የኢማን መዳከም ምልክቶች
የኢማን መዳከም ምልክቶች ብዙ ሲሆኑ እንደየድክመቱ ሁኔታና ደረጃ ከሰው ሰው ይለያያል። ከምልክቶች መካከል፡-
- የታዘዙበትን ነገር በሚፈለገው መልኩ ከመፈፀም አንፃር መሳነፍ፡፡ ለምሳሌ - ከጀማዓ ሶላት መዘግየት ። ከኢማሙ ጋር መጀመሪያ ሶፍ ላይ የሚገኝበት አጋጣሚ ኢምንት ነው፡፡ ሶላት ዉስጥ እያለም ቢሆን ዱንያዊ ሀሳቦች ይወሩታል፡፡ ኢማሙ ሶላትን ሲያጠናቅቅ ብቻ ነው ካለበት ሁኔታ የሚነቃው፡፡
- ለሱብሒ ሶላት ቀድሞ አለመነሳት። ለሰላትም በመስጂድ አለመገኘት። ከተኛበት ዐይኑን ሲገልጥ እና ሲነቃ ፀሐይ ቦግ ብላ ወጥታ ነው። የግዴታ ሶላቱን ሳይሰግድ፡፡ ባለመስገዱም የተነሳ የደረሰበትን ኪሳራ አያስተነትንም። ለዚህ ለደረሰበት አደጋ ምክንያት ሲያዝን፣ ሲጨነቅ፣ ሲረበሽ፣ ሲፈራ አይታይም። እንደዉም ምንም እንዳልተፈጠረ ነገር አድርጎ፣ ምንም ሳይመስለው ሙሉ ቀኑን ይዉላል።
- ወደ ጁመዓ ሶላት ዘግይቶ መሄድ። ኢማሙ ወደ ሚንበር ከወጡ በኋላ ነው መስጊድ የሚገባው፡፡ መላእክት ቀድመው የመጡትን ከመዘገቡና ከጨረሱ በኋላ ነው እሱ የሚገኘው፡፡
- ብተው ምንም ችግር የለውም በሚል እሳቤ ዋጋ ባለመስጠት ጭምር ብዙ የሱንና ሶላቶችን መተው። ግዴታ ሶላትን ብቻ ነው የሚሰግደው፣ ዱሐ ሶላትን አይሰግድም፣ ተውባን አያስብም፣ የሌሊት ሶላትን መስገድ ትዝ ብሎት አያውቅም፣ የኢስቲኻራ ሶላትንም እንዲሁ፡፡
- ኢማኑ የደከመ ከቁርአን የራቀ ነው፡፡ ቁርአን ቢያነብ በምላሱ ብቻ ነው፡፡ ስለ ጀነት እና እሳት የሚያወሳውን አንቀጽ ልብ አይልም፣ በመልዕክቶቹ ልቡ አይነካም፣ ዐይኑ አታነባም፣ ቁርአን ከጉሮሮው አይወርድም።
- ቁርአንን በማስተንተንና በማስተዋል ካለማንበብ በተጨማሪ ዚክር (አላህን ማውሳት) ይተዋል። እንዲሁም ለዱዓ እጁን አያነሳም፣ ቢያነሳም ወዲያዉኑ መልሶ ያወርዳል፡፡ ቀልቡና ምላሱ በተለያየ ዓለም ዉስጥ ናቸዉና።
- ከኢማን ድክመት መገለጫዎች መካከል - ነገሮችን ወንጀል ላይ ከመውደቅ እና ካለመውደቅ አንፃር ማየት ብቻ አንዱ ነው። መጥፎ ከመስራት ዓይንን አለመስበር ነው። የዚህ ዓይነቱ ቀልብ ባለቤት ቀስ በቀስ ወደ ሐራም ይጠጋል። በሂደትም ይዳፈራል፡፡
https://t.me/NejashiPP