ዘምዘም ውኃ የመጠጣት
አደብና ዱዓእ
▪️የዘምዘም ውኃ የተባረከ፣ ምድር ላይ ካሉ ውኃዎች ሁሉ የላቀና በላጩ፤ ለተራበ ሰው ምግብና ለታማሚ ፈውስ እንደሆነ ነቢዩ ﷺተናግረዋል።
አላህ ዘምዘምን ከቦታዎች ሁሉ መርጦ ከተከበረው ቤቱ (ከዕባህ) ዘንድ ማድረጉም የዘምዘምን ክብር ከሚያሳዩ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።
▪️ዘምዘምን በጥሩ ኒያህ (መልካምን ነገር አቅዶ) መጠጣት ተወዳጅ ተግባር ነው።ለምሳሌ ኢማንና የዲን ዕውቀትን፣ ጥሩና ደጋግ ልጆችን፣ ጤንነትን፣ ሰፊና ንጹሕ ሲሳይን ወዘተ ማግኘትን አቅዶና ነይቶ፣ እንዲሁም ዱዓእ አድርጎ መጠጣት ይገባል።
ታላቁ ሰሓቢይ ዐብዱሏህ ኢብኑ ዐባስ ዘምዘም ሲጠጡ የሚከተለውን ዱዓእ ያደርጉ እንደነበረ ዳረቁጥኒይና ሌሎችም ዘግበዋል፥
"اللهم إني أسألك عِلما نافعا ورزقا طيبا وشِفاءً مِن كلِ داء"
አላህ ሆይ ጠቃሚ ዕውቀትን፣ ሰፊ/መልካም ሲሳይን፣ ከበሽታዎች በሙሉ ፈውስን እጠይቅሃለሁ"::
ዘምዘም ሲጠጣ:-
▪️1/ቀድሞ ቢስሚላህ ማለት፣
▪️2/ቀድመው ሁለት ጊዜ ትንንሽ ፉት እያሉ በመቅመስ ሶስተኛው ላይ በደምብ ግጥም አድርጎ መጠጣት፣
▪️3/ ሲጠጡ በዛ አድርጎ (ጠግቦና ሆድን ሞልቶ) መጠጣት፣
▪️4/ጠጥተው እንደጨረሱ ከላይ የተገለጸውን ወይም ተመሳሳይና የግል ጉዳይን የሚገልጽ ዱዓእ ማድረግ ይመረጣል።
በርካታህ ሊቃውንት ሰሒሕ/ትክክለኛ ባሉት ሐዲሥ እንደተነገረው "ዘምዘም ውኃ ለተጠጣለት ዓላማ ይሆናል"። መካህ ሐረም ከሚገኘው ዘምዘም ውጪ ዓለም ላይ የትም ተመሳሳይ ትሩፋትና ጥቅም ያለው የተባረከ ውኃ የለም። ሊኖርም አይችልም።