Abedulwasil Edris Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

About me

I am worker. i love reading religeus books like kuran and hadith

Followings
1
Translation is not possible.

በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ የቀጠለው እልቂት እና የጅምላ ሰለባ።

4 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የጋዛ ሴቶች ጉዳይ ሒጃብ የማውለቅ ቢሆን ኖሮ አውሮፓዊያን የጦር መርከቦቻቸውን ይልኩላቸው ነበር። የጋዛ ወንዶች ጉዳይ የግብረሰዶማዊነት ጉዳይ ቢሆን ኖሮ አሜሪካ የአውሮፕላን ተሸካሚዎችን ትልክላቸው ነበር። የጋዛ ህጻናት ጉዳይ ጾታ የመቀየር ጉዳይ ቢሆን ኖሮ የተባበሩት መንግስታት በአንድ ድምፅ ያለቅስላቸው ነበር። ነገር ግን ጉዳዩ የእምነት እና የክህደት ሆነ። እምነት "የቲም" ሲሆን ክህደት ግን ብዙ ቤተሰቦች አሉት።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

⚡️🇷🇺В противостоянии с ХАМАС, Израиль не имеет права на самооборону, заявил представитель России при ООН Василий Небензя.

Он связал это с тем, что Израиль является «оккупирующим государством».

🌍 In the confrontation with Hamas, Israel has no right to self-defense, said Russia's representative to the UN Vasily Nebenzia.

He attributed this to the fact that Israel is an "occupying State".

Allahu a'alam (God Knows Best).

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የሙስሊም ሞቱ ከአላህ ወደ አላህ መሰደድ ነው። ልዩነቱ ከዱኒያዊ አለም ወደ አኬራ መሄድ ነው። ከዱኒያ ችግር ሃሳብ ወደ ምቾት አለም መንጎድ ነው። የካዱ ሰዎች መኖርን እንደሚወዱት ሁሉ ሙስሊሞች መሞትን ይወዳሉ። ይሄን ስንል ግን ሀቅን ይዘን ነው ሙስሊም ለሙስሊም ወንድሙ ነው። የሙስሊም ወንድሙ ህመም ሊሰማን ህመማቸው ህመማችን ነው።

┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

«ብዙዎች ስለ አል-አቅሷ የማያውቋቸው 8 ነገሮች»

ከከዓባ በ40 ዓመት ዕድሜ ስለሚያንሰው የምድራችን ሁለተኛው መስጂድና የኢስላም ሶስተኛው ቅዱስ ቦታ ስለሆነው አል-አቅሷ መስጂድ ብዙዎች የማያውቋቸውን 8 ነገሮችን ላካፍላችሁ፦

8፦ አንድ መስጅድ አይደለም

ብዙዎች መስጂደል አቅሷ ማለት በደቡባዊ ጫፍ የሚገኘው ባለ ብራማው ጉልላት «ቂብሊይ» መስጅድ ብቻ እንደሆነ ያስባሉ። ነገርግን እሱ ከአቅሷ መስጅዶች አንዱ እንጅ ብቸኛው አይደለም። መስጂደል አቅሷ የሚባለው መስጂዶቹና ዙራያውን ያለው «ቦታ» ነው።

ነቢዩ (ዐሰወ) በሌሊት ወደ አቅሷ በተጓዙበት ወቅት በቦታው ምንም መስጂድ እንዳልነበረ የገለፁ የታሪክ ጸሐፊዎች አሉ። በወቅቱ የነበረው የሮማ ገዢ አይሁዶች በየጊዜው እያደሱ ይጠቀሙበት የነበረውን መስጂድ አፍርሶት ነበረና። እናም ነቢዩ (ዐሰወ) በዚያ ሌሊት ነቢያቶችን ኢማም ሆነው ያሰገዱት መስጂዱ በፈረሰበት ቦታ ላይ እንጅ በቤት ውስጥ አልነበረም። መስጂድ ማለት ደግሞ መስገጃ ቦታ ማለት እንጂ የግድ ቤት ማለት ስላልሆነ አላህ በተከበረው ቃሉ ‹‹የሩቁ መስጂድ›› ሲል ጠርቶታል።

አቅሷን ከሮማውያን ነፃ ያወጣው ኸሊፋው ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረዐ) ሲሆኑ በጊዜው አነስተኛ መስጅድ ሰርተውበት ነበር። በኋላም ኸሊፋ አብደል መሊክ መስፋፊያ በማድረግ ባለ ወርቃማውን ጉልላት «ቁበት አል-ሳኽራህ» ሊሰራ ችሏል። ከዚያ በኋላ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከሁለት ጊዜ በላይ የፈረሰ ሲሆን በጊዜው የነበሩ የሙስሊም መሪዎች እንደገና ግንባታ አድርገዋል። በአሁኑ ሰዓት ከሁለቱ መስጂዶች በተጨማሪ ቡራቅ፣ መርዋኒ እና ሌሎችም መስጂዶች ይገኛሉ።

7፦ የመቃብር ቦታ ነው

በአቅሷ መስጂድ (ግቢ) ውስጥ ምን ያህል ነቢያቶችና ሰሃባዎች እንደተቀበሩ አይታወቅም። ነገርግን ይቀበሩ እንደነበረ ይታወቃል። ለአብነት ነቢዩላህ ሱለይማን የተቀበሩት አቅሷ ውስጥ ነው። የትኛው ቦታ የትኛው አካባቢ የሚለው ግን አይታወቅም።

6፦ የቆሻሻ መጣያ ነበር

ሮማውያን ከነቢዩ (ዐሰወ) መምጣት በፊት ቁዱስን ለረጂም ጊዜያት ይዘውት ነበር። እናም አይሁዶች ለቦታው ያላቸውን ክብር ሲያዩ መስጂዱን አፈረሱና ቆሻሻ መጣያ አደረጉት። በኋላም ዐመር ኢብኑል ኸጧብ (ረዐ) ኸሊፋ ሲሆኑ ሮማውያኑን በማባረር በእጃቸው ሳይቀር ቆሻውውን በማጽዳት የመጀመሪያው ሰው ሆኑ።

5፦ አል-ገዛሊ የኖሩበት አገር

በኢስላም ታሪክ የተሃድሶ መሃንዲስ የሚባሉትና በ10ኛው ክፍለ ዘመን የኖሩት ኢማም አቡ ሐሚድ አል-ገዛሊ ብርቅ ስራዎቻቸውን ለዓለም ያበረከቱት ከዚህ ቅዱስ ቦታ ነው። አል-ገዛሊ ፐርሺያዊ ሲሆኑ አላህ በየክፍለ ዘመናቱ ቢድዓና ኩፍር ሲስፋፋ ዲኑን ለማደስ ከሚልካቸው ታላላቅ ኡለማዎች ውስጥ አንዱ እንደሆኑ ይነገራል።

4፦ ቤተ-ክርስቲያን፣ ቤተ-መንግስት እንዲሁም መገደያ ቦታ ነበር

ሮማውያን በመስቀል ጦርነት ወቅት አቅሷን ከተቆጣጠሩ በኋላ መስጂዶቹን ወደ ቤተ-ክርስቲያንነት ቀይረዋቸው ነበር። አስተዳደሩንም እዚያው በማድረግ እንደ ቤተ-መንግስትነት ይጠቀሙበት ነበር። በጦርነቱም የተማረኩትን 70‚000 ሙስሊሞች በወርቃማው መስጂድ በር ላይ አርደዋቸዋል። በኋላም ሰላሁዲን በመራው ጦር ሮማውያን ተሸንፈው መስጂዶቹ እንደገና ታድሰው ተሰርተዋል። አቅሷ እስከ 1967 አይሁዶች አካባቢውን እስከወረሩበት ጊዜ ድረስ በሙስሊሞች እጅ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግን በፅዮናውያኑ ቁጥጥር ስር ይገኛል።

3፦ የኑረዲን ሚንበር

ኑረዲን ዚንጊ ቁዱስ በመስቀለኞች ከተያዘች በኋላ ነፃ ለማውጣት ይታገል የነበሩት ቀዳሚ አሚር ነው። አቅሷን በእጃችን የምናስገባበት ጊዜ ቅርብ ነው ብሎ ያምን ነበርም። ኑረዲን ድሉን ባያይም ምኞቱ በተከታዩ ሰላሁዲን ሊሳካ ችሏል። እናም እሱን ለማስታወስ ሲባል የኑረዲን ሚንበር በአቅሷ ውስጥ ታነፀለት። ይሁን እንጅ ይህ ሚንበር አይሁዶች ባደረሱበት ቃጠሎ ገፅታው ጠፍቷል።

2፦ የባለ ወርቃማው ጉልላት መልክ

ወርቃማው መስጂድ የአሁኑን መልክ የያዘው በኡስማኒያው መሪ ሱለይማን ዘመን ነው። ከዚያ በፊት ቅርፁም ሆነ መልኩ የተለያየ እንደነበረ ይነገራል።

1፦ ተደጋጋሚ ቃጠሎ

ፅዮናውያን ቁዱስን ከተቆጣጠሩ በኋላ ሙስሊሞችን ከአካባቢው ለማባረር በተለያየ ጊዜ መስጂዱን በእሳት አቃጥለውታል። በዚህም ምክንያት ብዙ ታሪካዊ መጽሐፍት፣ በየዘመኑ የነበሩ ኸሊፋዎች ያስቀመጧቸው እቃዎችና ቅርሳቅርሶች ሊወድሙ ችለዋል።

🌟🌟🌟🌟🌟

ኢንሻኣላህ ቁዱስ በእርግጥ እንደገና ነፃ ትወጣለች። በማን ካላችሁ ጉልበት ባለው ሃይል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group