UMMA TOKEN INVESTOR

7 ай Тәрҗемәсе
Татарчага аудару мөмкин түгел.

🌹"ሰለፎች እና የጀመዓ ሰላት!"🌹

☞ወኪዕ እንዳለው፦ "አል-አዕመሽ የተባለው ታላቅ ዓሊም እድሜው ወደ ሰባ ተቃርቦ የመጀመሪያው ተክቢራ አምልጦት አያውቅም። ለሁለት አመት ያህል ተከታትዬዋለሁ አንድ ረከዐ አምልጦት ተነስቶ ሲሞላ አላየሁትም።"

[تاريخ بغداد (5/10)]

――――――――――

☞ረቢዓ ኢብኑ ዘይድ ፦ "ለአርባ አመታት ያህል የዙህር አዛን ጥሪ መንገደኛ ወይም ህመም ላይ ካልሆንኩ በስተቀር መስጂድ ውስጥ ሆኜ እንጂ አልተጠራም!"

[سير أعلام النبلاء (240/5)]

――――――――――――

☞ሰዒድ ኢብኑል ሙሰየብ ፦ "ለሀምሳ አመታት የመጀመሪያው ተክቢራ አምልጦኝ አያውቅም። ለሀምሳ አመታትም በሰላት ውስጥ የሰዎችን ማጅራት አልተመለከትኩም!" ሁልግዜ የመጀመሪያው ሰልፍ ላይ ነበርና የሚሰግዱት።

[وفيات الأعيان( 375/2)]

―――――――――――

☞ኢብኑ ሰዕድ ፦ "ለሰላሳ አመታት ያህል ቤተሰቤ ውስጥ ሆኜ አዛን አልሰማሁም!"

[الطبقات الكبرى (131/5)]

―――――――――――

☞ኢብኑ ሰማዓህ ፦ "እናቴ የሞተች እለት ሲቀር ለአርባ አመታት የመጀመሪያዋ ተክቢራ አምልጣኝ አታውቅም!"

[سير أعلام النبلاء (636/10)]

―――――――――――

☞ሱፍያን ኢብኑ ዑየይናህ፦ "ሰላትን ከማክበር ከሚካተቱ ነገሮች ውስጥ አንዱ ከኢቃም በፊት መስጂድ መገኘት ነው።"

[صفة الصفوة( 235/2)]

―――――――――――

☞ኢብኑ መዒይን፦ "ኢብራሂም ኢብኑ መይሙን አል-መርወዚይ መዶሻውን አንስቶ የሰላት ጥሪን ከሰማ ወደ ታች ሳይመልሳት እዛው ባለችበት ይይዛትና ለሰላት ይነሳ ነበር።"

[تهذيب التهذيب (151/1)]

――――――――――――

☞ሱፍያን ኢብኑ ዑየይናህ ፦ "ለሰላት እስኪጠራ ድረስ የማይመጣ መጥፎ ባሪያ አትሁን!  የሰላት ጥሪ ከመጠራቱ በፊት ቀደም ብለህ መስጂድ ተገኝ።"

[التبصرة (137/1)]

――――――――――

☞ኢብራሂም አን ነኸኢይ ፦ "ከመጀመሪያው ተክቢራ የሚዘናጋ ሰው ካጋጠመህ ከሱ እጅህን ታጠብ!"

[صفة الصفوة (88/3)]

―――――――――

☞ሙሐመድ ኢብኑ ሙባረክ አስ ሱሪይ ፦ "ሰዒድ ኢብኑ ዐብዲል ዐዚዝ የጀመዓ ሰላት ካመለጠው ያለቅስ ነበር።"

[تذكرة الحفاظ (219/1)]

―――――――――――

☞አንድ ቀን መይሙን ኢብኑ ሚህራን ወደ መስጂድ ሲመጣ ሰዎች ሰግደው ተመልሰዋል ተባለ። እሱም "ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! ይህች ያመለጠችኝ የጀመዓ ሰላት ደረጃዋ የዒራቅ ንጉስ ከመሆን ለኔ የተሻለ ነው!" አለ። 

[مكاشفة القلوب (364/1)]

――――――――――

☞ሓቲም አል አሰም ፦ "አንድ ቀን ሰላተል ጀመዓ አምልጦኝ አቡ ኢስሓቅ አል ቡኻሪይ ብቻ አፅናናኝ። ልጄ ሞቶ ቢሆን ከአስር ሺህ ሰው በላይ ያፅናናኝ ነበር። ይህ የሆነው ሰዎች ዘንድ የዲን አደጋ ከዱንያ አደጋ አንፃር በጣም የቀለለ በመሆኑ ነው።"

[مكاشفة القلوب(364/1)]

⇡እኔም እላለሁ፦

»ዛሬ ሙስሊሞች የጁሙዓ ሰላትን እንደሚሰግዱት የፈጅር ሰላትን መስጂድና መንገዶችን አጨናንቀው  ቢሰግዱ የት በደረሱ! የፈጅር ሰላትና የዒሻ ሰላትን መስጂድ አለመስገድ ከመናፍቃን ምልክቶች ውስጥ ነውና ነቃ በሉ ወንድሞች!

☞ ከሞቀ ብርድ ልብስህ ወጥተህ ታጥበህ ወይም ውዱእ አድርገህ መስጂድ ከተፍ ያልክ ግዜ ነው "ወንድ" የምትባለው!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
7 ай Тәрҗемәсе
Татарчага аудару мөмкин түгел.

بسم الله الرحمن الرحيم

#ይድረስ_መገላለጥና_እርቃነሽ_መሄድ_ፋሽን_አድርገሽ_እየሔድሽ_ላለሽዉ_ሙስሊምዋ_እህቴቴቴቴቴቴቴቴ

አዎ የዛሬዋ ዱንያ በብልጭልጭና አርተፊሻል ጌጥ ባጌጡና በተንቆጠቆጡ ዉብ ነገራቶች የተሞላች ናት። ነገር ግን እነዚህ ዉብ የተባሉ ነገራቶች በአጠቃላይ ማጣፈጫዉ አንቺ ሲት ልጅ ነሽ ብለዉ ያሞካሹሻል ያደንቁሻል። በቃ ያላንቺ እቺ ምድር ጎደሎ እንደሆነች ያወጉሻል። ሁሌም ሲያገኙሽ ማሬ ወለላዮ እያሉሽ ይሸነግሉሻል ልብሽ ብርት ጥፍት የምትል የሶላር አምፖል እስክትመስልሽ ድረስ ዎና በሆነ ፍቅራቸዉ ያከንፉሻል።

ይህ የከነፈዉ አምሮሽ በለዘብ ድምፅ በጨዋ አንደበት ስክር እያደረጉሽ ዛሬ ብንገናኝ ብለዉ ይቀጥሩሻል። አንቺም መገናኘት ማዉራት መጫወት በፍቅር አይንት መተያየት በዉንሽም በህልምሽም የነበረ ሐሳብሽ ስለነበር በአንዴ እንቢ ላለማለት እንደመግደርደር ብለሽ ቅር የሚልህ ከሆነ እሺ በቃ እንገናኝ ብለሽ ትቀጥሪዉ አለሽ።

ስአቱ አልመሽ አልነጋ ይልሻል በቃ ራትሽ ቁርስሽ ምሳሽ በስሜት ታጅቦ አብሮሽ ካልተቀመጠ ዎና አፍቃሪሽ ጋር ሰዓቱ ይደርሳል። ተቻኩለሽ ለባብሰሽ ተቀባብተሽ ትሄጃለሽ ታገኚዋለሽ ታወሪዋለሽ ትመሰጫለሽ ትቅበዠበዢያለሽ ታልሚአለሽ በዉስጣዊ ሃሴት ፍንድቅድቅ ትያለሽ ብዙ ሁነቶችን አብሮ እንደሳለፈ ሰዉ በሃሳብ በወሬ በቁምነገር እና የፍቅር በሚመስሉ ወሬዎች ያጦዝሻል።

አዎ ልክ ብለሃል ይመስለኛል ይሆናል ነዉ ኧረ እያልሽ እየዘባረቅሽ ልብሽ መሸነፋ ታሳይዋለሽ። ኦኬ ይልና መክነፍሽንና መጦዝሽን ሲረዳ ጨዋ ለመምሰል በቃ ብዙ ቆየን ቀን አያልቅ በሌላ ጊዜ በሰፊዉ እየተዝናናን እናወራለን ሲልሽ ደስ ሳይልሽ እሺ ብለሽ እየተቅበዘበዝሽ ትለዪዋለሽ።

በመለየትሽ ደስተኛ አይደለሽም ብዙ መቆየት ምርጫሽ ነበር ነገር ግን ላዛሬ በቃ ስትባይ አማራጭ እንደሌለዉ አሳ እሺ ብለሽ ተለይተሽ ለቀጣይ ቀጠሮ እንገናኝ ይሆን እያልሽ በተስፋ ትለዪዋለሽ።

በቀጣይ ቀጠሮ:-

🔥🔥

🔥🔥🔥

🔥🔥🔥🔥

🔥🔥🔥🔥🔥

🔥🔥🔥🔥🔥🔥

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

ይቀጥላል

የቴሌግራም ግሩፓችን ይቀላቀሉ

https://t.me/+SZr_FCsW3uUgu6G7

ዑማላይፍ ላይ ፎሎ እንደራረግ

https://ummalife.com/umma1698085195

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Mohammed Hussen Сhanged his profile picture
7 ай
Татарчага аудару мөмкин түгел.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Mohammed Hussen Сhanged his profile picture
7 ай
Татарчага аудару мөмкин түгел.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group