zahara ahmed Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1
zahara ahmed shared a
Translation is not possible.

ዓጃኢብ የሆነ ታሪክ

November 26, 2022

አጃዒብ የሆነ ታሪክ ላካፍላችሁ‼

ዲኔ ላይ ደህና ነኝ፡፡ መልክ አለኝ ባይባልም አልከፋም፡፡ በባህሪዬ ጥሩ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡፡ ከቤተሰብ ሳልርቅ ነው ያደግኩት፡፡ የልጅነት ጊዜዬ አልፎ ወጣትነት መጣ፡፡ እንደማንኛዋም ሴት ትዳር አሰብኩ፡፡ ግና በማላውቀው ምክንያት ድርሻዬ ዘገየብኝ፡፡ ለጋብቻ የሚጠይቀኝ ጠፋ፡፡ ከኔ በኋላ የተወለዱ የቤተሰብም፣ የዘመድም፣ የሰፈርም ልጆች አንድ በአንድ አገቡ፡፡ ወለዱ፡፡ ልጆቻቸውም አደጉ፡፡ ሳላስበው 34 ዓመት ሆነኝ፡፡ እድሜዬን ሳስታውሰው ደነገጥኩ፡፡ ብቻዬን ቆሜ የቀረሁ እስኪመስለኝ ድረስ ተሰማኝ፡፡

⊙ የሆነ ጊዜ ከቅርብ ዘመድ የሆነ አንድ ወጣት ለጋብቻ ጠየቀኝ፡፡ ፈቃደኝነቴን ገለፅኩ፡፡ ሁለት ዓመት ይበልጠኛል፡፡ ዲኑም ፀባዩም ቆንጆ ነው፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ከሀሳቤ የተገላገልኩ መሰለኝ፡፡ ቤተሰብም ደስ አለው፡፡

≅ ኒካሕ ለማሰር ተዘጋጀን፡፡ አንዳንድ ጉዳዮችን ለመጨረስ ብሎ መታወቂያዬን ይዞ ሄደ፡፡ 

.

ከሁለት ቀን በኋላ ስልክ ተደወለልኝ፡፡ እናቱ ነበረች፡፡ እንደምትፈልገኝ ነገረችኝ፡፡ ምን ይሆን ብዬ እየበረርኩ ሄደኩኝ፡፡ ቤታቸው ገባሁ፡፡ ጥቂት ካወራን በኋላ መታወቂያዬን እያሳየችኝ እዚህ ላይ የተጠቀሰው የትውልድ ቀኔ ትክክል ስለመሆኑ ጠየቀችኝ፡፡ “አዎን! ትክክል ነው” አልኳት፡፡ 

“እንግዲያውስ አንች አርባ ተጠግተሻል መውለድ አትችይም” አለችኝ፡፡ “34 ዓመቴኮ ነው እንዴት አልችልም” አልኳት፡፡ 

“አይ … አንች ሰላሳ አልፎሻል እኔ ደግሞ ልጅ አይደለም ገና የልጅ ልጅ ማየት እፈልጋለሁ” አለች፡፡ ጋብቻው እንዲሰረዝ ሞገተች፡፡ ልጇንም አሳመነች። ለቤተሰቤ ምን እንደምላቸው እያሰላሰልኩ ተስፋ ቆርጬ ወደቤቴ ተመለስኩ፡፡

≅ ቀናት አለፉ፡፡ ድፍን ስድስት ወራትን በሐዘን አሳለፍኩ፡፡ ረጃጅም ቀንና ሌሊቶችን ስብሰለሰል ከረምኩ፡፡ በር በሩን ባይ እኔን ብሎ የሚመጣ ለኔ የተፃፈ ባል ጠፋ፡፡ ብቸኝነት፣ ባይተዋርነት፣ አጥንት ድረስ ዘልቆ ተሰማኝ፡፡ 

አባቴ ሁኔታዬን ይከታተላል፡፡ ስለኔ አብዝቶ ተጨነቀ፡፡ በመጨረሻም ከወንድሜ ጋር ለዑምራ እንድሄድ መከረኝ፡፡ “ሂጂና በተከበረው የአላህ ቤት አጠገብ ብሶትሽን ተናገሪ፤ የውስጥሽን የውስጥ አዋቂ ለሆነ ጌታ ተንፍሺ” አለኝ፡፡ 

ዑምራ ሄድኩኝ፡፡ የአላህ ቤት ከዕባ ፊት ቁጭ ብዬ ረጅም ዱዓ አደረግኩ፡፡ ለርሱ የውስጥ ስሜቴን ሁሉ አንሾካሸኩ፡፡ አለቀስኩ፤ ፈረጄን ያቀርብልኝ ዘንድ ተማፀንኩት፡፡

≅ የሆነ ቀን ሱንና ከሰገድኩ በኋላ ጥቂት ቁጭ አልኩ፡፡ ከኋላዬ አንዲት ሴት ባማረ ድምጽ ቁርኣንን ታነባለች። “የአላህ ችሮታ ብዙ ነው።” የሚል ትርጉም ያለውን የቁርኣን አንቀጽ ስታነብ ቀልቤ በተለየ መልኩ ወደዚያ ተሳበ፡፡ በቁርኣን ውስጥ የዚህ ዓይነት አንቀፅ ስለመኖሩ ገረመኝ፡፡ አላህ በችሮታው ያስበኝ ዘንድ ተማፀንኩት፡፡ 

ሴትዮዋ አየችኝ፡፡ ምን እንደሆንኩ ጠየቀችኝ፡፡ ሁኔታዬን ነገርኳት፡፡ “አብሽሪ” አለችኝ “አብሽሪ አላህም ያሰብሽውን ይሰጥሻል፤ ኢን ሻኣላህ ደስም ይልሻል” አለችኝ፡፡

≅ ዑምራውን አጠናቅቄ ተመለስኩ፡፡ ድንገት የረጅም ጊዜ ጓደኛዬንና ባሏን በአይሮፕላን ማረፊያው አገኘኋቸው፡፡ የባሏን ጓደኛ ለመቀበል እየጠበቁ ነበር፡፡ ሰላምታ አቅርቤላቸው ትንሽ እንዳወጋን ጓደኛቸው ደረሰና ተሰነባበትን፡፡ ወዲያው አባቴ ደርሶ ተቀበለኝ፡፡

ጥቂት ቀናት አለፉ፡፡ አሁን ከበፊቱ በተሻለ ልቤ በመጠኑ ሰክኗል፡፡ ዱዓዬን አላቋረጥኩም፡፡

የሆነ ቀን ያች ጓደኛዬ ደወለችልኝ ያን ቀን ያየኝ የባሏ ጓደኛ ለትዳር እንዳሰበኝ ነገረችኝ፡፡ በአንድ ቀን እይታ እንዴት ሊሆን ይችላል ብዬ ተገረምኩ፡፡ ግና ለአላህ ምን ይሳነዋል!!፡፡ 

በእውነቱ የማይታሰብ ነገር ሆነብኝ፤ ማመን አቃተኝ፡፡ እሱ ግን የምሩን ነበር፡፡ ስለኔ ሁሉን ነገር ከጓደኛዬ ከሰማ በኋላ አላንገራገረም፡፡ ወደ ቤተሰቦቼ ሽማግሌ ላከ፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ተስፋዬ ለመለመ፡፡ ወዜ ተመለሰ፡፡ ስሜቴ ታደሰ፡፡

በመጨረሻም አገባሁ። ጥሩ አፍቃሪ፣ መልካምና ደጋፊ፣ አዛኝና አሳቢ ባል … አላህ ሰጠኝ። ለኔም ለወላጆቹም ጥሩ ሰው ነበር፡፡

ካገባሁ ቀናት ሄዱ፣ ሁለትና ሶስት ወራት ተተኩ፡፡ ሌላ ሀሳብ አስጨነቀኝ፡፡ የእርግዝና ምልክት ናፈቀኝ፡፡ ግና እስካሁን ምንም አላስተዋልኩም፡፡ ሲበዛ አሳሰበኝ፡፡ እንቅልፍ አጣሁ፡፡

መመርመር እንደምፈልግ ለባሌ ነገርኩት፡፡ ወደ ሀኪም ቤት ሄድን፡፡ ጥቂት ቆይተን ለውጤቱ ተጠራን፡፡ ልቤ መምታቱን ጨመረ፡፡ ገና እንደገባሁ “መዳም መብሩክ!” አለችኝ ሀኪሟ፡፡

አርግዤ ነበር፡፡ ሱብሐነላህ! ለዚህ ብስራት ነበር እንዴ አላህ እዚህ ድረስ ያመጣኝ አልኩ፡፡

የእርግዝና ጊዜዬ ሰላማዊ ነበር፡፡ ግና የእድሜዬ መግፋት መጠነኛ ተጽእኖ ነበረው፡፡ ሆዴ እያደገ ሲመጣ ሰውነቴ ከበደኝ፡፡ እንደምንም የድካሙ ወራት አለፈ፡፡ የምጡ ቀን ደረሰ፡፡ በቀዶ ጥገና ነበር የወለድኩት፡፡ ከተሰጠኝ ሰመመን ስነቃ ቤተሰቦቼና ባለቤቴ ዙርያዬ ተሰብስበዋል፡፡ ይስቃሉ፣ ይጫወታሉ፡፡

“ምን ወለድኩ?” አልኳቸው ያለሁበትን ሁኔታ እያስታወስኩ፡፡

የተመካከሩ ነበር የሚመስለው፡፡ አንድ ላይ ሆነው ነበር ሰርፕራይዝ ያደረጉኝ “ወንድ እና ሴት!” አሉኝ፡፡ መንታ!!፡፡ የኔን መንቃት ሲጠብቅ የነበረው ባሌ በደስታ ተፍነከነከ፡፡ እኔንም ሀሴት የምሆነውን አሳጣኝ፡፡ ብችል ተነስቼ በዘለልኩ፡፡ ቁስሌ ገና እርጥብ ነው፡፡ ሱጁድም ራቀኝ፡፡ በተኛሁበት እንባዬ በሁለቱም ጉንጮቼ በኩል ዝም ብሎ ሲፈስ ይታወቀኛል፡፡ በትኩስ እንባ ፊቴ ታጠበ፡፡ ምስጋናዬን ያወጣሁበት ቃል እሱ ነበር፡፡ 

  የሚለውን የቁርኣን አንቀጽ አስታወስኩ፡፡ ስለ አላህ አሰብኩና በሀሳብ ርቄ ሄድኩ፡፡ የሱ ሥራ አብዝቶ ገረመኝ፡፡ እኛ ተስፋ እንቆርጣለን እንጂ እሱ ያዘጋጀልን ነገር አለ፡፡ እኛው ሁለት ልብ ሆነን ተቸገርን እንጂ በርግጠኝነት በአንድ ሆነን ልብ ይሰጠናል ብለን ብንለምነው ይሰጠናል፡፡ 

እኛው እንቸኩላለን እንጂ እሱ ለሁሉም ነገር መላና መፍትሄ አለው፤ ለሁሉም ነገር ምክንያትና ጊዜ አለው፡፡ ለአላህ ውሳኔ መታገስና ፈረጃውን መጠበቅ ትልቅ ዒባዳ ነው፡፡ 

እንኳን እኛ ነቢዩ ዘከርያም በልጅ እጦት ተፈትነዋል፡፡ “ጌታዬ ሆይ ብቻዬን አትተወኝ!!” ሲሉ ነበር ዱዓ ያደረጉት፡፡ 

ኢን ሻኣላህ ፈጣሪሽ ያሰብሽውን ይሰጥሻል፤ አንቺም አንድ ቀን ደስ ይልሻል፡፡

📚 “ቂሶሱን ሚነል ዋቂዕ” ከተሰኘ መጽሐፍ የተወሰደ፡፡ 

☑️ ተስፋ የቆረጡ ተስፋቸው ይለመልም ዘንድ እባክዎ ሼር ያድርጉ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
zahara ahmed shared a
Translation is not possible.

بسم الله الرحمن الرحيم

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

↪🟢👉በቁርዐን የተገለፁትን 25 ነብያቶች ያዉቃሉ?

1🔴👉 አደም (አለይሂ.ሰላም)

2🔴👉 ኢድሪስ (አለይሂሰሰላም)

3🔴👉 ኑህ (አለይሂሰላም)

4🔴👉 ሁድ (አለይሂሰላም)

5🔴👉 ሷሊህ (አለይሂሰላም)

6🔴👉 ኢብራሒም (አለይሂ ምሰላም )

7🔴👉 ሉጥ (አለይሂሰላም)

8🔴👉 እስማኤል (አለይሂሰላም)

9 🔴👉 ኢስሃቅ (አለይሂሰላም)

10🔴👉 ያዕቆብ (አለይሂሰላም)

11🔴👉 ዩሱፍ (አለይሂሰላም)

12🔴👉 አዩብ (አለይሂ.ሰላም)

13🔴👉 ሹዐይብ (አለይሂሰላም)

14🔴👉 ሃሩን (አለይሂሰላም)

15🔴👉 ሙሣ (አለይሂሰላም)

16🔴👉 ኢልያሥ (አለይሂሰላም)

17🔴👉 ዙልኪፍል (አለይሂሰላም)

18🔴👉 ዳዉድ (አለይሂሰላም)

19🔴👉 ሡለይማን (አለይሂሰላም)

20🔴👉 አልየሠዕ (አለይሂሰላም)

21🔴👉 ዩኑስ (አለይሂሰላም)

22🔴👉 ዘከሪያ (አለይሂ ሰላም )

23🔴👉 የህያ (አለይሂሰላም)

24🔴👉 ኢሳ (አለይሂ ሰላም) እና

25🔴👉 ሙሐመድ {{ሶለሏሁ አለይሂ ወሠለም}} ናቸዉ::

ከነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት 25🔴

ትታላላቅ ነብያቶች መካከል ደግሞ (አምሥቱ) ዑሉል-ዐዝም {መከራና ስቃይ ታጋሽ} በመባል ይታወቃሉ::

↪🔴እነሱም:-

👇👇👇👇👇👇

👉1🔴 ኑህ(አ.ሰ)

👉2 🔴ኢብራሂም(አ.ሰ)

👉3 🔴ኢሳ(አ.ሰ)

👉4 🔴ሙሣ (አ.ሰ)

👉5🔴 ነብዩ ሙሐመድ {ሰዐወ} ናቸዉ!!!

↪🔴👉፨በተጨማሪም:- በቁርዐን ዉስጥ የተጠቀሱትን አሥሩን

መላዕክቶችን, አንዲሁም የሥራ ድርሻቸዉንስ ምን ያህሎቻችን

ለማወቅ ጥረት አድርገናል???

↪🔴👇👇ዝርዝራቸዉን እነሆ! :-->.

👉➊🔴 ጂብሪል => መልዕክትን ማድረስ

👉➋ 🔴ሚካኤል => የዝናብ ተወካይ

👉➌🔴 አስራፊል=> የትንሳኤ ቀን ነፊ (ጥሩንባዉን)...

👉➍🔴 መለከል-መዉት=> ነፍስ አዉጭ

👉➎ 🔴ረቂብ ና አቲድ =>

ጥሩ ና መጥፎ ስራችንን የሚመዘግቡ

6🔴፨ ነኪር ና ሙንከር => ቀብር ዉሥጥ ጥያቄ የሚጠይቁ

👉7🔴፨ ማሊክ => የጀሀነም በር ዘበኛ

👉8🔴ሪድዋን => የጀነት በር ዘበኛ።

➖〰➖〰➖〰➖~ይህን ያውቁ ኖሯል?~~~

👉🔴ሶስቱ እጅግ በጣም አስፈሪ የጀሃነም ሸለቆዎች👉👉

➊🔴👉 አል ገይ ሸለቆ

➋🔴👉አል ዋይል ሸለቆ

➌🔴👉አል ሰቀር ሸለቆ

ዝርዝሩን እነሆ ፦

1ኛ🔴👉አል ገይ ሸለቆ

👇👇👇👇👇👇

----->ይህቺ የጀሃነም ሸለቆ (የተለያዩ ሰላቶችን አንድ ላይ ሰብስበው ለሚሰግዱ) {{ኡዝር ያለው ሲቀር}} እጅግ በጣም ምታቃጠል ከመሆኗ የተነሳ ጀሃነም እራሷ የአሏህን እርዳታ ትጠይቃለች ! የሰው ልጆች ይቋቋሙታልን ?

2ኛ🔴👉አል ዋይል ሸለቆ

👇👇👇👇👇👇

----->ይህቺ የጀሃነም ሸለቆ (ሶላትን ያለ አግባብ ለሚያዘገዩ ) የተዘጋጀች ስትሆን እጅግ በጣም ከሚያስፈሩ የጊንጥ እና የ እባብ አይነቶች የተሞላችዋ የጀሃነም ሸለቆ ነች ። አሏህ ይጠብቀን !

3ኛ🔴👉አል ሰቀር ሸለቆ

👇👇👇👇👇👇

----->ይህቺ የጀሃነም ሸለቆ የተዘጋጀችው (ሶላትን ለማይሰግዱት) ሲሆን ሰላት ማይሰግዱት ገና ሲገቡባት (ከሙቀቷ የተነሳ) አጥንታቸውን ምታቀልጥ የሆነች ነች። ሶላት የማይሰግዱ ሰዎች የሚቀሰቀሱት (ለፍርድ ሚቀርቡት ) ከነ ፊርኦን ከነ ሃማን ጋር ሲሆን!የነብያችንን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሸፋእ እንዳያገኙ አሏህ (ሱ.ወ.) ያደርጋቸዋል ። አሏህ ይጠብቀን !!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

እባክህን !!

በተቻለህ አቅም ይህንን ለምታቀውም ለማታቀውም share አድርግ ምን ታውቃለህ በዚህ ምክንያት ከጀሃነምና ከሸለቆዎቿ ትጠብቃቸውና ሰላታቸውን ወቅቱን ጠብቀው በጀማዓ መስጂድ ሄደው እንዲሰግዱና ሰላታቸውም ላይ ጠንካራ እንዲሆኑ ሰበብ ትሆን ይሆናል !!ያአሏህ ከጀሃነም እና ከሸለቆዎችዋ አንተ ጠብቀን!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
zahara ahmed shared a
Translation is not possible.

#ሸይኽ ኢብን ባዝ ተጠየቁ ፡ ሙቅ ውሃን በምናፈስበት ጊዜ

ቢስሚላህ እንላለንን፣ ይህም ጂን ቦታው ላይ ይኖራል ብሎ

በመፍራት ነው

መልስ፡

"አዎን! ቢስሚላህ ይበል ምን አልባት ቦታው ላይ ጂን ካለ

እንዲነቃ ለማድረግ ነው" ከዛም ሽይኹ እንዲህ አሉ" በርግጥም

በአንድ ወቅት አንድን ሰው ጂን ይዞት በሚቀራበት ቦታ ተገኝቼ

ነበር

#ሩቃ የሚያደርገው ሰው በሰውየው ላይ ለተደበቀው ጂኒ "ለምን

ያዝከው "አለው

#ጂንውም "የሞቀ ውሃ በአንዱ ልጄ ላይ ደፋና ገደለው "አለ

#የሚቀራዉ ሰውዬ ደግሞ "እሱ ልጅህ በቦታው መኖሩን

ስላላወቀ ነው" አለው

#ጂኒው ደግሞ "ለምን ቢስሚላህ አይልም ነበር እንዲያሳውቀው

(እንዲያነቃው)"

#ሽይኽ ዘይድ አል መድኸሊ ረሂምሁሏህ እንዲህ አሉ ፡

"ለማንኛውም የሞቀ ውሃ በፍሳሽ ትቦዎችም ይሁን በመሬት ላይ

አይደፋም ምክኛቱም መሬት በነዋሪዎች የተሞላች ነች

ምናልባትም በጂኖች አለም ወይም በትንንሽ ፍጡሮች ላይ ያርፋል

በዚህም ለበቀል ይነሳሱና ይይዙታል።ስለዚህ አንድ ሰው የሞቀን

ውሃ መድፋት ከፈለገ በቀዝቃዛ ውሃ ቅዝቃዘው የማያስቸግር

እስኪሆን ያብርደውከዛም ከፈለገ የፍሳሽ ትቦዎች ውስጥ ከፈለገ

መሬት ላይ ያፍሠው" ንግግራቸው እዚህ ጋር አለቀ ረሂመሁሏህ.

፟፟=========================

#ጉዳዩ አደገኛ ነው ሙስሊሞች ሆይ ነቃ በሉ ለወንድሞቻችሁ

ለእህቶቻችሁ ለእናቶቻችሁ አድርሱላቸው ስንትና ስንት እህቶች

በዚህ ሰበብ ችግር ውስት ይገባሉ ፓስታ የቀቀሉበትን ውሃ

አውጥተው በመድፋት ስንቱ ተለክፎዋል ስለዚህ አድርሱላቸው!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
zahara ahmed shared a
Translation is not possible.

ማዛጋት መንፈሳዊ ትርጉሙን ብታውቁት ኖሮ ማዛጋታቹን ታፍሩበት

ነበር ።

የማዛጋት ትርጉም በፊዚዮሎጂ....

ማዛጋት በሁሉም የጀርባ አጥንቶች ውስጥ የተለመደ እና አየር

ወደ ውስጥ የመማግ እና መተንፈስ እእንዲሁም የጡንቻዎችን

መወጠርን የሚያካትት የፊዚዮሎጂ እንቅስቃሴ ነው።

ማዛጋት የኛ የአጸፋዊ ስርዓታችን አካል ነው፣ እሱም በዋነኝነት

የሚቀሰቀሰው ያለፍላጎቱ በውጫዊ ተነሳሽነት ነው።

ለምን እንደምናዛጋ በፊዚዮሎጂ ብዙ ማብራሪያዎች አሉ፣ በጣም

የታወቀው ደግሞ በሳንባችን ውስጥ ያለው ዝቅተኛ የኦክስጂን

መጠን ነው።

ማዛጋት የሚጀምረው በማህፀን ውስጥ ነው, ነገር ግን በዋነኛነት

በአዋቂዎች ላይ ይታያል ። በልጆች ላይ የእንቅልፍ ጊዜ ወይም

አሰልቺ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ያነሰ ነው።

ይሁን እንጂ ማዛጋት ብዙውን ጊዜ እንደ ጸሎት ወይም ማሰላሰል

ባሉ በጣም አስፈላጊ ተግባራት ውስጥ ሊከሰት ይችላል።

ታዲያ በጸሎት ጊዜ ማዛጋት መንፈሳዊ ትርጉሙ ምንድን ነው?

በጸሎት ጊዜ ማዛጋት ያለውን ድብቅ መንፈሳዊ ትርጉም፣ ምን

እንደሚያመለክተው እና በሱ ልታፍሩበት እንደሚገባ በጥቂቱ ።

ስለ ማዛጋት ተምሳሌታዊ ትርጉሞች የበለጠ ለማወቅ ቀጣዩን

ፅሁፍ ያንብቡ

ማዛጋት መንፈሳዊ ትርጉም በእስልምና

በጸሎት ጊዜ ማዛጋት በእስልምና አብዛኛውን ጊዜ አማኞች

በሚጸልዩበት ወቅት ስለ ማዛጋት ብዙ ባህላዊ እምነቶች አሉ።

በጣም የተለመደው የሰይጣን ፈተና ነው።

በጸሎት ጊዜ ማዛጋት ሰይጣን ወደ ሰውነትህ ለመግባት

የሚሞክርበት መንገድ ነው።

እንደ ነቢዩ (ሰ.ዐ. ወ)ገለጻ፣ ሰይጣን የአማኞችን ትኩረት

አቅጣጫ ለማስቀየር እና እነሱን ለማዋረድ የሚሞክርበት

መንገድ ነው።

አማኞች ሲያዛጉ ሰይጣን በጣም ይደሰታል። ይህንንም የሚያሳካው

ሃሳባቸውን በመውረር እና ትኩረታቸውን እንደ ማዛጋት ባሉ

ፈተናዎች በማወክ ነው።

በተጨማሪም ወንዶች ሲያዛጉ የሚያሳዩዋቸው የፊት ገጽታዎች

በተለይ ለእሱ አስደሳች ሆኖ አግኝተውታል ታማኝ ሙስሊም

ከሰይጣን ፈተናዎች መራቅና ትጋቱን መጠበቅ አለበት።

ስታዛጋ ሰይጣን በአንተ ላይ ይስቃል፡- አንድ ሰው ሲያዛጋና አፉን

ሲከፍት የሚያሳየው የፊት ገፅታ ለሰይጣን የሳቅ ምንጭ ነው።

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል

አማኞች ሲያዛጉ በተቻለ መጠን ለረጅም ጊዜ ማዛጋቱን

በውስጣቸው መያዝ አለባቸው።

ሊቋቋሙት የማይችሉት ከሆነ ወዲያውኑ አፋቸውን በእጃቸው

ወይም በልብስ መሸፈን አለባቸው ይህ ምልክት የሚደረገው

ሰይጣን ወደ ሰውነት እንዳይገባ በመፍራት ነው።

እስልምና የመጨረሻው ሰላም ሀዲስ አንድ ሰው ከሞተ በኋላ

ሶስት ነገሮች አብረውት ይሄዳሉ

የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

የአደም ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል!! ከሶስት ነገሮች በስተቀር፡

1,ኛ ሰደቃ

2,ኛ እውቀቱ

3,ኛ ዱአው (ፀሎቱ )

ሰደቃ ጥቅሟ ቀጣይነት አለው

ዱአ እና እውቀት ከርሱ ጥቅማጥቅም የሚሰበሰብበት ነው

(ለምሳሌ ለሰዎች መልካም ነገር ብታስተምር ) ላንተ የፅድቅ

መንገድ ነው።

እነዚህ ሶስት ነገሮ ቀጣይነት ያላቸው እና ጥቅማቸው በአላህ

ዘንድ የሚታጨድበት ሲሆን ።ከሞት በኋላ የሚጠቅሙህ

ምንዳዎችን ይልኩልሃል

ረሱል (ሶ.ዐ.ወ) እውቀትን ከኔ ለሌላው አስተላልፉ አንድም

አረፍተ ነገር ብትሆን እንኩዋን ብለዋል።

እኔ ነቢያዊ መልእክቱን ለናንተ አድርሻለው

ይህንን ፅሁፍ ለወዳጅ ዘመዶዎ ይደርስ ዘንድ ሼር ያድርጉ

አላህ ሆይ በነዚህ ሶስት ነገሮች የምንጠቀም አድርገን

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
zahara ahmed shared a
Translation is not possible.

በአሜሪካን አይዞሽ ባይነት የህፃናትን ደም እጠጣች ያለቸው የጦር ወንጀለኛ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group