Amuna Mohammed Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

«ለመኖር ይለፋል»

----------------------------

በሀገሪቱ ላይ ሰው ሞልቶ ሰው ጠፋ፡

ትልቅ ያልነው ሁሉ ትልቅ እያጠፋ፡

ወዳጅ የተባለው እንደ ጠላት ከፋ፡

ሁሉም ይሯሯጣል የውስጡን አምቆ፡

ለገሀዱ ዓለም ቢታይ እንኳን ስቆ፡

ቢፈተሽ ብዙ አለው ልቡ ተሰንጥቆ፡

ያዘለው ጉዳጉድ ወንዝ ነው ሸለቆ፡

-------------------------------

ከፈገግታው ጀርባ ጥቁር ድንኳን ጥሎ፡

ልቡ መከፋትን ግፍን አንጠልጥሎ፡

ለመኖር እያለ ሁሉን ተቀብሎ፡

መኖርን ይዳዳል ይህም ያልፋል ብሎ፡

-------------------------------

ያስቸገረኝ ሁሉ አንድ ቀን ይጠፋል፡

እያለ በተስፋ እስኪ ሁሉም ያልፍል፡

በሰላ ጉልበቱ ዐለትን ይገፋል፡

ሞቱ እየናፈቀው ለመኖር ይለፋል፡

------------------------------

የፋሩቅ ባባ

----------------------------

http://t.me/nuredinal_arebi

http://t.me/nuredinal_arebi

Send as a message
Share on my page
Share in the group