UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

የኢማን መዳከም ምልክቶች

የኢማን መዳከም ምልክቶች ብዙ ሲሆኑ እንደየድክመቱ ሁኔታና ደረጃ ከሰው ሰው ይለያያል። ከምልክቶች መካከል፡-

- የታዘዙበትን ነገር በሚፈለገው መልኩ ከመፈፀም አንፃር መሳነፍ፡፡ ለምሳሌ - ከጀማዓ ሶላት መዘግየት ። ከኢማሙ ጋር መጀመሪያ ሶፍ ላይ የሚገኝበት አጋጣሚ ኢምንት ነው፡፡ ሶላት ዉስጥ እያለም ቢሆን ዱንያዊ ሀሳቦች ይወሩታል፡፡ ኢማሙ ሶላትን ሲያጠናቅቅ ብቻ ነው ካለበት ሁኔታ የሚነቃው፡፡

- ለሱብሒ ሶላት ቀድሞ አለመነሳት። ለሰላትም በመስጂድ አለመገኘት። ከተኛበት ዐይኑን ሲገልጥ እና ሲነቃ ፀሐይ ቦግ ብላ ወጥታ ነው። የግዴታ ሶላቱን ሳይሰግድ፡፡ ባለመስገዱም የተነሳ የደረሰበትን ኪሳራ አያስተነትንም። ለዚህ ለደረሰበት አደጋ ምክንያት ሲያዝን፣ ሲጨነቅ፣ ሲረበሽ፣ ሲፈራ አይታይም። እንደዉም ምንም እንዳልተፈጠረ ነገር አድርጎ፣ ምንም ሳይመስለው ሙሉ ቀኑን ይዉላል።

- ወደ ጁመዓ ሶላት ዘግይቶ መሄድ። ኢማሙ ወደ ሚንበር ከወጡ በኋላ ነው መስጊድ የሚገባው፡፡ መላእክት ቀድመው የመጡትን ከመዘገቡና ከጨረሱ በኋላ ነው እሱ የሚገኘው፡፡

- ብተው ምንም ችግር የለውም በሚል እሳቤ ዋጋ ባለመስጠት ጭምር ብዙ የሱንና ሶላቶችን መተው። ግዴታ ሶላትን ብቻ ነው የሚሰግደው፣ ዱሐ ሶላትን አይሰግድም፣ ተውባን አያስብም፣ የሌሊት ሶላትን መስገድ ትዝ ብሎት አያውቅም፣ የኢስቲኻራ ሶላትንም እንዲሁ፡፡

- ኢማኑ የደከመ ከቁርአን የራቀ ነው፡፡ ቁርአን ቢያነብ በምላሱ ብቻ ነው፡፡ ስለ ጀነት እና እሳት የሚያወሳውን አንቀጽ ልብ አይልም፣ በመልዕክቶቹ ልቡ አይነካም፣ ዐይኑ አታነባም፣ ቁርአን ከጉሮሮው አይወርድም።

- ቁርአንን በማስተንተንና በማስተዋል ካለማንበብ በተጨማሪ ዚክር (አላህን ማውሳት) ይተዋል። እንዲሁም ለዱዓ እጁን አያነሳም፣ ቢያነሳም ወዲያዉኑ መልሶ ያወርዳል፡፡ ቀልቡና ምላሱ በተለያየ ዓለም ዉስጥ ናቸዉና።

- ከኢማን ድክመት መገለጫዎች መካከል - ነገሮችን ወንጀል ላይ ከመውደቅ እና ካለመውደቅ አንፃር ማየት ብቻ አንዱ ነው። መጥፎ ከመስራት ዓይንን አለመስበር ነው። የዚህ ዓይነቱ ቀልብ ባለቤት ቀስ በቀስ ወደ ሐራም ይጠጋል። በሂደትም ይዳፈራል፡፡

https://t.me/NejashiPP

Telegram: Contact @NejashiPP

Telegram: Contact @NejashiPP

ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አብዱልሰላም(የሰላም ሰጪው አምላክ ባሪያ)

ሙሀመድ(ምስጉን)

አህመድ(አመስጋኝ)

አዲል(ፍትሀዊ)

ቢላል(ሀበሻዊው የመልህክተኛው የቅርብ ሀዋርያ)

ሀይደር(አንበሳ)

ሀማድ(አመስጋኝ)

ሀሰን(ጥሩ/መልካም)

ሁሰይን(ውብ ቆንጆ)

ሀምዛ(አንበሳ/ጠንካራ)

ሁዘይፋ(ከሶሀቦች/ሀዋርያት አንዱ)

ጁነይድ(ወታደር/ተዋጊ)

ረሺድ(የተመራ)

ረያን(ክምከጀነት በሮች አንዱ፥ጾመኞች ሚገቡበት)

ኡሳማ(አንበሳ)

አቡበክር/ኡመር/ኡስማን/አሊይ-(የ4ቱ ቅን ኸሊፋዎች ስም)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
kellifa dulla shared a
Translation is not possible.

« ይህች ኡማ (ህዝብ) ከባድ የመከራ ምጥን እያሳለፈች ነው። ለሁሉም ምጥ ደግሞ ልጅ አለው። ለሁሉም ልጅ ደግሞ ጩኸትና ህመም አለው። »

ሸሂድ (በአላህ ፈቃድ) ሰይድ ቁጥብ (ረህመቱላሂ ዐለይሂ)

ይህ የመከራ ምጥ በነዚህ ልጆች ልብ ውስጥ የሚፈጥረው ልጅ ይናፍቀኛል። አንረሳህም! አንረሳውም!

[ሰምሀር ተክሌ]

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Alhmduliahum this wib

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የጭንቅ ጊዜ ዱዓ

لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ الْعَظِيْمُ الْحَلِيْمُ، لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيْمُ، لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَرَبُّ اْلأَرْضِ وَرَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيْمُ.

'ላኢላህ ኢ ለልላሁል አዚይሙል ሐሊይሙ ላኢላሀኢልለልላሁ ረብቡል ዐርሺል ዐዚይም ላኢላሀ ኢልለልላሁ ረብቡስሰማዋቲ ወረብቡል አርዲ ወረብቡል ዐርሺል ከሪይም'

ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ታላቅና ፅኑ ነው፡፡ ከአላህ ውጪ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የታላቁ ዐርሸ ጌታ ነው፡፡ ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሰማያትና የምድር÷ እንዲሁም የታላቁ ዓርሽ ጌታ ነው፡፡

اَللَّهُمَّ رَحْمَتَكَ أَرْجُو فَلاَ تَكِلْنِيْ إِلَى نَفْسِيْ طَرْفَةَ عَيْنٍ، وَأَصْلِحْ لِيْ شَأْنِيْ كُلَّهُ، لاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ.

'አልሏሁምመ ረህመተከ አረጁ ፈላ ተኪሊኒ ኢላ ነፍሲይ ጠርፈተ አይኒን ወአስሊሀ ሊይ ሸእኒይ ኩልለሁ ላኢላሀ ኢልላ አንተ'

አላህ ሆይ! እዝነትህን አሻለሁ፡፡ ለቅፅበት ያክል እንኻ ለራሴ አትተወኝ፡፡ ሁለ ነገሬን ያማረ አድርግልኝ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡

لاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ سُبْحَانَكَ إِنِّيْ كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِيْنَ.

'ላኢላህ ኢልላ አንተ ሱብሃነከ ኢንኒ ኩንቱ ሚን አዝዛሊሚይን'

ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ ከበደለኞች አንዱ ነኝ፡፡

اللهُ اللهُ رَبِّي لاَ أُشْرِكُ بِهِ شَيْئًا.

'አልሏሁ አልሏሁ ረብቢይ ላኡሽሪኩ ቢሂ ሸይኣ'

አምላኬ አላህ ነው፡፡ በርሱ ላይ ምንንም ኃይል አላጋራም፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group