UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ሙዓዊያ እና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁማ በተጋጩ ግዜ ሁለት

ኢስላማዊ ስረወ መንግስት ተመሰረተ የሮሙ ንጉስ ይህን ሰምቶ

እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈ።

<<ከሮም ንጉሰ ነገስት ለ ሙስሊሞች መሪ ሙዐዊያ አቡ ሱፍያን!!

ባንተ እና በዐሊይ መካከል የተከሰተውን ግጭት

ሰምተናል።ስለዚህም ለሙስሊሞች መሪ አንተ መሆን

እንዳለብህም ስለምናምን አንተ ፍቃድህ ከሆነ የዐሊይን ጭንቅላት

ቀንጥሶ የሚያመጣልህን ወታደር ልላክልህ>>

ይህ ደብዳቤ ሙዐዊያ ጋር እንደደረሰም ሙዓዊያም

<<ከሙዓዊያ ለሮም መሪ!!! ሁለት ወንድማማቾች ስለተጣሉ

አንተ ምን አገባህ? አፍህን የማትዘጋ ከሆነ ጅማሬው እኔ ጋ የሆነ

እና ፍፃሜው አንተ ጋ የሆነ ሰራዊት ልኬ አንገትህን በማስቀንጠስ

ለዐሊይ በስጦታ መልኩ አበረክትለታለሁ>>

#ይህ_ትክክለኛ_ሙስሊሞች_ሳለን_ነው

_

___

ካሊድ ኢብን ወሊድ ለፐርሺያው ንጉሰ ነገስት እንዲህ ሲል

ደብዳቤ ፃፈለት

<<ስለም ትድናለህ። እንቢ ያልክ እንደሆን ግን፤ እናንተ ህይወትን

የምትወዱትን ያህል ሞትን የሚወዱ ሰራዊቶችን ይዤልህ

እመጣለሁ።>>

ንጉሱ ይህን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የቻይናውን ንጉስ የጦር እርዳታ

ሊለምነው ደብዳቤ ፃፈለት።

የቻይናውም ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ መልሶ ላከለት።

<<ንጉስ ሆይ! ተራራን እንኳን ለመናድ ካሰቡ ምንም

ከማያግዳቸው ወታደሮች ጋር ለመጋፈጥ አቅሙ ስለሌለኝ

ጥያቄህን መፈፀም አልችልም።>>

# ምን_ያህል_ሀያላን_እንደነበርን_ተመልከቱ

_

____

በደውለቱል ዑስማኒያ የአገዛዝ ዘመን የሙስሊም ወታደሮች የጦር

መርከቦቻቸውን ይዘው በአውሮፓ ደሴቶች ሲያልፉ በአከባቢው ያሉ

አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ሙስሊሞች መጥተው ፈትህ

እንዳያደርጉ በመፍራት ከበሮ ከመምታት እና ምንም አይነት ድምፅ

ከማሰማት ይቆጠቡ ነበር።

#ያኔ_ጀግና_ሳለን

_

____

በደውለቱል ኡስማኒያ የአገዛዝ ዘመን በያንዳንዴ ቤት ደጅ ላይ

ሁለት የበር ማንኳኩያዎች ይኖራሉ። አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ትንሽ

ነው። በትልቀኛው ከተንኳኳ አንኳኪው ወንድ ነው'ና በሩን ሊከፍት

ሚመጣው ወንድ ይሆናል። ነገር ግን በትንሸኛዋ ከተንኳኳ

አንኳኪዋ ሴት መሆኗ ስለሚታወቅ ሴት ትከፍትላታለች።

በዚያ ምርጥ ዘመን አንድ ቤት ውስጥ ሰው ከታመመ ደጅ ላይ

ቀይ አበባ ይንጠለጠል ነበር። ያን አበባ የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ

እዝያ ቤት በሽተኛ መኖሩን ስለሚያውቁ በበሩ ሲያልፉ ድምፃቸውን

ዝቅ ያደርጉ ነበር።

#ሹፍ_ምን_እንመስል_እንደነበር !!!

_

_

ግዜው ሰላሁዱን አል አዩቢ በይተል መቅዲስን ባስመለሰበት ግዜ

ነበር። እና ጦርነቱ ነገውን ሊጀመር ማታ ላይ የጦር መሪው

ሰላሁዲን የወታደሮቹን ድንኳን እየዞረ ሲያዳምጥ፤ ግማሹ ለይል

ይሰግዳል፣ ሌላው ቁርአን ይቀራል፣ የተቀሩት ደግሞ ይዘክራሉ።

ግን ድንገት በሆነ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ በድንኳኑ ውስጥ ያሉት

ሁሉም ተኝተው ነበር። ይህን ግዜ፦"በዚህች ድንኳን አዳሪዎች

ምክንያት ልንሸነፍ እንችላለን" ብሎ አለፈ።

#ማንተኛበት_ዘመን

_

___

ቀደምት ዑለማኦች በሶስት ነገራት አደራ ይባባሉ ነበር።

1፦ሰውዬው በሱ እና በአላህ መካከል ያለውን ግንኙነት ካሳመረ፤

በሱ እና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ያምርለታል።

2፦ሰውዬው ሚስጥራዊ ተግባሩን ካሳመረ አላህ ይፋዊ ተግባሩን

ያሳምርለታል።

3፦ሰውዬው የአኪራው ጉዳይ ካስጨነቀው አላህ የዱንያውንም

የአኪራውንም ጉዳይ ያግራራለታል።

_

_

#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው

ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ

ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።

በእለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ ቁርአንን መቅራት ካልተካተተ ትልቅ

ኪሳራ ነው።

ይህን ፅሁፍ በማሰራጨት ጓደኛህን እንድታነቃው ይከጀላል!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

سأظل طول العمر بابك أقرع | محمد عباس
سأظل طول العمر بابك أقرع | محمد عباس
01:01
Add to my audio
Download
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

♥ حدثوني عن الجنة.mp3
♥ حدثوني عن الجنة.mp3
04:15
Add to my audio
Download
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

☞«በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ዝምድናውን ይቀጥል‼️»

☞«ዝምድና ሚቀጥል ሰው አላህ የመረጠውና ትልቅ አድርጎም የፈጠረው ሰው ነው»

☞«ዝምድና መቀጠል በአኪራ ጀነት አለው፣ ባዱንያ ክብር አለው። »

☞«ዝምድናን መቁረጥ ትልቅ ወንጀል ነው፤ ከከባባድ ወንጀሎችም ውስጥ ይመደባል‼️»

☞ «ዝምድናን የሚቆርጥ ሰው ጀነት አይገባም ፤ባዱንያ ውርደት ነው፤ በአኪራ ስቃይ ነው»

☘️☘️🍀🌸🌺🌸🌸🌼🌸https://t.me/muhsinmooez

Telegram: Contact @muhsinmooez
t.me

Telegram: Contact @muhsinmooez

☞«በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ዝምድናውን ይቀጥል‼» ☞«ዝምድና ሚቀጥል ሰው አላህ የመረጠውና ትልቅ አድርጎም የፈጠረው ሰው ነው» ☞«ዝምድና መቀጠል በአኪራ ጀነት አለው፣ ባዱንያ ክብር አለው። » ☞«ዝምድናን መቁረጥ ትልቅ ወንጀል ነው፤ ከከባባድ ወንጀሎችም ውስጥ ይመደባል‼» ☞ «ዝምድናን የሚቆርጥ ሰው ጀነት አይገባም ፤ባዱንያ ውርደት ነው፤ በአኪራ ስቃይ ነው» ☘☘???????
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Mohammedselam Mohammed Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group