Translation is not possible.

🌹"ሰለፎች እና የጀመዓ ሰላት!"🌹

☞ወኪዕ እንዳለው፦ "አል-አዕመሽ የተባለው ታላቅ ዓሊም እድሜው ወደ ሰባ ተቃርቦ የመጀመሪያው ተክቢራ አምልጦት አያውቅም። ለሁለት አመት ያህል ተከታትዬዋለሁ አንድ ረከዐ አምልጦት ተነስቶ ሲሞላ አላየሁትም።"

[تاريخ بغداد (5/10)]

――――――――――

☞ረቢዓ ኢብኑ ዘይድ ፦ "ለአርባ አመታት ያህል የዙህር አዛን ጥሪ መንገደኛ ወይም ህመም ላይ ካልሆንኩ በስተቀር መስጂድ ውስጥ ሆኜ እንጂ አልተጠራም!"

[سير أعلام النبلاء (240/5)]

――――――――――――

☞ሰዒድ ኢብኑል ሙሰየብ ፦ "ለሀምሳ አመታት የመጀመሪያው ተክቢራ አምልጦኝ አያውቅም። ለሀምሳ አመታትም በሰላት ውስጥ የሰዎችን ማጅራት አልተመለከትኩም!" ሁልግዜ የመጀመሪያው ሰልፍ ላይ ነበርና የሚሰግዱት።

[وفيات الأعيان( 375/2)]

―――――――――――

☞ኢብኑ ሰዕድ ፦ "ለሰላሳ አመታት ያህል ቤተሰቤ ውስጥ ሆኜ አዛን አልሰማሁም!"

[الطبقات الكبرى (131/5)]

―――――――――――

☞ኢብኑ ሰማዓህ ፦ "እናቴ የሞተች እለት ሲቀር ለአርባ አመታት የመጀመሪያዋ ተክቢራ አምልጣኝ አታውቅም!"

[سير أعلام النبلاء (636/10)]

―――――――――――

☞ሱፍያን ኢብኑ ዑየይናህ፦ "ሰላትን ከማክበር ከሚካተቱ ነገሮች ውስጥ አንዱ ከኢቃም በፊት መስጂድ መገኘት ነው።"

[صفة الصفوة( 235/2)]

―――――――――――

☞ኢብኑ መዒይን፦ "ኢብራሂም ኢብኑ መይሙን አል-መርወዚይ መዶሻውን አንስቶ የሰላት ጥሪን ከሰማ ወደ ታች ሳይመልሳት እዛው ባለችበት ይይዛትና ለሰላት ይነሳ ነበር።"

[تهذيب التهذيب (151/1)]

――――――――――――

☞ሱፍያን ኢብኑ ዑየይናህ ፦ "ለሰላት እስኪጠራ ድረስ የማይመጣ መጥፎ ባሪያ አትሁን!  የሰላት ጥሪ ከመጠራቱ በፊት ቀደም ብለህ መስጂድ ተገኝ።"

[التبصرة (137/1)]

――――――――――

☞ኢብራሂም አን ነኸኢይ ፦ "ከመጀመሪያው ተክቢራ የሚዘናጋ ሰው ካጋጠመህ ከሱ እጅህን ታጠብ!"

[صفة الصفوة (88/3)]

―――――――――

☞ሙሐመድ ኢብኑ ሙባረክ አስ ሱሪይ ፦ "ሰዒድ ኢብኑ ዐብዲል ዐዚዝ የጀመዓ ሰላት ካመለጠው ያለቅስ ነበር።"

[تذكرة الحفاظ (219/1)]

―――――――――――

☞አንድ ቀን መይሙን ኢብኑ ሚህራን ወደ መስጂድ ሲመጣ ሰዎች ሰግደው ተመልሰዋል ተባለ። እሱም "ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! ይህች ያመለጠችኝ የጀመዓ ሰላት ደረጃዋ የዒራቅ ንጉስ ከመሆን ለኔ የተሻለ ነው!" አለ። 

[مكاشفة القلوب (364/1)]

――――――――――

☞ሓቲም አል አሰም ፦ "አንድ ቀን ሰላተል ጀመዓ አምልጦኝ አቡ ኢስሓቅ አል ቡኻሪይ ብቻ አፅናናኝ። ልጄ ሞቶ ቢሆን ከአስር ሺህ ሰው በላይ ያፅናናኝ ነበር። ይህ የሆነው ሰዎች ዘንድ የዲን አደጋ ከዱንያ አደጋ አንፃር በጣም የቀለለ በመሆኑ ነው።"

[مكاشفة القلوب(364/1)]

⇡እኔም እላለሁ፦

»ዛሬ ሙስሊሞች የጁሙዓ ሰላትን እንደሚሰግዱት የፈጅር ሰላትን መስጂድና መንገዶችን አጨናንቀው  ቢሰግዱ የት በደረሱ! የፈጅር ሰላትና የዒሻ ሰላትን መስጂድ አለመስገድ ከመናፍቃን ምልክቶች ውስጥ ነውና ነቃ በሉ ወንድሞች!

☞ ከሞቀ ብርድ ልብስህ ወጥተህ ታጥበህ ወይም ውዱእ አድርገህ መስጂድ ከተፍ ያልክ ግዜ ነው "ወንድ" የምትባለው!

Send as a message
Share on my page
Share in the group