ወንድሜ በመሞትህ ምን የሚታጣ ነገር አለ?
👉 በረሱልﷺ ሞት የአለማችን ግማሽ ወይም ሩብ ሳይሆን ሙሉ ደስታ ጠፍቷል።
👉 በአቡበክር ሞት ኢስላም ወንድ ልጁን አቷል
👉 በሰዐድ ኢብኑ ሙዐዝ ሞት የአረህማን
አርሽ ተንቀጥቅጧል።
👉 በኢማሙ አህመድ ሞት
ሱና ተግባሪው ተሰውሮበታል።
👉 በኢብኑ ተይሚያህ ሞት እውቀት
አባቱን አቷል።
👉 በሰለሀዲን ሞት የኢስላም ምድር
ጋሻው ተሰብሮበታል።
👇
ባንተ ሞትስ ምን ይታጣል⁉️
ምን ይሰበራል?
ምን ይቀነሳል?
👉 አሊም ሆነህ ሌሎችን ጠቅመሃል?
👉 የተጨነቀ ሲያማክርህ መፍትሔ ሰተሀል?
👉 ካለህ አውጥተህ የተራበን አብልተሀል?
የታረዘን አልብሰሀል?
👉 ዑመር ሲሞት ኢስላም ሩህሩህ ጀግናውን አቷል።
👉 ሀምዛህ ሲሞት ኢስላም አንበሳውን አቷል።
👉 አቡዑበይዳ ሲሞት ኢስላም ታማኝን አቷል።
👇
አንተ ስትሞት ኢስላም ምን ያጣል
ማህበረሰብህ ምን ይጎልበታል?
ራስህን ጠይቅ ⁉️
በመሞትህ ምን ሚታጣ ነገር አለ??
ወንድሜ እስቲ እራስህን መለስ ብለህ እየው!
||
©አቡ ረስላን