UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

መገፋት

.

.

አንዳንዴም መገፋት ጥሩ ነው። ጠንካራ ሰው በተገፋ፣በተበደለ ጊዜ ይበልጡን ይጠነክራል፤ ደካማ ሰው ደግሞ በተገፋ፣በተበደለ ጊዜ ከወደቀበት ለመነሳት ሲሞክር ይበልጡንም ሊሰበር ይችላል።

ወንድሜ ሁሉም ሰው ሊወድህም ሆነ ሊያከብር አይችልም እምነትህ በአላህ ላይ አድርግ በፍፁም በሰው ላይ እምነትህን እንዳታደርግ።

Brother የሰውን ልጅ ውደድ አክበር በፍፁም ግን እየተለማመጥክ አትኑር። ክብርህን ለመንካት ለሚፈልግ ሰው እየሄድክ በለው እንጂ በጭራሽ በክብርህ ጉዳይ ላይ እንዳትደራደር።

ወዳጄ ክብርህ በእጅህ ነው ያለው ክብርህን ለማንንም ቢሆን አሳልፈህ እንዳትሰጥ።

ክብርህን መንካት ለሚፈልጉ ሰዎች እዛው ባላችሁበት ፌሬን ያዙ በላቸው።

ሰዎች ብዙ ነገር ሊሉህ ይችላሉ ግን ንቀህ እርሳቸው እንጂ በፍፁም ለነሱ እጅ እንዳትሰጥ።

ምን አልባት እነሱ በሚሉህ ነገር ውስጥህ ሊሰማህ ይችላል አዎን ደግሞም ሊሰማህ ይገባል ምክንያቱም አንተ የሰው ልጅ ስለሆንክ።

ኢማም አሸ–ሻፊዒይ ረህመቱላሂ አለይ እንዲህ ይላሉ«አስቆጥተውት የማይቆጣ አህያ ነው ይቅርታ ጠይቀውት ይቅር የማይል ሸይጣን ነው» ስለዚህ ይሰማህ ግን ንዴትህ ቶሎ አቀዝቅዘው ለሸይጧን መጠቃቀሚያ እንዳትሆን።

ንግግራችንን በአላህ ቃል እንዝጋው................

وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَاهْجُرْهُمْ هَجْرًا جَمِيلًا

(سورة مزمل ١٠)

«(ካህዲያን)በሚሉህ ነገር ላይም ታገስ።(ንትርክ በሌለበት መልኩ) ባማረ ሁኔታ (ናቅ አድርገህ) ተዋቸው» (ሙዘሚል 10)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እናትና ልጅ በጠባቧ ክፍላቸው ውስጥ ተቀምጠዋል።

"እማ ርቦኛል" አለ ዩሱፍ ሆዱን እያሻሸ።

"ሀቢቢ ትንሽ ጠብቀኝ ቲማቲም ስልስ እሰራልሃለሁ" አለች እናት ፀጉሩን እያሻሸች።

ቤት ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ ባለመኖሩ የዩሱፍን ርሐብ ለማስታገስ ሁለት የቲማቲም ዘለላዎችን ፍለጋ ከቤት ወጣሁ። በበር በኩል አጮለቅኩና እስክመለስ በሩን እንዲዘጋ ነገርኩትና ወደ ጎረቤታችን ቤት አቀናሁ። ደጋግሜ አንኳኳሁ። መልስ የሚሰጠኝ አላገኘሁም። ከመንገዱ ማዶ ወደሚገኘው ወደ ኡሙ ሚቅዳድ ቤት አመራሁ።

  አንኳኩቼ ገባሁ። እንዴት ነሽ ልጆችሽስ ብዬ ሰላምታን አቀረብኩላት።

"አልሀምዱሊላህ ደህና ነን አላህ ይጠብቀን" ብላ መለሰችልኝ።

እያንዳንዱ ሰከንድ የመጨረሻ ሊሆን ይችላልና እኛ ፍልስጤማዊያን ጦርነት ውስጥ ስንሆን እንዲህ ነን ብዙ አንናገርም።

"ባለቤቴ ውሎ አዳሩ ሆስፒታል ሆኗል። ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወደ ቤት አልተመለሰም። አልሐምዱሊላህ" አልኩና ቲማቲም ካላት እንድትሰጠኝ ጠየቅኳት። በፌስታል ቋጥራ ያቀበለችኝን ቲማቲም ይዤ ልወጣ ስል "ሁኔታዎች ከባድ ሆነዋል በዱዓ እንተዋወስ" አለችኝ።

"በአላህ እርዳታ ይህ ሁሉ ያልፋል ኢንሻ አላህ..." እያልኳት ገና ንግግሬን ሳልጨርስ ከባድ ፍንዳታ ተሰማ። በጥቁር ደመና አየሩን ተሸፈነ። አካባቢው በአቧራ ተሞላ። አእምሮዬ የዩሱፍን ስም አቃጨለ። ከራሴ ጋር እየታገልኩ ወደ ጎዳናው ሮጥኩ። ሁሉም ይጮኻል።

ዩሱፍን አይታችዋል..? እዚህ አካባቢ አንድ ትንሽ ፍሪዝ የሆነ ልጅ አጊኝታችኋል? እያልኩ ጮኽኩ። መልስ የሰጠኝ ማንም አልነበረም። በአንቡላንስ ተጭኜ ሄድኩ። የመኪናው በር ሲዘጋ በዩሱፍ ላይ የዘጋሁት በር ታወሰኝ።

 

እየተብሰለሰልኩ አሽ-ሺፋእ ሆስፒታል ደረስኩ። ዩሱፍ....የሱፍ.... ብዬ ተጣራሁ። ለአላፊ አግዳሚው የ7 አመት ቆንጅዬ ልጄን አይታቹታልን? እያልኩ ጠየቅኩ።

የዓይኔ ማረፍያ ባለጥቅልል ፀጉሩ ጥቃቱ ፊቱን ከማበላሸቱ በፊት ቆንጆ ምስሉን በአእምሮዬ ሳልኩ። ፍርስራሽ አቧራ ከሰውነቱ ጋር ተጣብቆ በደም ተጨማልቆ አልጋ ላይ ተንጋሎ አገኘሁት። ዩሱፍ በባዶ ሆዱ ጌታውን ተገናኘ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
AmberiYa Kim Bado Changed her profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group