Ibnu abas Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1
Ibnu abas shared a
Translation is not possible.

አንድ ትንሽዬ ልጅ ለወላጆቹ፦"3 ጥያቄዎቼን የሚመልስልኝ

ጠንካራ ዑለማ አምጡልኝ" አላቸው።

ወላጆቹም በአከባቢያቸው ያለ አንድ ኡስታዝ አመጡለትና

አገናኙት።

💧ልጁ፦"ማን ነህ አንተ? እኔ ስለምጠይቀውስ ጥያቄ መልስ

እንዳለህ ምን ያህል እርግጠኛ ነህ?"

➣ኡስታዙ፦"ስሜ ዐብዱላህ ይባላል ከአላህ ባሪያዎችም አንዱ

ነኝ።ለምትጠይቀኝ ጥያቄዎችም በአላህ ፍቃድ መልስ

እሰጥሀለሁ።"

💧ልጁ፦"አንተ ግን ብዙ ዑለማኦች ሊያብራሩልኝ ያልቻሉትን

ጥያቄዬን እንደምትመልስልኝ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነህ?

➣ኡስታዙ፦"ልመልስልህ እሞክራለሁ በአላህ እገዛ።"

💧ልጁ፦" 3 ጥያቄዎች አሉኝ።

❶ ➛ እውነት ፈጣሪ አለ? አዎ አለ የምትል ከሆነ አሳየኝ የት ነው

ያለው?

❷ ➛ ቀዷ እና ቀደር ምንድነው?

❸ ➛ እውነት ሸይጣን ከእሳት የተፈጠረ ከሆነ እንዴት በእሳት

ይቀጣል? ከእሳት ተፈጥሮ እሳት አያቃጥለውም።

"ይሄን ግዜ ኡስታዙ እሳት በሆነች ጥፊ ልጁን አጮለው።

💧ልጁ፦"እንዴ!!! ለምን ትመታኛለህ? ምን ሚያስመታ ነገር

ተናገርኩ?

➢ኡስታዙ፦"አረ!!! እኔ አልተቆጣሁም ግን ያሁኗ ጥፊ ለሶስቱም

ጥያቄዎችህ መልስ ናት።

💧ልጁ፦"እንዴት? አልገባኝም...

➢ኡስታዙ፦"በጥፊ ስመታህ ምን ተሰማህ?

ልጁ፦"በጣም ህመም ተሰማኝ።

➢ኡስታዙ፦"ህመም እንዳለ ታምናለህ?"

💧ልጁ፦"አዎ አምናለሁ።"

➢ኡስታዙ፦"አሳየኝ የት ነው ያለው?"

ልጁ፦"አይ አለ ግን ማየት እንኳን አይቻልማ"

➢ኡስታዙ፦"ይህ ለመጀመሪያ ጥያቄህ መልስ ነው።ሁላችንም

አላህ እንዳለ እናምናለን ነገር ግን ማየት አንችልም።

እሺ ዛሬ እንደምመታህ ትናንት ማታ ገምተህ ነበር?"

ልጁ፦"አልገመትኩም።"

➢ኡስታዙ፦"እሺ እኔስ አንተን ዛሬ እንደምመታህ ትናንት ማታ አስቤ

ነበር?

💧ልጁ፦"አላሰብክም።"

➢ኡስታዙ፦"ለ2ኛ ጥያቄህ መልስ ይህ ነው ቀዷ ቀደር

የሚባለው።

እሺ እኔ አንተን የመታሁበት እጄ 💧ከምንድነው የተፈጠረው?"

ልጁ፦"ከአፈር"

➢ኡስታዙ፦"እሺ በእጄ የመታሁት ያንተ ፊትስ ከምንድነው

የተፈጠረው?"

ልጁ፦"ከአፈር"

➢ኡስታዙ፦"ስመታህ ምን ተሰማህ?"

💧ልጁ፦"አመመኝ"

➢ኡስታዙ፦"ከአፈር የተሰራ አፈርን ሲመታው

እንደሚያሳምመው ሁላ ከእሳት የተሰራውም ሸይጣን በእሳት

ሲቀጣ በጣም ያመዋል።"

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ibnu abas shared a
Translation is not possible.

ዛሬ የጉራጌ ዞኗ አስኩት በነዚህ ውብ ሐፊዞቿ ምርቃት ፍክት ብላ ውላለች።

በጉራጌ ዞን ጌቶ ወረዳ እስኩት ከተማ የሚገኘው ዑመር መርከዝ ላለፉት ተከታታት 3 አመታት ያክል የአላህን ቃል ቁርኣንን የሐፈዙ እና መሠረታዊ የዲን ትምህርቶችን የተማሩ ተማሪዎችን አስተምሮ ለማኅበረሰቡ አበርክቷል።

በአካባቢወወ ያለው ማኅበረሰብ መሠረታዊ የዲን ትምህርት ላይ እጅግ በጣም ክፍተት ያለበት እና ብዙ ሥራዎች የሚጠይቅ ቦታ በመሆኑ ይህን የመልካም ሥራ ፍሬ ማየት በጣም የሚያስደስት ነው። ለዚህ ሰበብ የሆናችሁ ሁሉ አላህ ኢኽላሱን ሰጥቶ ምንዳችሁን ከፍ ያድርገው። አላህ ይቀበላችሁ።

መሰል መልካም ተግባራት ሊጠናከሩና ሊበዙ ይገባል። ማሻ አላህ!

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group