UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

ስለ ባንኮች ይህን ታውቃላችሁ⁉️

=====================

(ሌላም ልንገራችሁ!)

||

✍ ከታች ትናንት ባያያዝኩት ከወለድ ነፃ ባንኮች ዳታ ላይ በባለፈው የጁን 2023 መረጃ መሠረት 191.72 ቢሊዮን ብር አሰባስበዋል። ከዚህ መካከል 74.52 ቢሊዮን የሚሆነውን ብቻ አበድረዋል (ፋይናንስ አድርገዋል)።

በአሁኑ ወቅት ዲፖዚት የተደረገው ወደ 210 ቢሊዮን ብር ገደማ እንደሆነና ፋይናንስ የተደረገው 78 ቢሊዮን ገደማ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

በአጭሩ ከወለድ ነፃ ካጠራቀሙት ገንዘብ 39%ቱን ብቻ አበድረዋል። ቀሪውን ግን በወለድ ነው ያበደሩት ማለት ነው። የሚገርመው ይሄንኑ 39%ቱን እንኳ በዋናነት ከፍተኛውን ገንዘብ ያበደሩት ለስንት ሰዎች እንደሆነ ታውቃላችሁ? 80 ገደማ ለሆኑ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ታዋቂ ለሆኑ ባለሃብቶች!

ሌላው ከ80ዎቹ ውጭ ያለው ብድር ቢሰጠውም አንድ ሁለት ሚሊዮን ወዘተ የመሳሰለችው አነስተኛ መጠን ናት።

ድሃውሳ! ድሃውማ ገንዘቡን ባንክ ላይ ያጠራቅማል፤ ባለሃብት ባንክ ላይ ድሃው ያጠራቀመውን ገንዘብ ይበደርና ይሠራበትና የበለጠ ባለሃብት ይሆናል። ከድሃው ጋር ያለውን የሃብት ርቀት በደንብ ያሰፋል። ድሃውማ ልበደር ቢልም ኮላተራል በሚል ሽፋን ማንም አያቀምሰውም።

√ መፍትሄው ምንድን ነው?

ከወለድ ነፃ እንሠራለን የሚሉ ባንኮች በመስኮት ቁጥር 5 ላይ ከወለድ ነፃ መስኮት ብለው ብራችንን ተቀብለውን፤ በመስኮት ቁጥር 3 ላለው የወለድ መስኮት ብሩን አሳልፈው ሰጥተው ለወለድ ተጠቃሚው ደንበኛ ይሰጡታል። ይህ አሠራር ይቅርና የእውነት ከወለድ ነፃ እንሠራለን ካሉ ራሳቸውን በቻለ ባንክ ይምጡና ሙስሊሙም እዛ ላይ ብድር ብቻ ሳይሆን ሼር እየገዛ ይጠቀማል።

*

√ እኛስ? አሁንማ ኢስላማዊ ባንኮች ስላሉን፤ ከነርሱ ሼር እየገዛን፣ አካውንት እየከፈትን፣ እነርሱን እየተጠቀምን አቅማቸውን እናጠንክር። ያኔ በርካታ ብራንች መክፈት ይችሉና ተደራሽ ይሆናሉ፣ ብድርም ሆነ የውጭ ምንዛሬ ለመስጠት ይችላሉ።

እንደ ሌሎች በኮላተራል ብቻ ማወሳሰባቸውን ሳያስቀጥሉ ድሃውንም ጭምር ያማካለ ተጠቃሚነት ይዘረጋሉ፤ በአማና መሰል መስፈርቶችን ላሟላ ድሃ ሳይቀር ይጠቅማሉ። ከዘካህ መስጠት ባሻገር ሠርቶ እንዲበላ ካፒታል ያመቻቻሉ።

ይህን ለማድረግ ቆራጥ አመራር ወሳኝ ነው። አስተያየት የሚያዳምጥ፣ ለውይይት ዝግጁ የሆነና ማንኛውንም ቅሬታ ለማስተናገድ በሩ ለውይይት ክፍት የሆነ ወርዶ የሚሠራ አመራር ያስፈልጋል። በርግጥም ከሂጅራና ከዘምዘም ባንኮች ይህን የሚያሳይ አመርቂ ተስፋ ታዝቢያለሁ፤ ኢንሻ አላህ ወደፊትም የበለጠ ይሆናል።

*

√ በአጭሩ ከአሁን በኋላ ድሃን የበለጠ ድሃ የሚያደርግ፣ በባለሃብትና በድሃ መካከል ያለን ርቀት የሚያሰፋ፣ ከወለድ ነፃ መስኮት ብሎ የሙስሊም ብር ተቀብሎ በወለድ መስኮት ለኸምር ቤቶች ሳይቀር ብድር የሚሰጥበት አሠራር ማክተም አለበት።

ሰሞኑን የተጀመረው የመጅሊስ የዑለማዎች ስብሰባም አንዱ አጀንዳው ከወለድ ነፃ ባንኮች ጉዳይ ስለሆነ ይሄን ጉዳይ በደንብ በሰፊወ ቢወያዩበት ኡማውን ከሐራሙ (ከወለድ) ታድጎ መጥቀም የሚቻልበት አሠራር እንዲዘረጋ ማድረግ አለባቸው።

አላህ ያግዛቸው‼

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🔴ሰበር :

የየመን ጦር ኃይሎች መግለጫ

==================

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው:–

♦️ዛሬ ማለዳ የየመን ጦር ሃይሎች የባህር ሃይል በሁሉን ቻይ አላህ እርዳታ በባብ አል-ማንዳብ በሚገኙ ሁለት የእስራኤል መርከቦች ማለትም “ዩኒቲ ኤክስፕሎረር” መርከብ እና “ቁጥር ዘጠኝ” መርከብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽሟል።

♦️የመጀመሪያው መርከብ በባህር ሃይል ሚሳኤል እና ሁለተኛው መርከብ በባህር ሃይል ድሮን ኢላማ የተደረገ ነው።

♦️ኢላማ የተደረጉት ሁለቱ መርከቦች የየመን የባህር ኃይል ሃይሎችን የማስጠንቀቂያ መልእክት ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው።

♦️የየመን ታጣቂ ሃይሎች የእስራኤል መርከቦች በጋዛ ሰርጥ በሚገኙ ፅኑ ወንድሞቻችን ላይ እያደረሱት ያለው ጥቃት እስኪቆም ድረስ የእስራኤል መርከቦች በቀይ እና በአረብ ባህር እንዳይጓዙ መከልከላቸውን እናሳውቃለን።

♦️የየመን ጦር ሃይሎች ይህን መግለጫ እና ከዚህ ቀደም የየመን ጦር ሃይሎች ያወጣቸውን መግለጫዎች የሚጥሱ ከሆነ ህጋዊ ኢላማ እንደሚሆኑ ለመላው የእስራኤል መርከቦች ወይም ከእስራኤላውያን ጋር ግንኙነት ላላቸው መርከቦች ማስጠንቀቂያችንን ድጋሚ እናቀረባለን።

ሰነዓ፣ 20 ጁማዳ አል-አወል 1445 ሂጅራ

ዲሴምበር 3 ቀን 2023 ዓ.ም

በየመን ጦር ሃይሎች የተሰጠ

መረጃው ለሌሎችም እንድደርስ ሸር ያድርጉት🙏

📢ሌሎች ፈጣን እና የተለያዩ መረጃዎች እንድደርስዎ ቻናላችንን ይቀላቀሉ

👇👇👇

ቴሌግራም: ► https://t.me/Nejashimedia888

Telegram: Contact @Nejashimedia888

Telegram: Contact @Nejashimedia888

እስልምና ብቸኛውና ትክክለኛው መለኮታዊ እምነት ነው፤ እንደ ሌሎች ሰው ሠራሽ ኃይማኖቶች edit, create, update, delete… የሚደረግ መሠረታዊ አስተምህሮ የለውም። ሃሳብ አስተያየት ካለዎት @Nejashimedia_Bot ያገኙናል።
Send as a message
Share on my page
Share in the group
ummu Muhammad 5 Changed her profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

የመን ይፋዊ በሆነ መልኩ እስራኤል ጋር

ጦርነት ያወጀች የመጀመሪያዋ ሀገር ሁናለች

...

ሀሩን ሚዲያ፥ ጥቅምት 20/2016

...

የየመን ታጣቂ ሃይሎች ሚሳኤሎችን እና ዩኤቪዎችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፋቸውን ተናግረዋል።

...

“የእኛ የታጠቁ ሃይሎች በእስራኤል የተለያዩ ኢላማዎች ላይ እጅግ ከባድ የሚባሉ የባለስቲክ እና የክሩዝ ሚሳኤሎችን እንዲሁም በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አስወነጭፈናል" ሲል ገልጿል። ከነዚህ ውስጥ ረጅም ርቀት የሚጓዙ ሚሳኤሎች የእስራኤል የኒውክለር ማብላያን ኢላማ ያደረጉ ጭምር ነበሩ ተብሏል።

...

የየመን ጦር ሃይሎች ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ያህያ ሳሪ የእስራኤል ጥቃት እስኪቆም ድረስ ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም የተሻሉ ጥቃቶችን ማድረሳችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

...

© ሀሩን ሚዲያ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ስለ ፈለስጢን ምን አዲስ ነገር አለ⁉️

========================

✍ የፈለስጢን (የጋዛ ሙስሊሞች) ጉዳይ በየቀኑ አሳዛኝነቱ ቀጥሏል። በየቀኑ የንጹሐን ህይዎት እየተቀጠፈ ነው፣ በርካታ መሠረት ልማቶች እየወደሙ ነው።

ዛሬ ይፋ በሆነው መረጃ መሠረት እስካሁን 5087 ሙስሊሞች በጽዮናዊቷ ያላባራ የቦምብ ዝናብ ተገድለዋል፣ ከነዚህ መካከል 2055 የሚሆኑት ህፃናት ሲሆኑ 1119 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። 217ቱ አዛውንቶች ነበሩ። 1500 የሚሆኑት በፍርስራሽ ስር እንደጠፉ ናቸው፤ ከመካከላቸው 800 የሚሆኑት ህፃናት አሉ። እስካሁን ድረስ ጀናዛቸው እንኳ አልተገኘም። 15,273 የሚሆኑት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አጠቃላይ የተፈናቀሉት 1 ሚሊዮን 400 ሺህ አካባቢ ሲሆኑ፤ 685 ሺህ የሚሆኑት ከሌሎች ቤተሰቦቻቸው ጋር ተፈናቅለዋል፣ 565 ሺህ የሚሆኑት ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞችና የእርዳታ ሥራ ኤጀንሲ (UNRWA) ጋር ግንኙነት ወዳላቸው ት/ቤቶች ተፈናቅለዋል፣ 101 ሺህ የሚሆኑት በመስጂዶች፣ በቤተ ክርስቲናትና በህዝባዊ ቦታዎች ተጠልለዋል፣ 70 የሚሆኑት በ67 ት/ቤቶች ተፈናቅለው ይገኛሉ።

የተለያዩ ሃገራት መንግስታት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ቢጠይቁም፤ አሜሪካ በጸጥታው ም/ቤት ያላትን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ተጠቅማ የፈለስጢናዊያን ጭፍጨፋ እንዲቀጥል አድርጋለች።

ምን ያክል የፈለስጢን ህፃናትና ሴቶች ተጨፍጭፈው ሲያልቁ እንደምትረካ አይታወቅም።

ሌላውም ዓለም በሰልፍ ድጋፉ እያሳዬ ቢሆንም ከዚያ የዘለለ ማድረግ አልቻለም።

በጋዛ አሁንም ቢሆን የውሃ፣ የመብራት፣ የምግብና የነዳጅ ማዕቀብ እንደተጣለ ነው። ባለፈ ብቻ 20 የሚሆኑ የጭነት መኪኖች ገብተው ነበር። ግን ለ2+ ሚሊዮን ህዝብ ምንም ማለት አይደለም። የጋዛን ሰብዓዊ ቀውስ ለመመከት በየቀኑ መቶ የጭነት መኪኖች መግባት አለባቸው።

አላህ በጥበቡ ከላይ ፈረጃውን አውርዶ ካሉበት በላእ ይገላግላቸው እንጂ እየተካሄደ ያለው ይፋዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ታሪክ የማይረሳው እጅግ አሰቃቂ እልቂት ነው።

ከዱዓእ ውጭ አቅም የለንምና ሁሌም ወንድሞቻችንን እናስታውሳቸው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group