Translation is not possible.

ስለ ባንኮች ይህን ታውቃላችሁ⁉️

=====================

(ሌላም ልንገራችሁ!)

||

✍ ከታች ትናንት ባያያዝኩት ከወለድ ነፃ ባንኮች ዳታ ላይ በባለፈው የጁን 2023 መረጃ መሠረት 191.72 ቢሊዮን ብር አሰባስበዋል። ከዚህ መካከል 74.52 ቢሊዮን የሚሆነውን ብቻ አበድረዋል (ፋይናንስ አድርገዋል)።

በአሁኑ ወቅት ዲፖዚት የተደረገው ወደ 210 ቢሊዮን ብር ገደማ እንደሆነና ፋይናንስ የተደረገው 78 ቢሊዮን ገደማ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

በአጭሩ ከወለድ ነፃ ካጠራቀሙት ገንዘብ 39%ቱን ብቻ አበድረዋል። ቀሪውን ግን በወለድ ነው ያበደሩት ማለት ነው። የሚገርመው ይሄንኑ 39%ቱን እንኳ በዋናነት ከፍተኛውን ገንዘብ ያበደሩት ለስንት ሰዎች እንደሆነ ታውቃላችሁ? 80 ገደማ ለሆኑ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ታዋቂ ለሆኑ ባለሃብቶች!

ሌላው ከ80ዎቹ ውጭ ያለው ብድር ቢሰጠውም አንድ ሁለት ሚሊዮን ወዘተ የመሳሰለችው አነስተኛ መጠን ናት።

ድሃውሳ! ድሃውማ ገንዘቡን ባንክ ላይ ያጠራቅማል፤ ባለሃብት ባንክ ላይ ድሃው ያጠራቀመውን ገንዘብ ይበደርና ይሠራበትና የበለጠ ባለሃብት ይሆናል። ከድሃው ጋር ያለውን የሃብት ርቀት በደንብ ያሰፋል። ድሃውማ ልበደር ቢልም ኮላተራል በሚል ሽፋን ማንም አያቀምሰውም።

√ መፍትሄው ምንድን ነው?

ከወለድ ነፃ እንሠራለን የሚሉ ባንኮች በመስኮት ቁጥር 5 ላይ ከወለድ ነፃ መስኮት ብለው ብራችንን ተቀብለውን፤ በመስኮት ቁጥር 3 ላለው የወለድ መስኮት ብሩን አሳልፈው ሰጥተው ለወለድ ተጠቃሚው ደንበኛ ይሰጡታል። ይህ አሠራር ይቅርና የእውነት ከወለድ ነፃ እንሠራለን ካሉ ራሳቸውን በቻለ ባንክ ይምጡና ሙስሊሙም እዛ ላይ ብድር ብቻ ሳይሆን ሼር እየገዛ ይጠቀማል።

*

√ እኛስ? አሁንማ ኢስላማዊ ባንኮች ስላሉን፤ ከነርሱ ሼር እየገዛን፣ አካውንት እየከፈትን፣ እነርሱን እየተጠቀምን አቅማቸውን እናጠንክር። ያኔ በርካታ ብራንች መክፈት ይችሉና ተደራሽ ይሆናሉ፣ ብድርም ሆነ የውጭ ምንዛሬ ለመስጠት ይችላሉ።

እንደ ሌሎች በኮላተራል ብቻ ማወሳሰባቸውን ሳያስቀጥሉ ድሃውንም ጭምር ያማካለ ተጠቃሚነት ይዘረጋሉ፤ በአማና መሰል መስፈርቶችን ላሟላ ድሃ ሳይቀር ይጠቅማሉ። ከዘካህ መስጠት ባሻገር ሠርቶ እንዲበላ ካፒታል ያመቻቻሉ።

ይህን ለማድረግ ቆራጥ አመራር ወሳኝ ነው። አስተያየት የሚያዳምጥ፣ ለውይይት ዝግጁ የሆነና ማንኛውንም ቅሬታ ለማስተናገድ በሩ ለውይይት ክፍት የሆነ ወርዶ የሚሠራ አመራር ያስፈልጋል። በርግጥም ከሂጅራና ከዘምዘም ባንኮች ይህን የሚያሳይ አመርቂ ተስፋ ታዝቢያለሁ፤ ኢንሻ አላህ ወደፊትም የበለጠ ይሆናል።

*

√ በአጭሩ ከአሁን በኋላ ድሃን የበለጠ ድሃ የሚያደርግ፣ በባለሃብትና በድሃ መካከል ያለን ርቀት የሚያሰፋ፣ ከወለድ ነፃ መስኮት ብሎ የሙስሊም ብር ተቀብሎ በወለድ መስኮት ለኸምር ቤቶች ሳይቀር ብድር የሚሰጥበት አሠራር ማክተም አለበት።

ሰሞኑን የተጀመረው የመጅሊስ የዑለማዎች ስብሰባም አንዱ አጀንዳው ከወለድ ነፃ ባንኮች ጉዳይ ስለሆነ ይሄን ጉዳይ በደንብ በሰፊወ ቢወያዩበት ኡማውን ከሐራሙ (ከወለድ) ታድጎ መጥቀም የሚቻልበት አሠራር እንዲዘረጋ ማድረግ አለባቸው።

አላህ ያግዛቸው‼

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group