Translation is not possible.

የኢሰራኤል ተጨማሪ ሸንፈት

ኢሰራኤል ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የፍልሰጤሙ ነፃ አውጪው #ሀማሰ #በአል_ሺፋ ሆሰፒታል መሬት ሰር መሸጓል ከኢሰራኤል ተይዘው የተወሰዱ ዜጎቻችንም እዛ ነው ያሉት ለዛም እርግጠኛ የሆነ የደህንነት መረጃ አለን ይሄንንም ሆሰፒታሉ ውሰጥ በመግባት በማሰረጃ ለአለም ህዝብ እናሳያለን እሰረኞቻችንንም እናሰለቅቃለን እያለች በምድርና በሰማይ ሰትደበድብ፣ ንፁሀንን ዜጎችን ሰትጨፈጭፍ ከርማ ትላንት ሆሰፒታሉን ተቆጣጥራ ለ18 ሰዓት ሰትበረብር ብትከርምም በጅምላ ከጨፈጨፈቻቸው የንፁሀን አሰክሬን፣ አገልግሎት ተቋርጦባቸው ከሚሰቃዩ ህሙማንና በሆሰፒታሉ ከተጠለሉ ዜጎች በሰተቀር ያገኘቸው ነገር የለም

ይሄ ሀማሰ #በአል_ሸፋ_ሆሰፒታል መሬት ሰር መሸጓል የሚለው ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የተሰራበትና ደጋፊዎቿ ምዕራባዊያን የተቀበሉት እንዲሁም ከዚህ በፊት ላወደመቻቸው የህዝብና የሀይማኖት ተቋማት ማርከሻ ይሆናት ዘንድ በጉጉት ሰትጠብቀው የነበረ ቢሆንም በአለም አደባባይ ፊት ባዶዋን ቀርታለች።

ይሄን ዘርፈ ብዙ ሸንፈቶቿ ላይ የተጨመረውን የሚዲያ ሸንፈቷን ለመሸፈን ከ18 ሰዓት በኃላ ምንጩ ያልታወቀ የተወሰነ የጦር መሳሪዎችን በመቅረፅ የሬንቲሲ ሆሰፒታል ላይ የሰራችውን አይነት ድራማዋን ለመድገም ያደረገቸው ሙከራ በድጋሚ ሳይሳካ ቀርቷል።

ሀማሰ እሰራኤል የምታነሳቸውንውንጀላዎች ወድቅ በማድረግ የአለም አቀፍ መርማሪ ገብቶ ጉዳዩን እንዲያጣራ ጥሪ አቅርቧል

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group