጎንሽ ነን፣ ሐማስ ሽብርተኛ ነው፣ በሐማስ ጥቃት ለሞቱተረ እስራኤላዊያን አዝነናል!…» እያሉ ነው።

ትንሽ አሻሻልን የሚሉት ደግሞ ጦርነቱ መቆም የለበትም፤ ግን የተወሰነች እርዳታ ይግባላቸው ይላሉ።

እስካሁን በጋዛ መብራት የለ፣ ውሃ የለ፣ ምግብ የለ፣ ነዳጅ የለ…። በዚህ የተነሳ የቆሰሉትና መደበኛ ህመም የሚታመሙትም መታከም አልቻሉም።

ዙሪያውን በከበባ ስለሆነ ለጠናበት ታማሚ የውጭ ሕክምና እንዲያገኝ ማድረግ አልተቻለም።

እስራኤል ከላይ በአየር ከምታዘንበው የቦምብ ዝናብ ባሻገር ከምግብና ውሃ እንዲሁም ከሕክምና ከልክላ በጅምላ ጭፍጨፋ የጦር ወንጀልና የዘር ማፅዳት ወንጀል በመፈጸም ላይ ትገኛለች። ይህ ሁሉ የሚሆነው ዓለም እያዬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ተመድ ተብዬውም ሆነ የትኛውም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚል ተቋም ሁሉ የውሃ ሽታ ሆኗል። የነርሱ ህግ እነርሱን ለማዳን እንጂ ለሌላው አይሠራም። እነርሱ ዘንድ የሙስሊም፣ የዓረብና የአፍሪካዊ ሞት ከውሻቸው ሞት በታች ነው።

ግን ነፍስ ሁሉ እኩል ናትና የእጃቸውን አንድ ቀን ማግኘት አይችሉም። ነገ ላይ በሌላ የነርሱ አካል ላይ ጥቃት ሲፈጸም በሚዲያቸውም ሆነ ባልተጻፈው ህጋቸው ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ሲለፍፉ እናገኛቸዋለን።

አላህ ውርደታቸውን ያቅርበው፤ ለተበዳዮች ነስሩን ያፍጥነው።

አላህ የአሸናፊዎች ሁሉ አሸናፊ የሆነ ጥበበኛና ታጋሽ ጌታ ነው። አንድ ቀን አይርላቸውም።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ይህ የአልጀዚራህ ጋዜጠኛ ከደቂቃዎች በፊት ከጋዛ የቀጥታ ስርጭት እያስተላለፈ ሳለ፤ ከቆይታዎች በኋላ ሚስቱ፣ ትልቁ ልጁ፣ ትንሹ ልጁና ሴት ልጁ እስራኤል ባዘነበችው የቦምብ ጥቃት መገደ'ላቸውን ሰማ።

አላህ የዚህችን አረ'መኔ መጨረሻዋ ያድርገው።

የስንቱን ቤተሰብ ጨረሰች፣ የተወለዱ ህፃናት ሳይቀሩ ቀጠፈች፣ ህልማቸውን አቀጨጨች፣ ህፃናት ያለ ወላጅ፥ ወላጆች ያለ ጧሪ ቀባሪ እንዲቀሩ አደረገች። አላህ ውርደቷን አፋጥኖ መጥፎ ፍጻሜዋን ያሳየን።

BREAKING! Al Jazeera reporter Wael al-Dahdouh bids farewell to his grandchildren, his wife, son and daughter who were just killed after Israeli warplanes bombed their home in #gaza city.

#palestine #gaza

70 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group