suleiman Demssie Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

ያሳዝናል‼

========

✍ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ባካሄደችው የአየር ድብደባ በትንሹ 11,078 ፍልስጤማውያን፣ 4,506 ህፃናት እና 3,207 ሴቶች ተገድ'ለዋል፤ ከ27,490 በላይ ቆስለዋል።

- ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 94 ህጻናትን ጨምሮ 260 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።

- 1,500 ህጻናትን ጨምሮ 2,700 ያህል ሰዎች አሁንም በፍርስራሹ ውስጥ አሉ።

- 1,130 የፍልስጤም ቤተሰቦች ተጨፍጭፈዋል።

- በእስራኤል ጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል 70% የሚሆኑት ህጻናት፣ ሴቶች እና አዛውንቶች ናቸው።

- 198 የጤና ባለሙያዎች ሲሞቱ ከ100 በላይ ቆስለዋል።

- በትንሹ 46 የፍልስጤም ጋዜጠኞች ተገድለዋል።

- 21 ሆስፒታሎች እና 47 ጤና ጣቢያዎች በነዳጅ መመናመን ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል።

- እስራኤል ነዳጅ ማቋረጧን በቀጠለችበት ወቅት ከ130 በላይ የፍልስጤም ጨቅላ ሕጻናት በአደጋ ላይ ናቸው።

በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ ኃያላን ሁሉ ተሰባስበው 351 km² ስፋት ባላትና ላለፉት 17+ አመታት በማዕቀብ (ከበባ) ውስጥ ባሳለፈች አንድት አነስተኛ ከተማ ላይ የጀምላ ዘር ማፅዳት ወንጀል እየፈጸሙ ይገኛሉ።

አንድ እንኳ ሃግ የሚላቸው የለም። ይህች አነስተኛ ከተማም ከ2.4 ሚሊዮን ገደማ ህዝቦቿ ጋር እስካሁን ድረስ አንድ ወር ሙሉ ትንፋሿ ሳይቋረጥ በጽናት ትግሏን ቀጥላለች።

መጨረሻውን አላህ ይወቅ።

ኢላሃና! እኛ ከዱዓእ ውጭ አቅም የለንምና አንተ ጣልቃ ግባ‼🤲🤲🤲

||

t.me/MuradTadesse

https://ummalife.com/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

ለፈገግታዎ

ህፃኑ «ጠለዐል በድሩ ዐለይና» የሚለውን ነሺዳ እያቀነቀነ ወደ መጻዳጃ ቤት ገባ። የልጁን ድርጊት የተመለከተው አባት የመፀዳጃ ቤቱን በር ከፍቶ በመግባት ልጁን መታው። ህፃኑ ክፉኛ አለቀሰ። የአብራኳ ክፋይ መመታቱን ያስተዋለችው እናትም ባለቤቷን «ለመሆኑ ልጁን የመታኸው ለምንድን ነው?» በማለት ጠየቀችው። ባለቤቷም «መጸዳጃ ቤት ውስጥ ሆኖ ቁርአን ሲቀራ ታዲያ ምን እንዳደርገው ታስቢያለሽ?» በማለት ምላሽ ሰጣት። የህጻኑ እናትም «ሲያቀነቅን የነበረው እኮ ቁርአን ሳይሆን የዐረብኛ ግጥም ነው» በማለት አስረዳችው። በዚህ ጊዜ የአባትዬው እንባ እንደ ደራሽ ወንዝ ድንገት ጎረፈ። ሚስቱም «ምን ሆነህ ነው እንዲህ ስቅስቅ ብለህ የምታለቅሰው?» ብላ ብትጠይቀው ጊዜ:-

«ላለፉት 30 ዓመታት ይህን ግጥም ሰላት ውስጥ ስቀራው ነበር» ብሏት አረፈ።

«أخبار الحمقى والغفلين»

ከተሰኘው የኢብነል ጀውዚ መጽሃፍ የተቀነጨበ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Arab Spring‼️

የአረብ አብዮት‼️

የዛሬ 13 አመት አካባቢ ሙሀመድ ባውዚዚ የተባለ ቱኒዚያዊ ጎዳና ላይ እንዳይሰራ በፖሊስ በመከልከሉ አደባባይ ላይ እራሱን በእሳት አቃጠለ።

ከሱ ሞት በኋላ ዲሞክራሲ እንፈልጋለን ያሉ አረቦች ቱኒዚያን ሊቢያን ሶሪያንና ሌሎችንም ሀገሮች በተቃውሞ ሰልፍ አጥለቀለቁ።

የተቃውሞ ሰልፎች ውጤት ግን በተጋላቢጦሽ ሁኖ ሀገራቱ ወደሙ፡ ፈራረሱ፡ በመቶ ሺዎች ተገደሉ፡ በሚሊየኖች ደግሞ ተሰደዱ።

እኛም ሀገር ድረስ ተሰድደው መጥተው ከሞቀው ቤታቸው ወጥተው ለልመናና ለጎዳና ህይወት ተዳርገዋል።

እዚህ'ጋ ሁለት ነገሮች አስተውሉ!

በመጀመሪያ ሙሀመድ ባውዚዚ የተባለው ቱኒዚያዊ እነሱ ሸሂድ ቢሉትም፡ ቃቲለ ነፍስ/ነፍስን የገደለ ነው፡ ህይወቱም ያጠፋው ለዲኑ ብሎ ሳይሆን ለዱንያዊ ጥቅም ነው፡ አሏህ ፊትም መጠየቁ አይቀሬ ነው ‼️

ሌላው ደግሞ ከሱ ሞት በኋላ መሬት አንቀጥቅጥ ሰልፍ ሲያደርጉ የነበሩ አረቦች ዐላማ የነበረው ቁርአንና ሀዲስን፡ የሸሪዓ ፍርድን ፈልገው ሳይሆን፡

አውሮፓዎች ዴሞክራሲ ብለዋል የፈለጉትን የሚገድሉበት፡ የፈለጉትን ሀገር የሚያፈርሱበት የጣጉት ህግ/መተዳደሪያ ፈልገው ነው ‼️

ሀቂቃ ከነዚህ ሀገራት የበለጠ አስተማሪ ሊኖረን አይችልም።

ሰላማዊ ሰልፍ የሚባለው ነገር በዲን የሌለ ከመሆኑም በተጨማሪ፡ ምን ያህል ጎጂ እንደሆነ ከነዚህ ሀገራት መማር ያስፈልጋል።

ድል የሚገኘው በተውሂድና በሱና አሏህን ስንገዛ፡ በሰለፎች መንገድ ላይ ቀጥ ስንል፡ ዑለሞችን ስናማክርና የዑለሞችን ምክርና ትዕዛዝ ስንቀበል ብቻ ነው ‼️

https://t.me/abufurat

https://ummalife.com/YunusHassen

Send as a message
Share on my page
Share in the group