UMMA TOKEN INVESTOR

Essa Sufian shared a
Translation is not possible.

Attempts to save a child during the Zionist occupation bombing of the Nuseirat camp in the central Gaza Strip 🇵🇸

በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ በሚገኘው የኑሴራት ካምፕ ላይ የጽዮናውያን ወረራ የቦምብ ጥቃት በደረሰበት ወቅት ልጅን ለማዳን የተደረጉ ሙከራዎች 🇵🇸

محاولات إنقاذ طفل أثناء قصف الاحتلال الصهيوني لمخيم النصرة وسط قطاع غزة 🇵🇸

17 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የዓለም ህዝብ ግን አይገርምም⁉️

=======================

(ዓለም በዚህ ዘመን አይታው የማታውቀው የጦር ወን'ጀልና የዘር ጭፍ'ጨፋ በጘዝ'ዛ)

||

✍ 365 km² ስፋት ባላት አነስተኛ ከተማ ውስጥ 2.3+ ሚሊዮን ዜጎች ተጠጋግተው ይኖሩባታል። በዚህች densely populated በሆነች ከተማ ላይ ለተከታታይ 3 ሳምንታት ያላባራ ከ12 ሺህ ቶን በላይ ቦም'ብ ሲዘንብ፤ በዚህም ሳቢያ፦

1) በትንሹ 7,028 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙስሊሞች ሲገ'ደሉ፣

2) ከ70% በላይ የሚሆኑት ህፃናትና ሴቶች ሲሆኑ (2,913 ህፃናትና 1,709 ሴቶች)፣

3) 18,482 የሚሆኑት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ሲዳረጉ፣

4) ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 481 የሚሆኑት ሲገ'ደሉ (ከመካከላቸው 209 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው።)፣

5) ከ1,650 በላይ የሚሆኑት ጀናዛቸው እንኳ ሳይገኝ እስካሁን ድረስ በቦ'ምብ በፈራረሱት ህንፃዎች ስር ሲሆኑ (ከመካከላቸው 940 ህፃናት አሉበት።)፣

6) 731 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙሉ ቤተሰቦች ሲገ'ደሉ፣

⑦) 101 የጤና ባለሙያዎች ሲገ'ደሉና 100 የሚሆኑት ሲቆስሉ፣

⑧) 12 ሆስፒታሎችና 32 የጤና ማዕከላት በነዳጅ እጥረትና በቦምብ ጥቃት ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ፣

9) በኢንኩቤተር ውስጥ የሚገኙ ከ130 በላይ የሚሆኑ ህፃናት ያሉበት ሆስፒታል ባጋጠመው በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ነፍሳቸው በእንጥልጥል ላይ ሲገኝ፣

⑩) ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ንጹሐን ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች፣ በት/ቤቶች፣ በሆስፒታል ግቢዎች፣ በመስጂዶችና ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ሳለ በዛው ባሉበት ጥቃቱ ሲያገኛቸው… (ከሰው ነፍስ አይበልጥምና ወደ አመድነት ስለተቀየሩት ውብ ህንፃዎችና መሠረተ ልማቶችማ አውርተን አንዘልቀውም።)

የሰለጠነ ተብዬው ዓለም አሁንም «ጦርነቱ ይቁም!» ከማለት ይልቅ «እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት፣ ሐማስ መጥፋቱን ማረጋገጥ አለባት፣ ከጎንሽ ነን፣ ሐማስ ሽብ'ርተኛ ነው፣ በሐማስ ጥቃት ለሞቱት እስራኤላዊያን አዝነናል!…» እያሉ ነው።

ትንሽ አሻሻልን የሚሉት ደግሞ ጦርነቱ መቆም የለበትም፤ ግን የተወሰነች እርዳታ ይግባላቸው ይላሉ።

እስካሁን በጋዛ መብራት የለ፣ ውሃ የለ፣ ምግብ የለ፣ ነዳጅ የለ…። በዚህ የተነሳ የቆሰሉትና መደበኛ ህመም የሚታመሙትም መታከም አልቻሉም።

ዙሪያውን በከበባ ስለሆነ ለጠናበት ታማሚ የውጭ ሕክምና እንዲያገኝ ማድረግ አልተቻለም።

እስራኤል ከላይ በአየር ከምታዘንበው የቦምብ ዝናብ ባሻገር ከምግብና ውሃ እንዲሁም ከሕክምና ከልክላ በጅምላ ጭፍ'ጨፋ የጦር ወን'ጀልና የዘር ማፅ'ዳት ወንጀል በመፈጸም ላይ ትገኛለች። ይህ ሁሉ የሚሆነው ዓለም እያዬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ተመድ ተብዬውም ሆነ የትኛውም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚል ተቋም ሁሉ የውሃ ሽታ ሆኗል። የነርሱ ህግ እነርሱን ለማዳን እንጂ ለሌላው አይሠራም። እነርሱ ዘንድ የሙስሊም፣ የዓረብና የአፍሪካዊ ሞት ከውሻ'ቸው ሞት በታች ነው።

ግን ነፍስ ሁሉ እኩል ናትና የእጃቸውን አንድ ቀን ማግኘት አይችሉም። ነገ ላይ በሌላ የነርሱ አካል ላይ ጥቃት ሲፈጸም በሚዲያቸውም ሆነ ባልተጻፈው ህጋቸው ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ሲለፍፉ እናገኛቸዋለን።

አላህ ውርደታቸውን ያቅርበው፤ ለተበዳዮች ነስሩን ያፍጥነው።

አላህ የአሸናፊዎች ሁሉ አሸናፊ የሆነ ጥበበኛና ታጋሽ ጌታ ነው። አንድ ቀን አይርላቸውም።

||

https://ummalife.com/MuradTadesse

t.me/MuradTadesse

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Essa Sufian Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group